"ጎንደር" የትንቢቷ ከተማ በታዴ የማመይ ልጅ

 

አሜን ብያለሁኝ። እንደ ሰው ምቀኛ ዬማያጣት ካስማዋ ባዕቴ እትዬ ጎንደሪና የተባች በምግባር ገናና።
ቅንነትን አጥጥታ እንደ ወተት ስላሳደገችኝ ዝቅ ብዬ የፀጋ
ስግደት እሰግድላታለሁኝ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 

 
ከደጉ ዘሃበሻ ያገኜሁት ነው።
"ጎንደር" የትንቢቷ ከተማ
በታዴ የማመይ ልጅ
"ለ251 ዓመት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነገስታት መቀመጫ ሁና በኩራት መርታለች 28 ንጉሶች ነግሰውባታል 18ቱ ሀያል ነበሩ 10ሩ በጣም ሀያልና አስፈሪና አይደፈሬ ነበሩ ንጉሶቻችን እስከ ሱዳን ኑቢያ በጀብድ ገዝተዋል ነጮቹ ያን የስልጣኔ የጥበብ አሻራ ዘመን The Glorious Gondarine Period ,The Luxury Life Of Gondarians ይሉታል።
ጎንደር የአፍሪካ መናገሻ( The Camelot Of Africa) African Naples, African Paris
እያሉ ያንቆለጳጵሷት የነበረች የከተሞች እናት ነች
የጎንደር ስያሜ የተገኘው "ጉንደ ሀገር" ከሚለው የግዕዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም
የሀገር መሰረት
የሀገር ግንድ
የሀገር ቁንጮ
የሀገር ቀንድ
የሀገር ምሰሶ
የሀገር ዳራ
የሀገር አውራ ታላቅ ምድር ማለት ነው።
ሌላኛው ደግሞ ጎን እደር ከሚል የወይኔ እና ሰይኔ እርቅ ጋር ተያይዞ በወንድምህ ጎን እደር ከሚል የተወሰደ ነው ይቺ ታሪካዊት የትንቢት ከተማ የተቆረቆረችው በ1624 በአለም ሰገድ ፋሲል ( አለም የሰገደለት ማለት ነው ) ሲሆን ንጉሶች ጎ ትነግስ መናገሻህ ጎ የሚል ህልም ያዩ ነበር በጎ የሚጀምር ቦታ ላይ ከነገሱ ንግስናቸው ይፀናልና በዚህ ትንቢት ምክንያት ገናናው ፋሲል ፈልጎ አፈላልጎ በሚያድነው ጎሽ ምክንያት አገኛት እና መቀመጫው አደረጋት በጥቁር አፍሪካ ምድር የአፍሪካ መናገሻይቱ ውብ ምድር የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል ።
ጎንደር የኢትዮጵያ ዋና ከተማ መሆኗ ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣው ጥበብና ስልጣኔ ገናናነት ጀግንነት የግንባታ ቴክኖሎጅ ብቻ አልነበረም ይልቁንስ ነገስታት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በመዞር ይገዙ ነበር እንጅ ከተማ አይመሰርቱም ነበር ጎንደር ከተመሰረተች በኋላ ግን ይሄ የመዘዋወር ባህል ቀርቶ በቋሚ ከተማ መምራት ተጀመረ።
የከተሞች እናት ጎንደር ዋናዋ የንግድ ማዕከል በመሆንም አገልግላለች ወደ ቀይ ባህርና ሱዳን የሚደረገው ንግድ ማዕከል ሁና ቆይታለች ።
ጎንደር እኮ …
የሰርፀ ድንግል ፣ የሱስንዮስ ፣ የፋሲል፣ የአዕላፍ ሰገድ፣ የአድያም ሰገድ የእያሱ…የበካፋ ፣ የምንትዋብ ፣ የተዋበች… የቴዎድሮስ እና የገብርዬ… ብቻ ሀገር አይደለችም። የጦረኛው አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ …የግራኝ አህመድም ሀገር ነች ። ከአስር አመት በላይ ጠላቶቼ የሚላቸውን ነገስታት እያሳደደ ህልሙን ለማሳካት የተንከራተተባት …በኋላም በጀግንነት እየተፋለመ የወደቀባት ምድር ናት #ጎንደር!!
ማን ያውቃል? …ግራኝ አህመድ አሸንፎ ቢሆን ከፋሲል ቀድሞ መቀመጫው ያደርጋት ይሆን ነበር እኮ… ግራኝ እና ገላውዲዮስ… ሁለቱ ተፋላሚዎች የየራሳቸውን የተለያዩ ርዕዮተ ዓለሞች ተሸክመው መንግስታቸውን ለማፅናት ሲሉ ጎንደር ላይ ተፋልመዋል። ሽምብራ ኩሬ …ሸዋ ላይ ፣ የገላውድዮስን አባት የአፄ ልብነ ድንግልን ጦር ያሸነፈው ጦረኛው ኻሊፌቱ ግራኝ አህመድ…
ጎንደር በጌምድር ፣ በለሳ ውስጥ ልዩ ስሟ "ወይና ደጋ" ከተባለች ቦታ ላይ ሲሰዋ የጎንደርን አፈር መቅመሱ እርግጥ ነው። ከአፋር እና ከሱማሌ በርሃዎች የፈለቀው በርኸኛው ግራኝ… በራስ ደጀን እና በጉና ተራሮች በተከበበችው …ከባለ ጣና ሃይቋ ምድር፣ "ከወይና ደጋዋ" ጎንደር ላይ አሸለቧልና አፋራዊያኑ ስለጎንደር ያገባቸዋል።
አፋር ተወልዶ አፋር ያደገው… ግራኝ ለህልሙ የተፋለመባትን ጎንደርን… አፋሩ እና ሱማሌው ሳይቀር "ሙቼ ነው ምወዳት" ቢል አልተሳሳተም። ጎንደር የግራኝም ሀገር ናት። የበረኸኞቹ፣ የሙስሊሞቹ ኢትዮጵያዊያን ደም እና የደገኞቹ የክርስቲያኖቹ ኢትዮጵያዊያን ደም የተጋመደባትን ምድር… ናት፣
#ጎንደር ... እናስ እርሷን "ሙተን ነው ምንወዳ " ቢባል ለክብሯ ይገባታል እንጂ አያንሳትም
# የጁዎቹ እነ ራስ አሊ በፍቅሯ ተነድፈው አፈሯን የቀመሱላት… ጎንደር። እነ አፄ ዮሃንስ ለሃያሉ ፍቅሯ አንገታቸውን የሰጡላት… ምድር ጎንደር… መወደድ ሲያንሳት ነው። "ሙቼ ነው ምወዳት " ሲያንሳት ነው!!
ፊት አውራሪ ገብርዬን ፣የታንጉትን ባል፣ "ቀኘ" ን፣…መቅደላ ስር "አሮጌ" ላይ …"ከጓዴ እና ከንጉሴ ከመይሳው በፊት እኔን ያርገኝ" ብሎ የተሰዋውን … ታማኙን ባለማተቡን… የሰጠችንን ጎንደርን… እኔስ "ሙቼ ነው ምወዳት" !!
መይሳው ካሳ… የልጅነት ህልሙን ታላቋን ኢትዮጵያ ያለመባትን ፣ ከጠላቶቹ ጋር ተዋድቆ እና ድል ነስቶ የንጉሰ ነገስትነቱን አክሊል ስሜን ደረስጌ ማርያም ላይ የዳፋባትን …የእናት የአባቱን ሀገር …ጎንደርን! …"ሙቼ ነው ምወዳት "… ተብሎ ቢዘፈንላት ቅር የሚለው አለ?
አፄ ምንይልክ… ገና በጋሜነቱ በንጉሳዊ ቤተሰብ አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገባትን ምድር… ጎንደርን! የልጅነት ሚስቱን የአፄ ቴዎድሮስን ልጅ የሰጠችውን ጎንደርን! … ኋላ ደግሞ ሩቅ አሳቢዎን እቴጌ ጣይቱ ብርሀን ዘ ኢትዮጵያን ፣ ያበቀለችለትን… ጎንደርን …ከምር "ሙቼ ነው ምወዳት!! "
…መቅደላ ላይ፣ እጅ መስጠትን እምቢ ብሎ ሽጉጡን ጠጥቶ የተሰዋባት የክንደ ብርቱው የመይሳው ልጅ ልዑሉ ወደ እንግሊዝ ሀገር የሚደረግን የግዞት ጉዞ ጭንቅላቷ አልቀበል ብሎ መንገድ ላይ የሞተችው የእቴጌ ጥሩወርቅ ልጅ … ትንሹ ልዑል ዓለማየሁ…ከእንግሊዝ እስከ ህንድ ናፍቆቷን ተሸክሞ በሰው ሀገር ተንከራቶ ...ተንከራቶ… በስስት የሞተባትን …ጎንደርን… ሙቼ ነው ምወዳት!!
አሁን በእኛ በዚህ ዘመን… "የኦሮሞ ደም የእኔም ነው︎!" ያለችውን፣ በኩራት ደረቷን ነፍታ "ስብሓት ሆይ አንተና የማፍያው ቡድንህ ህወሓት ትፈርሳላችሁ እንጅ ኢትዮጵያ አትፈርስም" ያለችውን… የእብሪተኞችን ውድቀት ያፋጠነችውን …ቅስም ሰባሪዋን… የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽን… ሀገር… ኢትዮጵያዊቷን ጎንደርን… "ሙቼ ነው ምወድሽ" … ብንላት ማን ይከለክለናል?
ጎንደር ለዘመናት ከጀግንነት ማማ ዝቅ ብላ አታውቅም
እንደውም እንደጉዳይ በአንድ ቀን ጀግና ትወልዳለች እንጂ !
ከጎንደርነት ሥፍሩ ትንሽም እንኳን ጎድሎ አያውቅም ! እንደውም ክብሩም፣ጀግንነቱም፣ዕውቀቱም ጥበቡም ሁሉ ነገሩ እያደር ይጠነክራል! ምክንያቱም ጎንደር _ጎንደር ነውና!
ስብሃት ለጎንደር ከብሮ ለሚያስከብረው!
ስብሃት ለጎንደር ጀግንነት ባሕርይው ለሆነው!
ክብርና ሞገስ ለጎንደር እውቀትና ጥበብ አርማ ላደረግው!
ስብሃት ለጎንደር ኢትዮጵያን ለሚታደገው!
እውነት ...አላችኋሁ
ጎንደርን አለማመስገን ንፉግነት ነው፡፡"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።