ኢዜማ + አብን = ዬቤርሙዳ ትርያንግል የአብይዝም የመቃብር ስፍራ ውህደት

 

አፍንጫህን ላስ አቶ ሂደት። ወዮ አማራ። ዕቃ ዕቃ አንዳትጫወት። መራራ ነው ግን ይጣፋል። ሌላ 12993 ዬልጆች ዬተስፋ እገታስ? አጀንዳ ሆኖ አያውቅም።
30 ኦነጋውያን ያለ ተወዳዳሪ ለቀጣይ ግራጆሺን ተወስኖላቸዋል። ህንፃው ግን ብቻውን ተገትሯል። ትግል ከዚህ ይኚ።ጀመር እንደማለት።
"ዬለመደ ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ"? ተፈቀደላችሁ አንድ ላይ ሆናችሁ አቅም ዬቅን አማራ ሰብስቡና የሞጋሳ ዳግሚያ ተንሳኤ ይሆን ተባላችሁ? መቼ ነው ወደ ዲሲ ብቅ ዬምትሉት? ወደ አውሮፓስ?? ለነገሩ ታናሽ እና ታላቅ ትመስላላችሁ ውስጣችሁን አህዱ፣ ክለቱ፣ ሰለስቱ እያልኩ ሳሰናዳው።
ከለፈቃድ ትውር የለም እና። ትርታችሁ በዶር አብይ መዳፍ ነው። ይልቅ አምላካችሁ ዶር አብይ አህመድ ጅል፣ ጅላጅል፣ ጅልአንፎ ያሏችሁን ጠጡት። ለግርባው ብአዴን ቢሆንም ዬተደማሪን ፍርሰት ያወጁበት ነው።
ከአምስት ዓመት ትንቢት በኋላ????
ኢዜማ + አብን = ዬቤርሙዳ ትርያንግል የአብይዝም የመቃብር ስፍራ ውህደት ይባል ጥምረት፣ ጥምረት ይባል ህብረት፣ ህብረት ይባል ዘመን መጣን መጣን እያሉን ነው።
በዚህ ሁስጥ ትጉኃኑን የኢዜማውን አቶ ዳንኤል ሽበሽን አይጨምርም። መደናበሩ ምክንያቱ ሁለት ነው።
1) የኦህዴድ እና የህወሃት ፍጥምጥም።
ይህን አስቀድሞ አስቦ ተንብዮ በቁጥብ መራመድ አለመቻል ከፖለቲካ ሳይንቲስትነት ምህንድስና #ያለሙጣል
2) ዬተዋህዶ ዊዝደም አስደነገጣችሁ፣ አስበረገጋችሁ። አራግፋችሁን ተራገፋችሁ። አሁን ደግሞ መልሰን በስል ገብተን እናራግፍ ነው። እሷ አጀንዳችሁ ሁና አታውቅም። ስትቀጠቀጥ ባሊህ የለም። ቋሚ ትምህርት ቤት ግን ከፍታላችሁአለች። ኢትዮጵያን ያበጀችው በዚህ ጥበብ ነው። ውርውር ያሉ ነገሮች ነበሩ ወደ ጎጆ ሳይመለስ ነኩቷል። በጅምላ ማሰብ፣ በጅምላ ጉዞ የለም።
በነጠረ ጉዞ ቂምን፣ ምቀኝነትን፣ ጥላቻን የተጠዬፈ ግን ለምርኮኝነት የማያረገርግ ትውልድ ላይ እንሠራለን። በአገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ የአማራን ህዝም አቅም ጥላሸት ዬቀባችሁት። ከዚህ ተደርሷል። የሁሉም አስተዋፆዖ አለበት።
ቅኖችን እናስረዳለን። እናስተምራለን። አማራ ሁልጊዜ ከተጎዱት ጋር መቆሙ ተፈጥሮው ነው። ይህን ተፃራችሁ፣ ግን አቅሙን ዘርፋችሁ ዛሬ ጋር ተገናኝታችኋል።
ለነገ ግን አይሠራም። በተፈጠራችሁበት ተልዕኮ ልክ መቀጠሉ ያዋጣል። አሁን ደግሞ ይህን አጀንዳ አንጠልጥለው የማይሰለቻቸው ወጤ አቶ ግርማ ካሳ ብቅ እንደሚሉ አስባለሁኝ። ደመቅ ሲል፣ ውጥን ብቅ ሲል ጉልህ ሆኖ መውጣት። ከዛ ሁሉንም አቻኩሎ መና።
ሚዲያ አላችሁ። አያያዙን ብወድለትም ከጥዋቱ ፔጁ ላይ ሄጄ ልኩን ነግሬዋለሁኝ። ሳብስክራይብ አድርጌዋለሁ ሁለት ቦታ ላይ። ሞገደኛው ስላለበት።
አልጫ ፖለቲካ ስለማልወድ። ተደማጭ ሚዲያ ሆኖ ጀምሮታል። በቋሚነት እማዳምጠው ሚዲያ ነው። የጋራ ውይይቱ ላይ ተክሌሻ ሞገደኛው ካለው። የሃሳብ ነፃነት በሱ የመኖር ህይወት ቁልጭ ብሎ ስለሚታዬኝ። ያው እንደሚታወቀው ሞገደኛው እና እኔ የረጅም ጊዜ የሙግት ማህበርተኞች ነን። ግን በፍቅር።
እንዲህ ዓይነት ትውልድ ነው የምሻው። የመሳዩም የተክሌሻም ሞጋች ነበርኩኝ። መሳዩ እና ማህበርተኞች ፁሁፌን ከሆም ፔጅ ላይ የማስነሳት አቅም ነበረው። የጎንደር ማህበር መኳንንቶችም። እኔም ምህረት የለኝም። የትውልዱ ብክነት ያንገበግበኛል። እኔም አለሁበት። የሆነ ሆኖ እኔ ለታገልኩለት፣ ዕውነት፣ እኔ ለታገልኩለት መርኽ ዛሬም ቆሜለሁ እያለን ነው አቶ ወንድም መሳዩ። አዲስ ፓርቲም እያሟሟቀ ነው። ያምርበታል ማሟሟቅ።
ድሪቶ ተሸኩሙልኝ ግን #ይሸቀነጠራል። ዬተጎዳን፣ ህይወታችን ምስቅልቅሉ የወጣ ዘግተን የምንኖር በግሎባል ደረጃ እንድንገለል ደባ የተሠራብን፣ ድርጅታቸው ግንቦት 7 አሳራችን ያበላን ምንዱባን አለን።
እስኪ የትኛው ሚዲያ ደፍሮ የሥርጉተ ሥላሴን ሥም ያነሳል??? አለ? ዬጎንደሬ ዬአማራ ነን ሚዲያ ነን ባዮችን ይጨምራል። ለእነሱ ፌስታ የመሠረት ድንጋይ የታነፀው በዛ ወጀብ ውስጥ ነው። ስለ ድል አጥቢያው የአብን ቁንጮ ትዕቢት እና ርጋታ ግጭትና ፍጭት ነገ ይናገረው።
ለመሆኑ ሥርጉተን የመሰለ ባተሌ ማሳደዱን መቼ ይሆን እምታቆሙት ማህበረ ግንቦት? አቤቱታ ነው። አንቃችሁ የያዛችሁት አቅም ሁሉ እኔን መሰሎች መቼ ነው ከእስር ይፍታህ ዬምትሉት የምትለቁት።
ለነገሩ ተደማሪ ለማድረግም ተግታችኋል። አልሆነም። አለቃ እንዲኖረኝ አልሻም።። በአሻራዬ ውስጥ አዛዥም ናዛዥም። ሲዊዝ ያለው ቋሚ አሻራ የሥርጉትሻ ነው። ካላችሁ ትነግሩኛላችሁ።
#ለቀጠሮ ፓርቲወች።
#ይቅርታው#ፀፀቱ #ጥሞናው እራስን ማረሙ ለመቼ ተቀጠረ ይሆን? #ዬቀጠሮ ፓርቲወች፣ ዕለታዊ እያልኩ በደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ሙገቴ እና ጥረታችን በስልብ የገዱ ቲም አፈር መጋጡ ቢያሳዝነኝም ዘመን እንዲያስተምራችሁ፣ ዬጥሞና ጊዜ እንዲሰጣችሁ ፈጣሪን እማፀነዋለሁኝ።
ቂም፣ በቀል፣ ጥላቻ አልፈጠረብኝም። ያ ቢሆን ህወሃትን በታገልኩበት ረቂቅ አቅም እናንተንም መመከት አቅቶኝ አይምሰላችሁ።
ሌላው ግን ከሳሽም ተከሳሽም ሊኖር አይገባም። አለ ዬተባለውን ሁሉ አጤ ዘመን አሳይቶኛል። ተመስገን። ምክንያት ሁሉም በአፀደቀው ሰነድ ውስጥ ኑሮ ስለማያውቅ። እናንተን ነጥሎ መከትከት አይገባም ብዬ አስባለሁኝ። የተሻለ ዬለም እና። አስርጋችሁ አስገብታችሁ መበተኑን መሐንዲስ እንደሆናችሁ አውቃለሁኝ።
ማናችሁም የሥልጣን ማማ በወጣችሁ ቁጥር እኩል ያን መከራ ተቀብሎ ያነገሳችሁን አማራ አላያችሁም፣ እኩል ትሪት አላደረጋችሁም፣ መንገዱም አናርኪ እና ብልጣ ብልጥ ነበር። ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው አማራ ቢሆን ለማስገበር እንጂ ጠርቶ አቅሙን ክብሩን ለማስጠበቅ ሳይሆን ተጎንብሶ ለመሄድ ነው።
ኢትዮጵያ አምላክ አላት። እኔም አምላክ አለኝ። አማራም አምላክ አለው። ቁጭ ብዬ ሁሉን እያዬሁኝ ነው። መኖሬን ባልፈቅደውም መኖሬን ግን ዛሬ ላይ ወድጀዋለሁ። ተመስገን።
አዲስ ሥም እንጠብቃለን። የኢትዮጵያ ሞሰብ፣ ዬኢትዮጵያ ማዕዶት፣ የኢትዮጵያ እያላችሁ ስትዋህዱ፣ ስትበተኑ፣ ስትካሰሱ በመሃል ስትታሰሩ ስታደክሙን ደግሞ እንገናኛል።
ምክሬ እንደ አፈጣጠራችሁ ሁናችሁ እራሳችሁን ችላችሁ ብትቀጥሉ ጥሩ ነው። ለምርጫ ኮረጆ አትትበስበሱ። እኔ #ዬፖለቲካ #ፓርቲ #ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም ባይ ነኝ። ተፈጥሮዋ አይፈቅድም።
ስለዚህ ሰባዕዊነት፣ ተፈጥሯዊነት የሚመራው ቲም ከፖለቲካ ድርጅቶች ውጭ የሆነ #አጽናኝ ቲም ይፈጠር ነው ዕይታዬ። እምተጋውም በዛ ዘርፍ ነው።
ለዚህ ነው ጎጎት ሲፈጠር ዝም ያልኩት። ከእንግዲህ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ዓርማ ከብራናዬ አትለጠፍም። ግዴታው ካልተወጣው ኦነጋዊው ብልጽግና በስተቀር።
በመጨረሻ ያሻችሁን ማድረግ፣ መሆንም መብታችሁ ነው። ግን አቅም ያለበትን እያሳደዳችሁ ማህበራዊ ኑሯችን አትምሱት። በቃ! እምትባሉት እናንተም ናችሁ።
ህወሃት እኔን አላሰደደኝም። እኔን ያሳደደ በሙሉ አቅሙ የተበቀለኝ፣ ያን ሁሉ አቅም የቀበረው ግን ግንቦት 7 ነው። ሙኒኮችን ጀርመን ኖርወዮችን አይመለከትም። እነሱ ነፍሶቼ ናቸው።
ዬአማራ ትውልዱ ደግሞ በአዲስ ትብብር ውስጥ በሚፈጠር ፓርቲ ገብቶ የእሳት እራት እንዳይሆን እመክራለሁኝ። በቃው መገበር። ማንዘርዘሪያ ይኑር። ሳሙኤል አወቀ ሺብሬ ደስአለኝ ምን ተጠቀሙ???
ዶር አብይ ህወሃትን ከሥር ለቀዋል። ቻሉት። እነ መንትዮሽ ሚር። ግንቦት 7 መቼ ነው ሥርጉትሻን በነፃ ዬምትለቋት?
ደህና ሁኑ። አልመለስበትም። ተሟግተናል። ዛሬ ሙጣጭ ላይ ትገኛላችሁ። ብትሰሙኝ ኑሮ ከክብራችሁ ማማ ላይ ትሆኑ ነበር። ከሙግት በፊት ሙያዊ እገዛዬን ያለመሳሰት ለግሻለሁ፣ አሻም ስትሉ እስከ ሚዲያችሁ ሞግቻለሁ። ተቋሞቻችሁ የሉም። በሽርፍራፊ ካልሆነ። ሥርጉትሻ ግን አሻራዋን አንሰራፍታ አለች እንደ አለች።
ፀረ ስሜን፣ ፀረ አማራ እሳቤያችሁ ተዚህ አደረሰ። ዶር አብይ የተደገፋትም ይህን ስለሚያሟሉ ነበር። ዛሬ ስሜናዊው ጨካኙ ህወሃት ትቢያውን አራግፎ ተነስቷል።
በአጭር ጊዜ አገር መምራት የሚያስችለውን ፖለቲካዊ አቅሙን ያሟላል። በቀለኛው ድርጅት የትንሳኤው ለት እናንተን አያድርገኝ።
ቤተ መንግሥት እስኪለቅ ሞግቸዋለሁ ህወሃትን፣ ሲለቅ ግን አንድ ቀን ምንም አላልኩትም። እንዲያውም አጽናኙ ነበርኩ። ጦርነቱንም ተው ብያለሁ ግራ ቀኙ። ጉዳቱንም እኩል ዘግቤያለሁኝ።
እጅግ የከፋኝ በበቀል ሰክሮ አማራ እና አፋርን ሲወር ነበር። ከዋና ደጋፊ ዬህወሃት ባላባቶች እምለዬው ለህወሃት አቅም መቼውንም አለማዋጣቴ ነው። ለኦነግም። ወደፊትም። ምክንያት ፀረ አማራ እና ፀረ ተዋህዶ ስለሆነ ቅንጣት አቅም አይሰጡም።
ይህም ሆኖ ቂም፣ በቀል ጥላቻ ዬለብኝም። ሁሉም ከሴት ማህፀን ከእናት ተፈጥሯል እና። እናቶች ያሳዝኑኛል። ክፋአቸውን አያሰማኝ። አሜን።
የመግለጫ ኳኳቴ ቆሞ መሪነት እና አዛኝነት፣ የህዝብን ፍቅር አሽቀንጥሮ ለራስ ማደር፣ ብቅ ያሉ አቅሞችን ማሳደድ ጆኖሳይድ መሆኑን አጥኑት። ዬንስኃ ጊዜም ውሰዱ።
ከእኔ ራስ ውረዱ። እዚህ ላለው ወኪላችሁም በተለይ ግንቦቶች መመሪያ ስጡ። ተሰቃይቻለሁኝ። ተንገርግቤያለሁ። ተቀቅያለሁኝ። ተሳቅቄያለሁኝ። ሥርጉተማ ታዬች። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ጉደኞች እኮ ናችሁ በነፃ ህዝብ ለማገልገል እንኳን የማትፈቅዱ??? በራሴ ወጪ ለምደክመው? ኧረ ጡር ፍሩ። ልሳናችሁንም የፈንድ ካፒቴናችሁን ካፒቴናችሁን ፈጣሪ አሳይቶኛል። ተመስገን ነው። ህይወቱ ግን ደህና ይሁን። ተባብራችሁ አሳደዳችሁኝ።
እምሰራው በፋክት ላይ ነው። የተጋሁለት መርህ ከጣሰ ከእኔ ቤት ምህረት የለም። የዛሬ 15 ዓመት ጀምሮ የተጋሁለት ባለ ተስፋት ሰብዕና ዛሬ የለም። በመንፈሴም። ለምን? ላም እረኛ ምን አለን ስላላዳመጠ። እንዲህ ናት ሥርጉትሻ፣
ዬቲም አንባቸው መሰዋት ፌስታው አተረፈ ወይንስ አከሰረ??? ለፍኖተ ካርታ አዘጋጆች የቀረበ ጥያቄ ነው።
አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/93/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።