እራስንመማር። እኔነትንመማር።
እራስንመማር?
እኔነትንመማር?
ምህረት ነው። ሙሉሰውነት ነው። ላቂያነት ነው።
ውስጥነት ነው። ተፈጥሯዊነት ነው። ሰዋዊነት። ሥርዬትም ነው። ዕርቀ ሰላምም ነው። እራስን ማስተዋል። እራስን ፊደል መቁጠር። ተነባቢም አናባቢም።
ህሊናዊነት። ተደሟዊነት። ብጡላዊነት። ግን ይቻላል ወይ? ግን እንችላለን ወይ? ትሁታዊው ጥያቄ ይህ ነው።
ለመቻላችን ስለማውቀው። የምንፈልገውን እራሱ ጊዜ ወስደን አናወያዬውም። ለዚህ ነው ቅጥልጥላችን ወዘተረፈ የሆነው።
የራስ ንግግር?
የራስ ጥሞና?
የራስ ግምገማ?
ማን ይችለዋል?
ማን ይፈትነዋል?
ማን ያሸንፈዋል?
እራስን ማሸነፍ ፍላጎትን መጥኖ ከመነሳት ይቻለዋል። ፍላጎት በዬሰከንዱ ይፈላል። ይንፎለፎላል። ያን ለመያዝ ስንራወጥ ከሁሉም ሳንሆን መሐል ቤት እንቀራለን።
ዛሬ ያለውን የዘመኑ ባህሪ ሳስበው ያ ሁሉ ድካም ለኦነግ ልዕልና፣ ለኦነግ ብፅዕና መሆኑን ሳይ ከራስ ጋር መማር የማቃት፣ እኔነትን ለመማር ካለመፍቀድ የመነጨ ነው።
እራስንመማር። እራስንማጥናት። በእኔ ውስጥ እኔ ስለመኖሬ ማረጋገጥ የሚቻልበት ሜቶሎጂ ነበር። ግን የሰው ልጅ እራሱንለመማር ከሚያጠፋው ይልቅ የሌሎችን ለመኮረጁ፣ የሌሎችን ለመዋስ፣ ሌሎችን ለመምሰል የሚያጠፋው ጊዜ፣ የሚያፈሰው መዋዕለ ንዋይ ይበልጣል።
ቀድሞ ነገር እራስንመማር አጀንዳም ሆኖ አያውቅም። ግን ትዝ ብሎን ያውቃልን? ሥርጉትሻ ሥርጉተ ሕይወትን ለማጥናት፣ እራሷን የምርምር ማዕከል አድርጋ የወደቀችበትን የተነሳችበትን ላጥና ብትል ስንት ግድፈት በተሰናበተ።
እኔ እንደ እኔ፣ እናንተም እንደ እናንተ የራስነት አስተምህሮ ላይ ቢተጋ በወል የተጠና፣ የታረመ፣ የተስተካከለ ትውልድ ለመፍጠር ያስችለን ነበር።
በጠፋንበት ውስጥ እንዳንመላለስ ያግዘን ነበር። ሰኔን ጠልቸዋለሁ። ባይመጣ እሻለሁ። ለምን? እራስንመማር ላይ ስላልሆን። የሰው ግብር ክብር እና ሞገስ ሆኖ ስለማስተውል። በጓጎለ ጎዳና ተስፋችን ሲስተጓጎል ስለማስተውል።
እራስንመማር። ቢቻል - ቢኮንበት - ቢቀድም ጣዕማችን፣ ቃናችን፣ ትልማችን ተጣጥሞ ይሰክን ነበር። ሁሉ በእኩል መስመር ላይ መሆን ባይቻልም ማቀራረብ ይቻል ነበር።
ለአንዱ ትክክል በሙገሳ፣ ለሌላው ወንጀል በክትከታ። ግን አመክንዮው አንድ ነው። አመክንዮው አንድ ከሆነ ዳኛው መርህ፣ ዕውነት እንጂ የግለሰቦች ወይንም የተቋም ቀበሬታ እና እርቀት ሊወስነው ወይንም ሊዳኜው አይገባም።
የሰው ልጅ አፍ አንድ ነው። ይህ ዕውነት ነው። ሁለቱም የሰው ልጅ አፍ ሦስት ነው ቢሉ። ሁለቱም ያቀረብናቸውም ሆነ ያራቅናቸው ስህተተኞች ናቸው። ይህን እኔ ይፈራዋል። ስለዚህ ይፈርጃል፣ ዳኝነቱን ይሰባብረዋል።
ይህን ባለቤት አልባውን፣ ሁነኛ አልቦሹን በአማራ ፖለቲካ የሚቀርቡት እና የሚርቁት ሰብዕናወች፣ ተቋማት ላይ የዳኝነት አሰጣጡን ዝም ብዬ አያለሁኝ።
እንደ ድሮው መማገድ የለም። ግን እንዲህ ህሊናን የሚፈትሽ አመክንዮ አቅርቤ ህሊናችሁ እንዲዳኜው ሜዳውም ፈረሱም እላለሁኝ።
ምንጩን ሳስሰበው እራስንለመማር ፈጽሞ አስበነው አለማወቃችን ነው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
ሰብለ©ሕይወት
12/06/2022
እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ ጥሪ አለበት።
እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ይወለዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ