አገር በጨካኞች ታፍና አገር በጠላት እጅ ወድቃ

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
 

 
 
አገር በጠላት እጅ ወድቃ
 
ቃ ብሎ በደረቀ አመራር ተደቅታ
በድብልቅልቅ ተሰልቃ
ደቃ!
አገር በጨካኞች ታፍና
ተቀምታ
ታምቃ
መፈናፈኛ አጥታ
በዋይታ ተደፍታ
ህምታ!
አገር በወራሪ ተቁላልታ
በዴሞግራፊ ተንቃቅታ
በመደፈር ተብቃቅታ
ህቅታ!
አገር በፋሽት ተሰቅዛ
ኤሉሄን ተናዛ
ውርዴትን አርግዛ
በክህደት ተገርዛ።
እግዚኦ አለች አነባች
ቋቷ ሞልቶ ኡኡታን ተመገበች
ታፈነች፣
አምላኳን ተማፀነች
ቀን ተዘርፎ ባዘነች
ተንተከተከች።
ሥርጉተሥላሴ
SerguteSelassie
22/03/2021
11/57
ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ።
ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።