አስክኑት፣ አረጋጉት ቢያንስ ኢትዮጵያ ለምተነፍሰው ጋራ ሸንተረሩ፣ ወንዝ እና ተራራው።

 

አስክኑት፣ አረጋጉት ቢያንስ ኢትዮጵያ ለምተነፍሰው ጋራ ሸንተረሩ፣ ወንዝ እና ተራራው።
 
 

የእኔ አዱኛወች ርህርህናችሁ ቁሞ አስተማረኝ። ስለእኛ የለጠፍኩት ነበር። ከሺህ በላይ ሼር አገኜሁኝ። በእኔ ሥራ ያልተለመደ ነው። ዕውነት አጋፋሪ ሊጋባ እና የፕሮቶኮል ሹም የላትም እና።
በጥሞና ለማዬት ውስጣችሁን ራዲዮሎጂ አግኝቻለሁኝ። ስፍስፍ ስንዱ መሆናችሁን። ፌስቡክን ባገኜው ለመንፈሱ የወርቅ ሃብል አስርለት በነበረ። ይህን ዕድል መሪ፣ ሙሴ፣ የአይዟችሁ አንበል እንፈጥርበት ዘንድ ብልህነትን ገትሮ የሞገተ አሰስመንት ነው።
የተዋህዶን ፃድቅ ዬመለያዬ አናት አድርጌ እናት አገራቸውን ኢትዮጵያ ማተባቸው ያደረጉ ሁሉ ይደግፋኛል።
በተዋህዶ ፈተና ዓውዱን ለቀው ዬውስጥ መሻታችን እንፈፅም ዘንድ ብሩካን የቤታችን፣ ብሩካን የእልፍኛችን የእስልምና፣ የፕሮቴስታንት፣ የዋቄፈታ፣ የማርክሲስቶች ቤተሰቦቻችን ታላቅ ተጋድሎ በአደብ ፈፀሙ።
ትናንት እንኳን ለሮመዳን ፆም አደረሳችሁ ብዬ የክቡር ጭምትነት ቀንዲልን የዶር ሙፍትሂን ምስል አስቀመጥኩኝ። አይቸው የማላውቀው የተዋህዶ ልጅ ሚኒሊካውያን ላይክ አድርጎት አገኜሁኝ። ፌቡ የጀመርኩ ዕለት ያዬሁት ትናት ውስጡን አገኜሁት።
መስከን ምን ያህል እንደሚያስፈልገን ተማርኩበት። በዕለታዊ አጀንዳ አንባክን። ቂም፣ በቀል፣ ፋክክር፣ እልህ፣ ተበቃይነት፣ ጥላቻ ሲጋልቡ ፈረሰኛ ላለመሆን ልጓም እንሁን።
ብዙ ደክመናል። በአንድም በሌላ የልባቸውን መሻት ያገኙ ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ተስፋችን የት ነህ ብዬ ስመረምር ዜሮ ላይ ነኝ ብሎ በትህትና መለሰለኝ። ተግ እንበል። ባዶ እጅነታችን እንቀበል። ተሸንፈናል። ትውልድን ከብክነት ታሪክን ከእርዛት አላዳነም።
ምን ያህል እንደ ተጓዝኩ አላውቀውም።
ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም።
አለማወቄን ስጠይቀው፣ አለማወቁን ገለፀልኝ።
ተስፋን እጠብቃለሁኝ።
ተስፋ መፀሐፌ የመጨረሻ ገፄ ላይ ዬተፃፈ ነው።
ተስፋን ለማግኜት ምን እናድርግ? የጀመርኩት ስምንተኛው ምዕራፌ የአትኩሮት አቅጣጫ ነው። ተግ እንበል ርግብ በሩ ነው። ቦኩሱ ይቁም።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።