ስድብ እና ተጋድሎ? ቦክስ እና ተጋድሎ? ጥላቻ እና ተጋድሎ?

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ ብራ
በሰብለ ህይወት ብራ
ለራህብ የሚራራ።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)



 
ዛር ማዕዶተ ጠባቂ ነው። ህሊናዬ ያሰኜውን አጀንዳ የሚስተናገድበት። ያደሩ አጀንዳዎች፣ ሊቀድሙ የሚገባቸው አጀንዳዎች፣ ያልተቋጩ አጀንዳዎች ሁሉም ይለፍ አላቸው።
ስድብ እና ተጋድሎ?
ቦክስ እና ተጋድሎ?
ጥላቻ እና ተጋድሎ?
አድመኝነት እና ተጋድሎ?
መረጋገም እና ተጋድሎ?
ቂም እና ተጋድሎ?
በቀልና ተጋድሎ?
ተከላሎ እና ተጋድሎ?
ተቧድኖ እና ተጋድሎ?
የገመና ዝርዝር
የተስፋ ግርር
የራዕይ በረዷማ ግግር።
የመቃብር ሥፍራውን አብይዝም፣ ማህበረ ጥፋቲዝምን ለመሞገት ሦስት ዓመት፣ ሦስት ጊዜ 365 × 3= ? ቀናት፣ በዛ ውስጥ ያሉ ሰዓታት፣ ደቂቃት ሁሉ ጭካኔ፣ ግፍ በደል ሲመረት ስለባጄ የግፍ ቅደም ተከተል መበራከት ይቸግረን ካልሆነ ይህን የመቃብር ሥፍራ በአመክንዮ ለመሞገት አቅም አለን።
ትርፍ ነገር፣ መራከሱ አይበጅም። አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶችም አረም አምራች ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቧካሹን በህቡ አደራጅቶ ሲያፋልም ዘመን ጥሎን ሄዶ ድህነታችን አልበቃ ብሎ ሰው የሚበላ ሥርዓት ተፈጠረ። አብረን እንፈር።
ከዚህ መማር ያልቻለ ሱፍ እና ከረባቱን፣ ሽብሽቦውን አውልቆ ከፖለቲካው ዓለም ሊሰናበት ይገባል። ዕድሜ ዘመን ሞገድን ተማምኖ እንኩሮ ሲያነኩር ከሚባጅ።
እዬጠፋህ ጥፋትህን የሚያፋጥን ክፋ ተግባር መታመም ነው። መተላለፍም እንዲሁ። ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ ሥርዓተ ህግጋት ነው። እራስን ጥሶ አገራዊነት የለም።
"ልብ አምላክ ዳዊት ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ ይላል።"
ይህ ምስባክ እኛ እንድንበት ዘንድ ነው ለክርስትና አማንያን። እስልምናም ቢሆን ሰላምን ለሚያመጡ በጉነቶች መታጋት ጎዳናው ነው።
ዕምነት ካለን ፈጣሪ አክብሮ የፈጠረውን ሰውነት አክብረን ርኩስ ተግባሩን ግን በአመክንዮ መለመላውን ማስቀረት እንችላለን። እርቃኑን።
በአማርኛ ቋንቋ ለሚደረግ ሙግት ሙሉ አቅም አለን። ዘነዘና ለማስቀረት። ይህ እዬተቻለ ወርዶ መዘላለፍ ፈጣሪ የሚጠዬፋቸው እኩይ ህፃፆች ቤተኛ መሆን አያስፈልግም።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/03/2021
ጎዳናዬ ለሥርነቀል ለውጥ መታገል ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።