#መካነ #ነገሥት #ግምጃ #ቤት #ማርያም

 

እቴጌዋ እና ፀጋዋ። ጠረነ ህወኃት ይህ እንደሚያንገሸግሻቸው አውቃለሁኝ። ንጡኃን ተጋሩ ግን ክብራቸው ነው። በህወሃት ፖለቲካ የተነደፋ ቅድመወችም ጎንደር ሲነሳ ፀጉራቸው ይቆማል። ክብሩ በልቅና፤ ጽድቁ በልዕልና ግን የምዕት ዬተፈጥሮ ማሾ ነው።
ከአቶ እዮኤል ተገኜ
_____________ጎንደር______________
አኩፋዳ ፕሮጀክት
 


 
"አጼ ፋሲል ካሳነጿቸው አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስትሆን። ከዚያው ከፋሲል ግቢ ውስጥ በስተምዕራብ አቅጣጫ ትገኛለች። ፋሲል ግንብን ሊጎበኝ የሄደ ሰው ከዚያው ያገኛታል። ከቀድሞ ጀምሮ ስመ ጥር ሊቃውንት የተማሩባት ናት። በውስጧ የመጻሕፍተ ሐዲሳትና የመጻሕፍተ ሊቃውንት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት አለ። ደርቡሽ ወደ ጎንደር በመጣ ጊዜ ወንበሬን/ጉባኤየን ፈትቼ አልሸሽም በማለት ሰማዕትነትን የተቀበሉት መምህር ወልደ አብ ወልደ ሚካኤል (የኔታ ወልደ ሚካኤል) የነበሩበት ጉባኤ ቤት ነው። ጎንደር ካሉ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤቶች አንዱ የሚገኘው መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን ነው። ደቀመዛሙርቱ ብዙ ዓይን ያላቸው፣ የዓለምን ሁኔታ የተረዱ፣ በሁለንተናዊ እውቀት የተራቀቁ ይሆኑ ዘንድ መጻሕፍት ያስፈልጋቸዋል። ለዚህ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን "አኩፋዳ ፕሮጀክት" የሚል መርሐ ግብር ቀርጾ መጻሕፍትን ከበጎ አድራጊ ምእመናን እያሰባሰበ ይገኛል። ስለዚህ መንፈሳዊ መጻሕፍትን፣ የታሪክ መጻሕፍትን፣ የሥነ-ልቡና መጻሕፍትን፣ ሳይንሳዊ መጻሕፍትን ____ ወዘተ ማምጣት ትችላላችሁ። በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ መጻሕፍት ቢሆኑም አምጧቸው። አንብባችሁት የተቀመጠ መጻሕፍት ካለ ትውልድ የሚቀርጹ መምህራን እንዲያነቡት ለጉባኤ ቤት ይስጡ።
ጎንደር ፒያሳ መስቀል አደባባይ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን አኩፋዳ ፕሮጀክት ብሎ መጻሕፍትን እያሰባሰበ ይገኛል። ከዚያ የፈለጉትን መጻሕፍት ለጉባኤ ቤቱ ይስጡ።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።