በታሪካችን ውስጥ እንገኛለን።
ይጠብቁን። ዛቻ አይደለም። ገዱን አምነን የሰጠነውን ሙሉ ክህሎት ምርኮኛ መሆኑን ብናውቅም በታሪካችን ልቅና ውስጥ ሆነን እናንተን ትዕቢተኞችን ያስተማረ ተግባር ፈጽመን ዊዝደም እናበራለን። በፍልስፍናችን #ተፈጥሯዊነት በቀና ጎዳናችን #ሰዋዊነት በልካችን ልክ ሆነን የዳዊትን በትረ ዓምድ ለመላ ዬኢትዮጵያ ህዝብ እኩል ያበራ ዘንድ ፈጣሪ አላህ ይረዳናል። ሮመዳን መሆኑን አይርሱት። በተናገሩት ውስጥ ቅኖቹ አገር ወዳዶቹ ጨዋቹ #የአማራ እስልምና እምነት ተካታዮችን የዳጠም፤ ዲስክርምኔሽን የፈፀመ ንግግር ስለመሆኑ ሊነገረወት ይገባል።
ብቻ አወን ብቻ ዬድቡሽት ትምክህቱ በላይኛው ኃይል ይደረመሳል። ሙት መሬት ላይ ያሉት ጉፋዓን ዜጎቻችን የዕንባ ዋነተኞች ሁሉ ችግርን፤ ዬብሶት ፖለቲካን አንበርክከው #ጠሐይ ይወጣል። የፓን አፍሪካኒስቷ መሪ የምትፈሯት ኢትዮጵያ አማራን ጨምራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አክብራ ቅዱሳን ዬሌሎች ኃይማኖት ነፃነታቸውን አስከብራ ትንሳኤዋ ይመጣል።
ሥርጉተ©ሥላሴ (ሰብለ©ህይወት) እባላለሁኝ። ከገበርዲን እና ከሱፍ ከረባት እንዲወጣ ዬኢትዮጵያ ፖለቲካ ዬተጋች እና ለስኬት ያበቃቻችሁ እህት ናት ይህን መልዕክት ዬላከችው። መልዕክቴ በአክብሮት እና በትህትና ይድረሰወት። ፆመ ሮማዳን አይተላለፋት። በወንጌል ንጉሥ ዳዊት ልብ አምላክ የሚባል ቅዱስ አባት ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ ይላል። ህግ የሰማይም የምድር ነው። ይህ ቦታ መሪነት ነው። ህግ ረጋጮች፤ ህግ ጠቅጣቂወችን መሸከሙ ግን ያሳዝነኛል። አፍላም ቢሆን።
ዝልግልግልጉ እና ዝርክርኩ ፖለቲካችሁ ያከትማል። ችግራችን ሁሉን ማዳን የሚያስችል ዊዝደም እንደ ቀደምቶች እንከተል ስለምንል ነው። ቅንቅን የበላው ግንድ ይገረደሳል። ህወሃትን ጫካ መልሶ ያስገባ አቅም አሁንም አለ። ቅንቅን ሆናችሁ እዬበላችሁ ላላችሁት ፊተኞች፤ #ትናንት አልነበራችሁም #ዛሬም የላችሁም ነገንም አትኖሩትም።
መኖር በህግ ውስጥ በጋህዱ እና በሰማዩ ዓለም ጭምር ነው።
ተሰዳችሁ ዝም እንላለን። ዬለገጣፎዋ ትዕቢተኛ እንደ ተሰደዱ ሰምቼ ነበር። ተሰዳችሁ መኖሪያ ፈቃድ ታገኛላችሁ። ዝም እምንለው ቤተሰብ ወላጅ እህት ወንድም ስለ አለ ነው። አማራ እንዲህ በርቀት ያስባል። " ከአማራ ጋር አትዋለዱ አትጋቡ አትገበያዩ" ያሉት አቶ በቀለ ገርባ አሜሪካ ስደተኝነት እንደጠዬቁ ተሰምቷል። አቅም ጠፍቶ አይደለም። ልጃቸው አለች። ስለ እነሱ እናስባለን። ትውልድ ለዛሬ ሳይሆን ለነገ በቂም፤ በበቀል፤ በጥላቻ እንዳያድግ መጣር ነውና ጥሪያችን። ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን፤ ጀግና አብዲሳ አጋ እና ሌሎችም በዚህ ቅዱስ መንፈስ ውስጥ ያለፋ ናቸው። አረም ዕሳቤ የጊዜ ጉዳይ ነው። ተነቅሎ ይወድቃል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
24/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
እንበርታ።
ከቂም ጋር ተጣሉ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ