ልጥፎች

የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት።

  ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝማራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) • የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት። የእኔ ሃሳብ ከሌላው የተለዬ ነው። በጦርነቱም፤ ጦርነቱን ለማስነሳት የነበሩ ቅድመ ጉዝጓዝ ሁኔታዎችን አስመልክቶም ለዬት ያሉ ሃሳብ ነው የነበረኝ። እራሱ አቶ ሴኩትሬ የማን ነበሩ የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። በኦነጋዊው ኦህዴድ ሰበር ሳይዋጡ እርጋታን ይጠይቅ ነበር ሁሉም ነገር። ከመቀደም ለመቅደም። ጦርነቱን አስመልክቶ ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ተለያይተናል። አንዳንዶቹ የኦህዴድ ጥጋብ ፕሮፓጋንዲስት እንድሆንም ጠይቀውኝ ነበር። ድፍረቱ ቢገርመኝም። በምን ታምር? በምን ቀመር ሥርጉተ ሥላሴ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቅራሪ ልቅላቂ ፕሮፖጋንዲስት እንድትሆን እንደታሰበ አሁንም ይገርመኛል። ወይ ልክን አለማወቅ። ይህም ሆኖ መዳን አለ ብለን „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ“ ሲባል እኮ ዕድሉን ሰጥተን አይተነዋል። የሆነ ሆኖ ከጦርነቱ ዋዜማ ጀምሮ ዞር ብላችሁ ፕሮፋዬሌ ላይ ብትበረብሩ ታገኙታላችሁ። ከጦርነት አመድ እና በቀል ብቻ ነው የሚተርፈው። በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም። የሰሜን ፖለቲካ ድቅትም ነው። በጦርነት በዓይኔ ያዬሁትን ሁሉ በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ከሁሉ በላይ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን ያመነ ጉም የዘገና ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ለውጩ ዓለም እኮ የአማራን ሊቃናት ፈጅተው አማራ ሥልጣን ሊገለብጥ ነበር ብለው ሪፖርት አድርገዋል። ለጎረቤት አገሮችም እንርዳችሁ ተብለን ተጠይቀን በቁጥጥር ሥር አውለናዋል አልናቸው ብለው ነግረውናል። ያን ጊዜ እኮ አማራ ክልል ላይ ቀዝቃዛ ጦርነት ነበር ያካሄዱት። በብስጭት ባህርዳር ውድም እንድትል ሁ

ጎዳናዬ ሥርነቀል ለውጥ ነው።

ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝማራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) • የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት። የእኔ ሃሳብ ከሌላው የተለዬ ነው። በጦርነቱም፤ ጦርነቱን ለማስነሳት የነበሩ ቅድመ ጉዝጓዝ ሁኔታዎችን አስመልክቶም ለዬት ያሉ ሃሳብ ነው የነበረኝ። እራሱ አቶ ሴኩትሬ የማን ነበሩ የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። በኦነጋዊው ኦህዴድ ሰበር ሳይዋጡ እርጋታን ይጠይቅ ነበር ሁሉም ነገር። ከመቀደም ለመቅደም። ጦርነቱን አስመልክቶ ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ተለያይተናል። አንዳንዶቹ የኦህዴድ ጥጋብ ፕሮፓጋንዲስት እንድሆንም ጠይቀውኝ ነበር። ድፍረቱ ቢገርመኝም። በምን ታምር? በምን ቀመር ሥርጉተ ሥላሴ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቅራሪ ልቅላቂ ፕሮፖጋንዲስት እንድትሆን እንደታሰበ አሁንም ይገርመኛል። ወይ ልክን አለማወቅ። ይህም ሆኖ መዳን አለ ብለን „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ“ ሲባል እኮ ዕድሉን ሰጥተን አይተነዋል። የሆነ ሆኖ ከጦርነቱ ዋዜማ ጀምሮ ዞር ብላችሁ ፕሮፋዬሌ ላይ ብትበረብሩ ታገኙታላችሁ። ከጦርነት አመድ እና በቀል ብቻ ነው የሚተርፈው። በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም። የሰሜን ፖለቲካ ድቅትም ነው። በጦርነት በዓይኔ ያዬሁትን ሁሉ በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ከሁሉ በላይ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን ያመነ ጉም የዘገና ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ለውጩ ዓለም እኮ የአማራን ሊቃናት ፈጅተው አማራ ሥልጣን ሊገለብጥ ነበር ብለው ሪፖርት አድርገዋል። ለጎረቤት አገሮችም እንርዳችሁ ተብለን ተጠይቀን በቁጥጥር ሥር አውለናዋል አልናቸው ብለው ነግረውናል። ያን ጊዜ እኮ አማራ ክልል ላይ ቀዝቃዛ ጦርነት ነበር ያካሄዱት። በብስጭት ባህርዳር ውድም እንድትል ሁሉ

ነገረ ኢትዮጵያ። ልጆቻችን በኦነጉ ማህበረ በበኮሃራም የታፈኑት፣

  ነገረ ኢትዮጵያ። ልጆቻችን በኦነጉ ማህበረ በበኮሃራም የታፈኑት፣ የታገቱት በታህሳስ ነው አሸባሪው ኮሮናም በዚህው ወር እንደከቸቼ ይነገራል። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። አሁን ደግሞ ኮሮና ኢትዮጵያ ገባ በተባለ ሰሞናት አቶ ታዬ ደንዳኣ አዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ብለዋል። አቅጣጫ ቀያሽ ይመስላል። ቀጣይ ነገርን እንጠብቅ ዘንድ። አቶ ታዬ ጨካኙ ኦነግን የጭካኔው ጥግ ገልፀዋል። አስገድዶ የሰውን ልጅ የራሱን አካል እንዲበላ ስለማድረግ ሳይቀር። ሎቱ ስብኃት። ለምድራችን ቅጣቱ ቢመጣ ይህን ስታስቡት እራስን ይፈትናል። ከተፈጥሮ ውጪ የሴቶችም፣ የተባዕቶችም መደፈር፣ ተገድሎ መቃጠል፣ ድብዛቸውን ማጥፋት በሌሎች በኦሮምያ ቦታወችም ቄሮ በሚያስነሳው ቁጣ የባጁ ቢሆንም በራሳቸው አንደበት ምስክርነቱ መሰጠቱ የባሰ የእነዛ ዓለም ደጁን የዘጋባቸው የአማራ ህዝብ ተስፋዎች የደንቢደሎ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ህይወት ቀጣይነት እጅግ አሰጋኝ። በተለይ አምኒስት ኢንተርናሽናል የአዳማ ሥርዕዎ መንግሥት ሁኔታውን ከገለፀ በኋላ እንዲያውቀው ተደርጎ ያን ዘሎ ለሌሎች ሰባዕዊ ረገጣዎች አትኩሮት ሲሰጥ ፈጣሪ ተስፋውን የተስፋዬ ጠበቃ ካለው ድርጅት ሲያጣ እንዴት አይቆጣ? ከሰሜን የሚነሳ ንፋስ ሁልጊዜም ለዓለም አስጊ ነው ይላል የቅዱሳኑ ትንቢት። ከዚህ ጋር አያይዤ የማነሳው ዓለም የታደመበት ቦይንግም ፈተና ላይ የወደቀበት የመጋቢት 1 ቀን 2011 ዓም የዕንባ ቀንም ይታሰብ። ያን ጊዜ በብሎጌ ላይ እዮር ተከፍቷል እና አብይወለማ አመድ ነስንሰው ሱባኤ ይግቡ እንደ እምነታቸው፣ የጥሞና ጊዜ ይኑራቸው እነሱ ከመጡ ጀምሮ የሚታዬው የሰማይም የምድርም ቁጣ የተለዬ ነው ብዬ ፅፌም ነበር። እነሱም በሴራቸው ቀጠሉ ዕንባውም ቀጠለ ሰማያዊውም ቁጣ ጠንክሮ ሉላዊ ሆኖ ቀጠለ። ፈራሁኝ። ፈራሁኝ። ያስፈራኝ የአቶ

የቤርሙዳ ትርያንግል የገመና አንግል።

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)     የቤርሙዳ ትርያንግል የገመና አንግል። የማግስት አራሙቻ የገዳይ ማህበር ስልቻ መቃብር ቆፋሪነት ብቻ። ማህበረ ደራጎን በፍርሰት በውድቀት ዝምንምን። የዘመን ቅርሻ የንቅለት ዋሻ የድንጋይ ዘመን ግርሻ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22/03/2021 12/11 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ። የሞት ነጋሪት ታንቡር የሚነቀልበት ዕለት ናፈቀኝ።

የዋይታ አለቃ

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)     የዋይታ አለቃ ክብሩ ወላቃ። የኡኡታ ማህንዲስ ግርድስ የዕብለት ፍሩንድስ። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 22/03/2021 12/02 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ። ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

አገር በጨካኞች ታፍና አገር በጠላት እጅ ወድቃ

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)       አገር በጠላት እጅ ወድቃ   ቃ ብሎ በደረቀ አመራር ተደቅታ በድብልቅልቅ ተሰልቃ ደቃ! አገር በጨካኞች ታፍና ተቀምታ ታምቃ መፈናፈኛ አጥታ በዋይታ ተደፍታ ህምታ! አገር በወራሪ ተቁላልታ በዴሞግራፊ ተንቃቅታ በመደፈር ተብቃቅታ ህቅታ! አገር በፋሽት ተሰቅዛ ኤሉሄን ተናዛ ውርዴትን አርግዛ በክህደት ተገርዛ። እግዚኦ አለች አነባች ቋቷ ሞልቶ ኡኡታን ተመገበች ታፈነች፣ አምላኳን ተማፀነች ቀን ተዘርፎ ባዘነች ተንተከተከች። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 22/03/2021 11/57 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ። ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)     ዝንቅንቅ ድብልቅልቅ ቅይጥጥ ውጥንቅጥ። የሃሰት ቅጥቅጥ። ምንቅርቅር። ሙርቅርቅ ፍርክርክ ዝርጥርጥ የዕብለት ልቅልቅልቅ። ውልቅልቅውልቅልቅውልቅልቅ ፍጥርቅርቅ። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 22/03/2021 11/21 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ። ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

ገዳይ ባይቀጥፍ

  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) ገዳይ ባይዋሽ? ሽብሽብ። ገዳይ ባይቀጥፍ ጥልፍልፍ። ገዳይ ባያብል ዕምልምል። የዘመን ብል የፍዳ ገደላገደል የሉባ ግልገል ግምልምልግምልምልግምልምል - ልል። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 22/03/2021 11/21 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ። ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

መናኛ!

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትንቢተ ዕንባቆብ ፫ ቁጥር ፲፯) መናኛ! መጋኛ! የከንቱ ውዳሴ ዘበኛ። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 22/03/2021 11/14 ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ።  

"እኛ ባዕድ ነን"

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ "ሰባኪው ከንቱ፥ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ ይላል።" (መክብብ ፩ ቁጥር ፪)   "እኛ ባዕድ ነን" ሥንኙ በደንብ ከውስጥ ይነበብ። ኢትዮጵውያን ባዕዶች ነን። ስንት አዬነ አቃፊነት? ድንቄም? በፍርሰት፣ በንደት፣ በውድመት፣ በቀውስ፣ በቃጠሎ፣ በማተራመስ፣ በክህደት፣ በበቀለኝነት የበቀለ ትውልድ የለም። የከሰለ እንጂ። ኢትዮጵያን አከሰሏት፣ ከክብሯ አውርደው ሰቀዟት። አቅመ ቢስ ደካማ፣ ሰነፍም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22/03/2021 የመቃብር ሥፍራው አብይዝም ከሥሩ የሚነቀልበት ቅዱስ ዕለት ናፈቀኝ።

የሬሳ ሃሳብ ተሸካሚ

  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) "ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው" የጎንደር ብሂል ነው። የኦነጉ ማህበር የገለጠውን ሃቅ የዳጠው የክህደት ባቡር የኢትዮጵያ ፍርሰት ህልመኛ ነው። እራሱም ፍርስራሽ ራዕዩም ፍርስራሽ። የሬሳ ሃሳብ ተሸካሚ መቆሚያ ጀርባ የለውም። ላንቁሶ ነው። ዘመንህን ሁሉ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ቁማርተኛ ሆነህ አሁንም ለፍርስራሹ ራፊ ይሰጠኝ ጎንድ ተክለሃይማኖት ያሰኛል። እንደ ደግነት ማፈር የተሰደደባት አገር ናት ኢትዮጵ። መጥኒ ለእሷ። ጄኒራል ከማል ገልጁ የዘለቁትን ዕውነት ማን ይድፈረው? ማህበረ ፈሪ የደራጎን ፍርፋሪ! ገና ከዚህም በላይ ሰቆቃ ሱባኤ ላይ ናቸው የአብይዝም ኦርኬሰተር ባንድ። ማህከነ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22/03/2021 የትውልድ ዕዳ እንዲህ ከሜዳ!

ስድብ እና ተጋድሎ? ቦክስ እና ተጋድሎ? ጥላቻ እና ተጋድሎ?

ምስል
ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት ብራ ለራህብ የሚራራ። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)   ዛር ማዕዶተ ጠባቂ ነው። ህሊናዬ ያሰኜውን አጀንዳ የሚስተናገድበት። ያደሩ አጀንዳዎች፣ ሊቀድሙ የሚገባቸው አጀንዳዎች፣ ያልተቋጩ አጀንዳዎች ሁሉም ይለፍ አላቸው። ስድብ እና ተጋድሎ? ቦክስ እና ተጋድሎ? ጥላቻ እና ተጋድሎ? አድመኝነት እና ተጋድሎ? መረጋገም እና ተጋድሎ? ቂም እና ተጋድሎ? በቀልና ተጋድሎ? ተከላሎ እና ተጋድሎ? ተቧድኖ እና ተጋድሎ? የገመና ዝርዝር የተስፋ ግርር የራዕይ በረዷማ ግግር። የመቃብር ሥፍራውን አብይዝም፣ ማህበረ ጥፋቲዝምን ለመሞገት ሦስት ዓመት፣ ሦስት ጊዜ 365 × 3= ? ቀናት፣ በዛ ውስጥ ያሉ ሰዓታት፣ ደቂቃት ሁሉ ጭካኔ፣ ግፍ በደል ሲመረት ስለባጄ የግፍ ቅደም ተከተል መበራከት ይቸግረን ካልሆነ ይህን የመቃብር ሥፍራ በአመክንዮ ለመሞገት አቅም አለን። ትርፍ ነገር፣ መራከሱ አይበጅም። አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶችም አረም አምራች ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቧካሹን በህቡ አደራጅቶ ሲያፋልም ዘመን ጥሎን ሄዶ ድህነታችን አልበቃ ብሎ ሰው የሚበላ ሥርዓት ተፈጠረ። አብረን እንፈር። ከዚህ መማር ያልቻለ ሱፍ እና ከረባቱን፣ ሽብሽቦውን አውልቆ ከፖለቲካው ዓለም ሊሰናበት ይገባል። ዕድሜ ዘመን ሞገድን ተማምኖ እንኩሮ ሲያነኩር ከሚባጅ። እዬጠፋህ ጥፋትህን የሚያፋጥን ክፋ ተግባር መታመም ነው። መተላለፍም እንዲሁ። ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ ሥርዓተ ህግጋት ነው። እራስን ጥሶ አገራዊነት የለም። "ልብ አምላክ ዳዊት ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ ይላል።" ይህ ምስባክ እኛ እንድንበት ዘንድ ነው ለክርስትና አማንያን።

ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።

ምስል
ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።   "የደጋግ ሰወች ልጆች ስሙኝ በረድኤት ታደሱ፤ አበባ በምድረ በዳ ጠል እንዲያብብ እንደሱ አብቡ። (በረድኤት ታደሱ) ዬሽቶ ማዕዛ ደስ እንደሚያሰኝ ማዓዛ ትምህርታችሁ እንደዚያ ደስ የሚያሰኝ ይሁን።"   አሜን ብዬ ልጀምር።   ፍቅር ተፈጥሮው ጥልቅ ነው። የዛሬ 7 ዓመት አንድ የጀርመን አውሮፕላን አብራሪ ፈቅዶ ከተራራ ጋር አውሮፕላን አጋጭቶ እሱን ጨምሮ ወደ 150 ሰወች አጠፋ። ፈጀ። 15 ቀን CNN ዘገበው። ሬሳው ከአውሮፕላን ላይ ሰው ተንጠልጥሎ ለቀመው። እጅግ አሰቃቂ ነበር። መተኛት መመገብ አቃተኝ። ከዛ የሰውልጅ ክፋነትን ከምን አመጣው የሚል ምርምር ቤቴን ዘግቼ ሰራሁኝ። ከማህፀን እና ከአብራክ አለመሆኑን ተረዳሁ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ንፁህ ሆኖ መፈጠሩን ለራሴ ሙግት መልስ አገኜሁ። ሁለተኛ ደረጃ አቅጣጫዬ ዬሰው ልጅ ከአብራክም ከማህፀንም ክፋትን ካልተማረ ከዬት ዬሚለው ሆነ ፍለጋዬ። መልሱ ከቤተሰብ፤ ከማህበረሰብ ዬሚል ሆነ። ለምን ዬሚለውን ሦስተኛው ጉዞዬ አንድ ጭብጥን ሸለመኝ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ሙሉ ሆኖ ሲኖር አንገቱ ተቆርጦ። ማዘዣ ጣቢያ አልባ። መኖር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተር ዓልባ። ፕላኔታችን አሳሰበችኝ። ነገ አስጨነቀኝ። ምክንያቱ ቀላል ግን ትኩረት ያላገኜ። ለክፋ ነገር ማርከሻ አልተሰራለትም። ክፋ ነገር ካለ ዬሚመክት ዬደግነት ትምህርት ቤት ሊኖር ይገባ ነበር። ያ ደግሞ ዬፍቅር ተፈጥር ካሪክለም ተሠርቶለት በመደበኛ ዬዓለም ዜጋ መማር አልቻለም። ዬፍቅር ተፈጥሮ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ፤ ኤክስፐርት፤ ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ፤ ሙዚዬሣ።ም፤ ሚዲያ፤ መጋዚን፤ ግሎባል ቀን፤ ዬመንገድ ትርዒት ዬለውም። ዓለም በዘመኗ በፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት ላይ አጀንዳ ቀርፃ ተወ

አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው።

ምስል
  አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም። #ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው። ስስት ሰፊ ትርጉም አለው። እኔ አሉታዊ ስስት ላይ ነው ማተኮር እምሻው። "ለመብል ሁሉ አትሰስት ላዬኽውም እህል ሁሉ አትሰስት፤ ብዙ መብላት ደዌ ይሆናልና ስስትም ጓታን ያበዛዋል እና አትሰስት፤ ስስት የገደላቸው ሰወች ብዙ ናቸው፤ መጥኖ ዬሚበላ ግንሰውነቱ ጤና ነው።"     ስስታም ዓይኑ ጠባብ ነው። ይቅበዘበዛል። ጎላ ብሎ በወጣው ላይ አንቴናውን ይዘረጋል። የእህል ስስት ለቁንጣን ይዳርጋል። የሥልጣን ስስት ደግሞ ለፋሺዝም። ስስት የህሊና ቀውስም ያስከትላል። ቀውሱ #ማናንሼ እለዋለሁኝ እኔው። የማንነት ቀውስ ያለበት ሰብዕና ውስጡ ሰላም የለውም። ይናደፋል። ይቦጭራል። ሁልጊዜ ግስላ፤ አራስ ነበር ነው። ሥልጣን ኖረውም አልኖረው ቅምጥ ፍላጎቱን ለማስቀጥል ሩጫው አጋጣሚውን በመጠቀም ይሆናል። አድብቶ ይጠብቃል። ብቅ ብሎ ይሰወራል። አረሳስቶም ጠቀራውን ያንዶለዱለዋል። እሳቱን ጫጭሮም ዞር ይላል። ገባ ወጣ ነው። ለምዱ እስቲገለጥ። አክ እስኪባል። መነገጃው ግን ያው የፈረደበት ኢትዮጵያዊነት ነው። እያከሰለ በምራቁ ቀለም ቀቢነት ያጎሳቁለዋል። እርግጥ ጠንቀኛውን ዬአንድ ለአንድ አጋበስባሽ ስስቱን አምቀው የያዙ ጊዜ ራዲዮሎጂ ሆኖ እስኪያጋልጣቸው ብዙ ማገዶ ይጠይቃል። ሰብዕናቸው #ግራጫ #በሲቃ ነው። አካሄዳቸው #ተርገብጋቢ እና #ገርበብ ያለ ነው። አልፎ አልፎ ፍንጭ ቢሰጡም ለሰከኑ ዬሰብዕና አጥኝወች ካልሆነ በስተቀር ተሎ ለማዬት ያስቸግራሉ። የሆነ ሆኖ አቅም፤ አቅል፤ ብቃት፤ ታሪክ ላለው ማህበረሰብ ስስታም ግለሰቦችም፤ ስስታም ተቋማትም የትውልድ ጠንቅ ናቸው። ካንፓቸው እና ካንፓሳቸው #ጥላቻ ነው። ምርታቸው ዲዲቲ ነው። ከሚጠሉት ዘለግ ብሎ የ

የመኖሬ ወይንም የህወቴ ፍልስፍና በጥቂቱ።

ምስል
ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ፣ እንዳልከዳህም“ (ምሳሌ 30 ቁጥር    • ዕፍታ። ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። • የመኖሬ ወይንም የህወቴ ፍልስፍና በጥቂቱ። የህይወት ፍኖተ ካርታ ልንለው እንችላለን። ህይወቴን እምመራበት በርካታ መርሆዎች አሉኝ። ዝርግነት አልወድም። ዝርግ ሰውም ክፍሌ አይደለም። ልሙጥነትም ተጠግቶኝ አያውቅም። ጠፍጣፋነትንም እጠዬፋለሁኝ። ውራጅ ሰብዕና የለኝም። ራሴን ተውሼም አልኖርኩም። ልብ እንዲገጠምልኝ አልፈቅድም፤ ምን እንዳለኝ፤ ምን እንደምችል፤ ምን እንደሚፈቀደልኝ፤ ምን ደግሞ እንደማይፈቀደልኝ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። በሚገባ። እራሴ ተቋም ነኝ። ዝንቅ ያልሆነ ወጥ አሻራም አለኝ። (1) መኖር ነፃነት ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። (2) ለነፃነቱ ደግሞ መታመን። (3) ለመታመኑ ተፈጥሯዊነት። (4) ለተፈጥሯዊነቱ ጥሩ አስተዳዳሪነት። (5) ለጥሩ አስተዳዳሪነቱ ጥሩ አድማጭነት። (6) ለጥሩ አድማጭነት ጥሩ ዕውቅና። (7) ለዕውቅናው ውስጥን ሳይሰስቱ ወይንም ሳይነፍጉ መስጠትን። ( መስጠትን በተሰጠው ልክ ሚዛኑን አስጠብቆ እራሰን ሳይሸሹ ወይንም ከራስ ጋር ድብብቆሽ ሳይጫወቱ። 1) በቅድሚያ ስለ ነፃነት። ነፃነት ነፃነትን ይፈልጋል። ለነፃነት ነፃነት መስጠት የባለቤቱ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ አድዋ ግሎባል የነፃነት ክስተት ነው። አድዋ የነፃነት ክስተት ሆኖ ግን ነፃነቱን ተቀምቶ በኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ዘንድሮ አስተውለናል። ስለዚህ የዓድዋ ነፃነት ለራሱ ነፃነት አልበቃም ማለት ነው። ስለምን? አድዋ ክስተት እንጂ ሰው ስላልሆነ። ስለዚህም አድዋ ነፃነቴ ያለ ሰብዕና