የቤርሙዳ ትርያንግል የገመና አንግል።

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
 

 
የቤርሙዳ ትርያንግል
የገመና አንግል።
የማግስት አራሙቻ
የገዳይ ማህበር ስልቻ
መቃብር ቆፋሪነት ብቻ።
ማህበረ ደራጎን
በፍርሰት በውድቀት ዝምንምን።
የዘመን ቅርሻ
የንቅለት ዋሻ
የድንጋይ ዘመን ግርሻ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/03/2021
12/11
ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ።
የሞት ነጋሪት ታንቡር የሚነቀልበት ዕለት ናፈቀኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።