ባለቤት የሌላቸው አመክንዮዎች፣ ማህረሰቦች፣ ቅርስ ውርሶች፣ ባህል ወጎች፣ ልማድ ትሩፋቶች የሚዳሰሱበት ዕለት ነው። ለዛሬ ሁለት ባለቤት አልቦሾቹን ላንሳ፣ ከአመክንዮ

 

ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
ማዕዶተ ይግቡ፣
 

 
ባለቤት የሌላቸው አመክንዮዎች፣ ማህረሰቦች፣ ቅርስ ውርሶች፣ ባህል ወጎች፣ ልማድ ትሩፋቶች የሚዳሰሱበት ዕለት ነው። ለዛሬ ሁለት ባለቤት አልቦሾቹን ላንሳ፣ ከአመክንዮ "አቅምን" ከማህበረሰብ "አማራን"
ፌስቡክ እንደ ጀመርኩ ሁሉም አቅም የሚሻው ከአማራ ህዝብ ነው። የአማራ ልጅ ፊደል መቁጠር ካለበት አቅሙን ቆጥቦ እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት ሊማር ይገባዋል ብዬ ነበር።
አማራ በነፍስ ወከፍ ይሁን በማህበረሰብ ደረጃ የሚከዳ ነውና። እሱ ያደራጃል የሌላ ሲሳይ ይሆናል። ስለሆነም በገፍ በሚሰጠው አቅሙ ልክ ዕውቅና ማግኜቱ ዘመን ይመልሰው። ቅንነቱ በዛ ማገዶነቱም።
ብቻ ተቋም ይፈጠር፣ ድርጅት ይዋቀር፣ ሚዲያ ይቋቋም አማራ የደም ሥር ነው። ኢትዮጵያን ላስቀደመ ሁሉ እስከ ቀራንዮ ነው ጭምቱ አማራ። በሚገበረው ልክ አማራ ዋቢ አግኝቷል ወይ ሲባል? እጬጌው ሂደት ይመለስው።
ብቻ፣ አወን ብቻ አማራ አሳዛኝ ፍጡር ነው። ይካዳል። መታመኑ በበዛ ሁኔታ ይጠቀጠቃል፣ መማገዱ ከብሄራዊ አልፎ ተረፎ ሉላዊ በሆነ ሁኔታ ይወገዛል።
ነገረ አማራ መጨረሻው ይናፍቀኛል። አቅሙን ለአቅሙ በሥርዓት አደራጅቶ የሚመግብበት፣ በሚያገባውም በማያገባውም ጉዳይ ዘውታውን በቅጡ የሚያስተዳድርበት፣ በማገዶነቱ ልክ መኖሩ የሚረጋገጥበትን ቀን ይናፍቀኛል።
ከውስጤ አዝናለሁ። በእያንዳንዱ የአማራ ልጅ ያለው ቅንነት፣ መታመን፣ ንፁህ የእኛነት ፍቅራዊነት ተነፍጎ ሲንገላታ፣ ሲወድቅ ሲነሳ፣ ጭራሽ ድራሹ እንዲጠፋ እንዲህ በሁሉም ሁኔታ ተስፋ ሲርቀው አዝናለሁ።
እንሰሳውን ሳይቀር በሬ ሆይ! አያ ሆይ! እያለ እያባበለ የሚጠራው፣ የመቻቻሉ ንጉሥ አማራ የዛሬ፣ የዛሬ 25/30/40 ዓመት መኖሩ በቀጣይነት ምን ይሆን?
የትስ ይሆን መግቢያ ቀዳዳው? እስራኤሎች ልባም መሪ አግኝተው በተሰጣቸው መክሊት ልክ ተከብረው ይኖራሉ። አሳዛኙ አማራ ያሳዝነኛል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/03/2021
ጎዳናዬ ሰብዓዊነት፣ ተፈጥሯዊነት ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።