ስውር መንግሥት፤ ግርዶሽ መንግሥት ሁለት መንትዮሽን መስመር ላይ አገናኝቷል።

 

ስውር መንግሥት፤ ግርዶሽ መንግሥት ሁለት መንትዮሽን መስመር ላይ አገናኝቷል። መንታ ከረባት። ጊዜ ራዲዮ ነው።
#ኢትዮጵያ በፕሮፖጋንዳ አልተሠራችም። #በዊዝደም እንጂ።
 

 
አማራም መኖሩን ያኖረው በቅንነት ወተት ቢሆንም ብልህነቱን #አስጥቶ አለመሆኑ ይታወቅ።
"አቤቱ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።"
(መዝሙር ፻፳፱)
ይህ ዕሳቤ ዬጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን የማዳን #መለከት ነው። ተረኝነት እያሉ ፋሺዝምን በምርጫ ዕውቅና ያሰጡ ሰብዕናወች ዛሬ ከህወሃት እና ከኦህዴድ ቀለበት ማግሥት ብቅ ብለዋል። በአካሄድ ቢለያዩም። በአፈፃፀም ረቀቅ ቢልም።
የጉራጁ እና የሽራፊው ኢህዴግ የነፍስ አባት አንባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሰሞኑን ሠርግ እና መልስ ናቸው። ሁለት አንደበተ ርትዑ የኢህአዲግ ቧንቧወች ቀን ሰጥቷቸዋል። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። ቲም ደመቀወገዱ ነፍሱን አይማረው። አሜንወአሜን።
ዘመኑ በፖለቲካ ቋንቋ መግለጽ ዳገቱ ነበር ለአምስት ዓመቱ የፖለቲካ የኢትዮጵያ የነፍስ ውጪ ግቢ አሳር። " ተረኝነት " ቀድሞ ያለው እከሌ ነው የሚልም ዕድምታ አዳምጣለሁኝ። ቁምነገር ሆኖ ግድፈት። አዳነ? አስነሳ? ወይንስ ፈጠፈጠን? ብሎ መጠዬቅ የአባት ነው። እኔ አገር ቤት ያሉት እራሱ "ተረኝነት" ዬሚለውን እንዲጠቀሙበት አልሻም። መስዋዕትነት መቀነስ የአመራር ጥበብ ነውና።
ውጭ የሚኖረው ግን አሉታዊ ዴሞግራፊ ገና በጥዋቱ በአደባባይ ይፋ ዬተደረገባት አገር #ፋሺዝም መርህ ልዕልት ኢትዮጵያ እንደገባች እንደምን አይቀበሉም? ዬሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጽነሰቱም ውድቀቱም አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። ወረራ፤ መስፋፋት፤ መዋጥ እና መጫን። በዛ ላይ የገዳ አስተምህሮ ተቀምሞበታል። የሚገርመኝ ጥሞና መውሰድ የአባት ሳለ አሁንም "ተረኝነት" የሚሉትን ሳዳምጥ ይገርመኛል።
ይህ አስተኝ ጉዞ ሚሊዮኖችን አሰልፎ ትግሉን አፈዘዘው። ልዝ እንጨት ወይ አይነድ፤ ወይ አያነድ ጢስ ብቻ፤ ማጨናበስ። ይህ አልበቃ ብሎ አሁን ጠቅላያችን የሚበጠብጡት እዛው ውስጥ የተፈጠሩ አንጃወች ናቸው፤ ሌላው የማዳኛ ጨለማ ጉድጓድ ሲኦላዊ ጉዞ ሆኗል። ጠቅላይ ሚር፤ ፕሬዚዳንት፤ የስለላ ተቋማት የበላይ ጠባቂ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፤ የፀጥታው ምክር ቤት እጬጌ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የቬርሙዳው ትርያንግል በህይወት እያሉ ስውሩም ግልጡም ጡጧቸው ገድለዋቸዋል። ከአቅማቸው የወጣ አንጃ ተፈጥሯል እያሉ። ስንት የእብደት የወፈፌ ፖለቲካ እንደ አለ አስታውሱት።
ወርደው ቀበሌ መንደር እግር ኳስ ዬሚጫወቱ መሪ እያሉ። ዬገጠር ከተማወችን ከንቲባ ሽም ሽረት የሚወስኑ ቁንጥንጥ እያሉ። ይህ ጉዞ ዬተራገፈው የደጋፊ አቅሙ ከሞት ተነስቶ በገፍ ይታደል እና ሬሳውን እናንግሥ ነው ጉዞው። ምን አልባት አንድ ሞደሬተር የብአዴን እና የአብን ቡድን ያው የፖለቲካው ቴርሞ ሜትር ያለው ዲሲ ነው ይላክለት ይሆናል። ለግርባው ብአዴን መግለጫ አወጣ ተብሎ አገር ምድሩ ተጥለቅልቆ ነበር። የአብይዝም የአቅም መሰብሰቢያ ብዬው ነበር። አሁን ደግሞ ሌላ ዜማ ተለቋል ስውር መንግሥት። #ልፋጭ እሳቤ፤ #ስጦ ግንዛቤ።
#ለስምንተኛ ጊዜ ልፃፈው።
ሞገድ የሚባል የማፍያ ጋዜጣ ልበወለድ ወጣት እያለሁ አንብቤው ነበር። ለምሳሌ ፊውታውራሪ ሞገድ ጋዜጣ 20 ሚሊዮን ዶላር ያወጣ እና #ሽብር ይገዛል። ሽብሩ የሚፈፀምበት ታዋቂ ሙዚዬም፤ ታዋቂ ዓለም ዓቀፍ ተቋም ላይ ነው። ጋዜጣው ተሰናድቶ ይቆያል። ሽብሩ በተፈፀመበት #ቅፅበት ጋዜጣው ይለቀቃል። 50 ሚሊዮን ዶላር ይሸጣል።
ይህን ሰላዩ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ መፀሐፋን አንበበው እንደ #ጥንቸል ሙከራ በሚደረግባት አገራችን ላይ እዬፈፀሙት ነው። ሽፍታውም፤፥ቀውሰኛውም ካፒቴኑ ጠቅላይ ሚር አብይ ናቸው። ሽብር ያደራጃሉ አፈፃፀሙ እና #ሰበሩ እኩል ይለቀቃል። ይህን #ባይረስ ተሸከሙልን ነው ዬስውር መንግሥት አቀንቃኞች የቀጣዩ የአቅም አውዳሚ፤ ዬአቅም አዛይ እና በታኝ ስንክሳር። አይሰቡት። ደቋል። ቀብሩ ላይ እንዳይገኙ ሙያ በልብ ተመስጥሮበታል።
ሌላው ቅኑ ኢትዮጵያዊ፤ ሩህሩሁ ኢትዮጵያዊ ደግሞ መከራው ጋር ቁጭ ብሎ ይነጋገር። ለኢትዮጵያ መከራ ፕሮፖጋንዲስት፤ ተንታኝ አያስፈልገውም። እራሱ ረግረጉ በደጁ እዬተገኜ ቤት ለዕንባ ላይ ስላለ። 100 ቀን ሳይሞላ ደቡብ ላይ ተጀምሮ አዲስ አበባ ላይ እርጋ ተብሏል የጥድፊያው የሙሴ የዋይታ ግጥግጦሽ ሰኔ 16/2010 - ሀምሌ19/2010=
#የቁርጭምጭሚት አጥመ - ርስት ፖለቲካ።
ከዚህ ቀደምም ጽፌዋለሁኝ። ህወሃትን ለማሳጣት በሱማሌ የነበረው ግጭት፤ እና አዲስ አበባ ዴሞግራፊ ቅድመ መሰናዶ፤ ዬሬቻ ጭፍጨፋ ሰሞኑን ከፋይሌ አውጥቼ ስመረምረው ነበር። ያ በእነማን እንደተቀነባበረ ዛሬ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ መንገዱን እናውቀዋለን አታክቱ ሲሉ እሰንሰማቸዋለን። ቀድሟል ወጀቡ ቀውስ አደራጅቶ መምራት እንደ ማለት።
የሆነ ሆኖ ሦስቱ ሰኔወች፤ ሦስት ጥቅምቶች፤፦አንዱ መስከረም የአዋሳው #የመጥፎ አጋጣሚ ሾተላይ ጥንስሱም የኮሶ ጠላውም ባለሙያ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ናቸው። በዛ ጭንቀት ውስጥ ነው ዬተመረጥን ትረካ ዬተወለደው። 98%። ያ እንዲሳካ 24 ሰዓት የታተሩት ከስኬት በኋላ ተቃዋሚ ሆነው ሲወጡ ለሰከንድ ሂደቱን ላጥናው ያለ ቅንጣት ሰብዕና ከደቂቅ እስከ ሊሂቅ አላዬሁም። ለይቶላቸው በግልጽ ለሚደግፋት ምስጋና ነው ያለነኝ። አላደከሙኝም።
ስውሮቹ ግን አሁን ይሰለስሉታል። በተለዬ ዬአማራ ሊቅ ሲወጣ እያደኑ አፈርድሜ ሲያስግጡቱ ባጅተው አሁን ደግሞ ጠቅላዩ ፃድቅ ነው፤ ኦህዴድ ብቻውን የሠራው የለም የሚል ባንድ አደራጅተው ኦርኬስተሩን እያስደለቁት ነው። በስንት ሲዲ እንደሚያሳትሙት እናያለን።
እረቂቁ ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ የገዳወኦዳ ሥርዕወ የጥድፊያ ሂደት የመውረስ፤ ዬመስፋፋት የመንፈስ ነቀላ እና ተከላ ለማሟላት አሁንም ይተጋሉ። እርሾው ደግሞ የአማራ አቅም ነው። ደጋፊውም ዘውድ ደፊውም። ይልቅ ከባለቤታቸው ዘዬ የወረሱትን ዶር አብይ ጅል፤ ጅላጅል፤ ጅልአንፎ መሆን ያሰኜው አብሮ መጪ ይበል። ሥርጉትሻን አይነካካትም። አቅም አይባክንም። ቅንጣት።
መያዣ፤ ማያያዣ አባይ፤ ደቡብ ሱዳን፤ ሰሜን ሱዳን ሉዓላዊነት ቀጣዩ የአሳቻ የአብይዝም የስውር ደጋፊወች ስልብ ጉዞ ይሆናል። ኢትዮጵያ በፕሮፖጋንዳ አልተሠራችም። በዊዝደም እንጂ። ልብ ከቋንጃ ላይ እንዳይሰካ አደራ እንላለን እኔ እና ሸበላዋ ብዕሬተብራና።
1) ዬትኛውም አካል የሚፈልገውን መደገፍ መብቱ ነው። በማጭበርበር ግን አይሆንም።
2) ዬአማራን ህዝብ እንመራለን ብላችሁ ገባሪ ያደረጋችሁትም ተለመኑን። የጉሮሮ አጥንት አትሁኑት። መስዋዕትነትን ሰርክ አትመግቡት።
3) በአማራ አቅም የከበራችሁ የአማራ ልጆች ለክብሩ ምንጭ ቁልፍ ጉዳይ ታገሉ። "ወልቃይት ብረሳሽ???"
4) በአማራ አቅም ዘረፋ እና የኮፒ ራይት ፍልሚያ መስዋዕትነቱን ያገዘፋችሁበት ዬአማራ ሊቃናት እና ሊሂቃን በአቅማችሁ ልክ ሁኑ።
5) መኖር የተቀማውን አማራ ብቅ ሲል እዬቀለባችሁ የምታስማግዱትም አደብ ይስጣችሁ።
6) ዬዜግነት ታጋዮች ምሽጋችሁ አማራ ብቻ አይሁን። ኢትዮጵያ ለአማራ ብቻ ፊርማ የተፈፀመባት አገር አይደለችም። አይደለም አገሬው ኢትዮጵያ የግሎባሉ፤ ከዚህም ባለፈ የሰማይ፤ የምድርም ዬዩንቨርስም የወል አጀንዳ ናት።
ከቁጥር አንድ እስከ ስድስት የተደረደሩት ትዕዛዝ አይደለም። ኧረ ምን በወጣኝ። እህታው ትህትናዊ ምልከታ። ምክንያት በዝምታ እማልፋቸው ጉዳዮች ከ20 ዓመት በላይ መኖሬን ገብሬ ላም እረኛ ምን አለ ስለ ተቀጠቀጠ ነው። ከእንግዲህ ስለ ግለሰብ ሰብዕና አልመሰክርም፤ ተነካ ብዬም አልሞግትም። ሰው ሚስጢር ነው። ሚስጢሩን የሚያውቀው ባለቤቱ ብቻ ነው። እኔ አውቄኃለሁ ብዬ መድከሜ ያሳዝነኛል። ላውቅ የሚገባኝ ዕውነት፤ መርኽ እና ፋክት ትውልድን እንዴት ሊያንፁ እንደሚችሉ ብቻ ነው።
እንቆቆ ታውቃላችሁ? አሳንጋላስ? ባህላዊ የኮሶ ህዋስ መፈወሻ ናቸው። አዘገጃጀታቸው ይለያያል እንደ ጉርሽጥ እና እንደ እንሶስላ።
የሆነ ሆኖ እንቆቆ እና አሳንጋላውን እንሆ። #ዜሮ #ላይ #ነን
*** ዜሮ ላይ ያለው****
1) መንፈሰ #ኢትዮጵያኒዝም
2) መንፈሰ አማራዊ ንቅናቄም።
///// ምን መደረግ አለበት???/////
አትቀመሽ ጎምዛዛ ነሽ፦
አትዋጭም መራራ ነሽ፤
ዕውነት ደፋር ካላገኜሽ
#ቃና የለሽ ትሆኛለሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ
* ዕርዕሱ ቃና የለሽ ነው። ለህትምት የበቃ ነው። ሥነ ፁሁፍ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ባህልና ስፖርት በሚያዘጋጀው ኮርስ ላይ እያለሁ የፃፍኩት ነው። የትኛው መፀሐፌ ላይ እንደሚገኝ ግን አላስታውሰውም።
ማህበረ አይዞን ሩህሩኃን ሆይ!
ቸር ዋሉልኝ። ቸር ሁኑልኝ። ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/03/2923
ኢትዮጵያ በፕሮፖጋንዳ መለከት አልተበጀችም። በዊዝደም እንጂ።
ጊዜ ራዲዮ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።