የሬሳ ሃሳብ ተሸካሚ

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
"ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው"
የጎንደር ብሂል ነው። የኦነጉ ማህበር የገለጠውን ሃቅ የዳጠው የክህደት ባቡር የኢትዮጵያ ፍርሰት ህልመኛ ነው።
እራሱም ፍርስራሽ ራዕዩም ፍርስራሽ።
የሬሳ ሃሳብ ተሸካሚ መቆሚያ ጀርባ የለውም። ላንቁሶ ነው። ዘመንህን ሁሉ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ቁማርተኛ ሆነህ አሁንም ለፍርስራሹ ራፊ ይሰጠኝ ጎንድ ተክለሃይማኖት ያሰኛል። እንደ ደግነት ማፈር የተሰደደባት አገር ናት ኢትዮጵ። መጥኒ ለእሷ።
ጄኒራል ከማል ገልጁ የዘለቁትን ዕውነት ማን ይድፈረው? ማህበረ ፈሪ የደራጎን ፍርፋሪ!
ገና ከዚህም በላይ ሰቆቃ ሱባኤ ላይ ናቸው የአብይዝም ኦርኬሰተር ባንድ። ማህከነ!
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/03/2021
የትውልድ ዕዳ እንዲህ ከሜዳ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።