ነገረ ኢትዮጵያ። ልጆቻችን በኦነጉ ማህበረ በበኮሃራም የታፈኑት፣
ነገረ ኢትዮጵያ።
ልጆቻችን በኦነጉ ማህበረ በበኮሃራም የታፈኑት፣ የታገቱት በታህሳስ ነው አሸባሪው ኮሮናም በዚህው ወር እንደከቸቼ ይነገራል። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
አሁን ደግሞ ኮሮና ኢትዮጵያ ገባ በተባለ ሰሞናት አቶ ታዬ ደንዳኣ አዲስ መረጃ ይዘው ብቅ ብለዋል። አቅጣጫ ቀያሽ ይመስላል። ቀጣይ ነገርን እንጠብቅ ዘንድ።
ከተፈጥሮ ውጪ የሴቶችም፣ የተባዕቶችም መደፈር፣ ተገድሎ መቃጠል፣ ድብዛቸውን ማጥፋት በሌሎች በኦሮምያ ቦታወችም ቄሮ በሚያስነሳው ቁጣ የባጁ ቢሆንም በራሳቸው አንደበት ምስክርነቱ መሰጠቱ የባሰ የእነዛ ዓለም ደጁን የዘጋባቸው የአማራ ህዝብ ተስፋዎች የደንቢደሎ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ህይወት ቀጣይነት እጅግ አሰጋኝ።
በተለይ አምኒስት ኢንተርናሽናል የአዳማ ሥርዕዎ መንግሥት ሁኔታውን ከገለፀ በኋላ እንዲያውቀው ተደርጎ ያን ዘሎ ለሌሎች ሰባዕዊ ረገጣዎች አትኩሮት ሲሰጥ ፈጣሪ ተስፋውን የተስፋዬ ጠበቃ ካለው ድርጅት ሲያጣ እንዴት አይቆጣ? ከሰሜን የሚነሳ ንፋስ ሁልጊዜም ለዓለም አስጊ ነው ይላል የቅዱሳኑ ትንቢት። ከዚህ ጋር አያይዤ የማነሳው ዓለም የታደመበት ቦይንግም ፈተና ላይ የወደቀበት የመጋቢት 1 ቀን 2011 ዓም የዕንባ ቀንም ይታሰብ።
ያን ጊዜ በብሎጌ ላይ እዮር ተከፍቷል እና አብይወለማ አመድ ነስንሰው ሱባኤ ይግቡ እንደ እምነታቸው፣ የጥሞና ጊዜ ይኑራቸው እነሱ ከመጡ ጀምሮ የሚታዬው የሰማይም የምድርም ቁጣ የተለዬ ነው ብዬ ፅፌም ነበር። እነሱም በሴራቸው ቀጠሉ ዕንባውም ቀጠለ ሰማያዊውም ቁጣ ጠንክሮ ሉላዊ ሆኖ ቀጠለ።
ፈራሁኝ።
ፈራሁኝ። ያስፈራኝ የአቶ ታዬ ደንዳኣ ሪፖርት እና የሰማዩ ቁጣ መገናኜት ነው። እስቲ ልብ ብለን እናስተውለው። ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጣሪ ፍጥረቶች ላይ ሲወርድ የባጀው መከራና፣ አይዟችሁ የሚል ሙሴ የማጣቱ ሁኔት። ተጠያቂነትም ኃላፊነትም የሚወስድ ጠፍቶ እንዴት ማላገጫ፣ እንዴት መሳለቂያ ሆኖ በቤተ መንግሥት እንደባጀ።
ይባስ ብሎ በደሉ ድልዳል ያገኝ ዘንድ ሰላም ባጣች አገር የሰላም አባት የዓለም ተሸላሚነት በእዮር አደባባይ ሲመዘን ምን ይባላል።
ሁለት ዓመት ሙሉ ከመጋቢት እስከ መጋቢት ኢትዮጵያ ከ100 ቀናቱ ውጪ ዕንባ ያላስተናገድንበት ሰዓት አልነበረም። የሚገርመው ዕንባውን የሚያዳምጥ ሁነኛ ማግኜት አልተቻለም ነበር።
ቢገኝም በሽንጥ እና በሸፍጥ ገብተው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ያዳፍኑት ነበር። ከእሳቸው ጋር ያለው መንፈስ እዮር የሚቀበለው ነበር ብዬ አላስብም። የፈጣሪ ማመስገኛ ቦታዎች እንደ ሹግ እዬነደዱ። በተቃራኒው መንፈስ የመወዳጀት እና ትልምን በማን አለብኝነት የማሳካት ሂደትን ነው እኔ ያስተዋልኩት።
የሚገርመው ይህ ሁላ መከራ እዬነደደ በዳዩ ተጠያቂ ሳይሆን ተበዳዩ ተጨማሪ ቅጣት አለበት እስአሁን ድረስ። የቀደሙት የዕንባችን አድማጮች ሁሉ ሁሉንም ኖቤል ጋረደቸው። ዛሬስ?
ሁሉም በጋራ የዕንባ ቤተኛ ሆነ። እከሌ ተከሌ ሳይባል። እዮር የዕንባን ጠብታ የሚያዳምጥ አንድ ነፍስ ሲያገኝ ለዛ ነፍስ ሲል ምህረትን ይልካል። ግን አልሆነም። አሁን ተያይዞ ማልቀስ ሆነ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እናስተውል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ