ልጥፎች

ከማን የተማሩትን፨ የኦሮሞ ፖለቲካን ጎለጎታ እየላኩት ነው፨ "#ሸለፈታም።" የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አዛዥ ጠቅላይ ሚር #አብይ #አህመድ። "#ማበሳበስ። ስድ አደግ" ጄኒራል #ብርኃኑ #ጁላ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም። ሁለት ቁንጮወች ወደ ጅራትነት አሰኛቸው።

ምስል
  ከማን የተማሩትን፨ የኦሮሞ ፖለቲካን ጎለጎታ እየላኩት ነው፨ " #ሸለፈታም ።" የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አዛዥ ጠቅላይ ሚር #አብይ #አህመድ ። " #ማበሳበስ ። ስድ አደግ" ጄኒራል #ብርኃኑ #ጁላ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም። ሁለት ቁንጮወች ወደ ጅራትነት አሰኛቸው።   "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"     # በር እኔን ስለመግለጽ።   ፊልዴም አይደለም። የማይመለከተኝን ዘርፍ አልነካካውም። መከላከያን በሚመለከት ዝምታዬ ከመቃብር የሚከብደውም ለዛ ነው። ኢኮኖሚ ዘርፍንም ትውር እማልልበትም በዚህው ሎጅክ ነው። ሁሉም ዘርፍ ባለሙያ፤ ኤክስፐርት ፈላስፋም አለውና። #የማህበረ ኦነግ ካሪክለም ጠያፍ ቃላትን መዳፈር።   የማህበረ ኦነግ የአይዲኦሎጂ ካሪክለም ግን ይገርመኛል። ማህበረ ኦነግ በፖለቲካው ዘርፍ በብሄራዊ፤ በአህጉራችን በእማማ አፍሪካ፤ በምዕራብውያን እና በአውሮፓውያኑ እንደዚህ ዘመንም ከፎቅ የተፈጠፈጠበት ዘመን ያለ አይመስለኝም። በታሪኩ ኦነግ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥት #አራጦ እንዲመራ፤ በትረ ሥልጣኑም ያለ ከልካይ ተሰጥቶት በወርደ ጠባቡ ቁመናው ኢትዮጵያን መምራት ተስኖት በዚህ መልክ ወድቆ ማዬት ጊዜ ራዲዮሎጂነቱን አስመስክሯል።   ዛሬ ስለ አጤ ጊዜ ቅኔነትም ልከልለት። አወን! ጊዜ #ቅኔም ነው። አጤ ቅኔ ቅኔውን በተሰጠው ልክ እንዲህም ይዘርፈዋል። ለቅኔ ማህበረ ኦነግ ስለማይችሉት ሲዋጉት // ሲወጉትም በበታችነት ስሜት ሲናውዙም፤ ኮሽ ባለ ቁጥር ሲደነጋግጡ እዚህ ደርሰዋል። በሌሉበት ቦታ ሁሉ መልካሙን ነገር ሁሉ በፀርነት ፈርጀው ሲፈሩትም፤ ሲመነጥሩትም ኑረዋል። ታሪክ በቀደመ ህዝብ፤ አገርም በቀደም ህዝብ ዊዝደም ይሠራል።    ኢትዮጵያ አንጡራ ጠላቱ የሆነ

አይ No“ ልዩ አቅም ነው።

ምስል
  አይ No“ ልዩ አቅም ነው። ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Sselassie) 04.03.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ።) „ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሄር ምህረት የተናሳ ነው። ርህራሄው አያልቅምና።“ ሰቆቃው ኤርምያስ (ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፪) እስቲ ዛሬ ትንሽ ስለ «አይ» እናውጋ። ወግ ቢጤ።   ሁልጊዜ የሰው ልጅ ሃሳቡ ተቀባይነት ሲያገኝ እጅግ ደስተኛ እና ሳቂተኛ ይሆናል። „እሺ“ ከሁሉም በላይ የመልካም ነገር ማህጸን ነው እና። እንደ እኔ ዕይታ ደግሞ „አይ“ ማለትም ተወዳጅ ሰብዕና ነው። ብልጽግናው „በማዬት“ አድማጭነት ስለሚለካ። እንደዚህ ዓይነት ሰብዕና ፊት ለፊት ሲሞግተን ደስ ሊለን ይገባል። „እሺን“ ሆነ „ይሁንን“ ስንቀበል ደስ እንደሚለን ሁሉ „አይ“ „አይቻልም“ „አልተቀበልኩትም“ ስንባልም ከውስጣችን ደስ ሊለን ይገባል። ምክንያቱም „በአይሆንም“ ውስጥም ሌላ የአቅም ቅምጥ ሃብት አለና። አንደኛ የሰው ልጅ እንደ ፈጣሪ እራሱን ከሚያይበት ወንበር ዝቅ ብሎ ተፈጣሪ መሆኑን ያውቅበታል። የሰው ልጅ የአቅሙን፤ የመብቱን ጣሪያና ግድግዳ ማወቅ በቻለ ቁጥር የሰውነቱን የማስተዋል ፍሬ ነገር ያያል። በሌላ በኩል የ„አይ“ ቤተሰቦች መንፈስ „ከእሺ“ የበለጡና የተሻሉ ሲሆኑ፤ መሬት ላይ ሙሉ የሆነ ስብዕናን የተላበሱ መንፈሶች ጥሪታቸው እንዲሆን የማድረግ ባለ ልዩ አቅም ናቸው። ሰው ከቁሳዊ ነገሮች አምልኮት ጋር ባበደበት በዚህ ዘመን „አይን“ የሚደፍሩ የህሊና ዓይን ያላቸው ብቻ ናቸው። ምከንያቱም ጥልቅ የተፈጠሮ ሚስጢራት መገለጫዎች „ከማዬት“ ማዬት የተገኙ ናቸው እና። ምንም ነገር በምድር ላይ ግኝቱ „በማዬት“ ውስጥ የተፈጠረ ነው። „ማዬት“ ትልቅ ጸጋ ነው። „ማዬት“ ትልቅ ጸጋ የሚሆነው ከውስጥ በአትኩሮት ከተቀመመ ብቻ ነው። ከዚህም ባለፈ

ስክነት የሚጠይቁ አመክንዮወች አሉ ለአማራ ፖለቲካ። መርገብገብ አያስፈልግም። ችኮላም!

ምስል
  ስክነት የሚጠይቁ አመክንዮወች አሉ ለአማራ ፖለቲካ። መርገብገብ አያስፈልግም። ችኮላም! ትርትትሩ የኦነግ ፖለቲካ ሊያሸብረው ወይንም በቀውስ በጀት ሊያሰምጠው አይገባም። በስክነት፣ በመደማመጥ በለመደበት የዊዝደም ልቅና መራመድ ይጠይቃል። እርግጥ ነው መሪ የለውም። ነገር ግን ችግሩ በራሱ ጊዜ መሪ ይፈጥራል ጠብቁት። ብስጭት አያስፈልግም። የሚስፈልገው አይደለም የድምፅ ምቱን አዬሩን እራሱን ማድመጥ። አቅምን አላግባብ አለማባከን። በማይረቡ አቲካራዋች ጊዜን አለማጥፋት። አማራነትን መሰነቅ። ውስጥነትን በውስጥነት ማዋሃድ። መሆን በመሆን ማስተናበር። ከተራ ግርግር መውጣት። ለፈንጠዝያ ጊዜ አለመስጠት። በረጅሙ ማሰብ። ለዘለቄታ መሥራት። ለታሪካችን፣ ለትውፊታችን ቀናዕይ መሆን። "የቤትህ ቅናት በላኝ" ያለውን የንጉሥ ዳዊትን ቃለ ህይወት መመስጠር። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/12/2021 አማራ ሆይ! የደምህ ዋጋ ታሪክህን አሳልፈህ አለመስጠት ነው።        

እኔን አፈር ልብላላችሁ። ማቆሚያው ግን መቼ ነው?

ምስል
  አቶ ብዙአዬሁ እንደዘገቡት። ነፍስ ይማር። አሜን። የጎጃም አዴት #ወንድማማች ፋኖዎች ወራሪውን አንገት ላንገት ተናንቀው በክብር አርፈዋል!! ውለታችሁን አለብን!! ፋኖ አለነ ሃይሉ ፋኖ ይበልጣል ሃይሉ በሰላም እረፉ!! እኔን አፈር ልብላላችሁ። ማቆሚያው ግን መቼ ነው? ባለፈው አቶ እሸቱ እሰከ ልጃቸው። አሁን ወንድማማቾች። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/12/2021 ፈጣሪ ሆይ በቃችሁ በለን።    

#ኢትዮጵያዊነት የክት እና የዘወትር፣ የቤት እና የእዳሪ ልጅነት የለውም። እናት ላለውም ለሌለው ለእኔ ቢጤውም እኩል ናት።

ምስል
  #ኢትዮጵያዊነት የክት እና የዘወትር፣ የቤት እና የእዳሪ ልጅነት የለውም። እናት ላለውም ለሌለው ለእኔ ቢጤውም እኩል ናት። የሆነ ሆኖ ኦነጋዊው ኦህዴድ ፩ሚሊዮን ኃብታም ዲያስፖራ ኢትዮጵውያን የመደመርን መርኃ ግብር የፈቀዱ እንዲገቡ ወደ አገር ቤት ብሔራዊ ጥሪ አቀርቧል። ተቃውሞ የለኝም። በሰላም ገብተው የልባቸው ደርሶ በሰላም የእኔ ድንግል ትመልስልኝ። አሜን። ለእነኝህስ ማነው ተጠያቂው? ማነው ወደ ቤታችን፣ ወደ ባዕታችን እንመለስ ሲሉ የሚፈቅድላቸው እገዛ የሚያደርግላቸው። ጥያቄው ይህ ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/12/2021 ኢትዮጵያ የሁሉም እናት ናት የድኃውም የዲታውም! እነኝህንስ ኢትዮጵያ እና ኦነግ ሠራሹ ኦህዴድ በሩብ ልብ ቢያንስ ለመቀበል ቢያስብበት ስል በትህትና እና በአክብሮት አመለክታለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/12/2021 ኢትዮጵያዊነት የክት እና የዘወትር የለውም።  

#የደም ግብር ዘረፋ በአስቸኳይ ይቁም! 14.12.2021

ምስል
  #ይድረስ ለዘኃበሻ ዋና አዘጋጅ ለጋዜጠኛ ሄኖክ አለማዬሁ። #"የኢትዮጵያ ኃይሎች" እያልክ የምትዘግበው ከኡራኖስ ተላከልህን? #የደም ግብር ዘረፋ በአስቸኳይ ይቁም! እንደምን ሰነበትክ ልጅ ሔኖክ? ዛሬ የምር የሆነውን ግድፈትህን ልነግርህ እሻለሁ። ግን ደህና ሰነበትክ ወይ? "የኢትዮጵያ ኃይሎች" እያልክ የምትሰራው ዜና ታሪክን ጥቅርሻ የሚያለብስ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። አንተን የማዘዝ አቅሙ ባይኖረኝም የታሪክ ሊቀ - ሊቃውንት ሊሞግቱህ እንደሚገባ ግን አምናለሁ። ስለምን ዝም እንዳሉህ ይገርመኛል። ታሪክን ነጭ ባህርዛፍ አልብሰህ መቃብር ውስጥ አታስተኛ። እረፍ! ሃግ ልትባል ይገባል። ዜና ፕሮፖጋንዳ አይደለምና። ወይንም #የድብቅ የፖለቲካ ቅምጥ ፍላጎት ሱቅ በደረቴ። ያን ሁሉ ዘመን የደከምክበትን የተጋድሎ ዘመን ስለምን በወሳንሳ ለቆመ ሥርዓት ለማበርከት እንደተነሳህ አይገባኝም። ፎቅ? የአንድ አውሎ የቅፅበት ጉዳይ ነው። ከዕድሜህ በላይ አከብርህ የነበረው የቁም ነገርህ ዝልቀት ነበር። ብዙ ሠርተህ አግዘህ ነበር። የጥንቱ ሄኒ ናፍቆኛል። የዛሬው ግን ሃራም እዬሆነ ነው። ዛሬ ግን አንተ አይደለህም። አንተ እንድትሆን እሻለሁ። ይህን ሁሉ ግብር ለሚከፍል የአማራ ህዝብ ሥሙን ለመጥራት ስለምን ፈራህ? #ቅራቅር ላይ ብቻውን ባይመከት ይህ ሁሉ ዕድል ይኖር ነበርን? መልስ አለህን? ቀደም ባለው ጊዜ የአማራን የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ግንቦት 7 "የነፃነት ኃይል" እያለ ሲያላግጥ የአንተ ድህረ ገፅ እኛን በማሳተፍ ግንቦት 7 ስንሞግተው እንደነበር ታስታውሳለህ። አሁን አንተ #ተነከርክበት ። የት አምጥተህ ነው "የኢትዮጵያ ኃይል" የምትለው? የሚዋደቀው። 1) የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፣ አዬር ኃ

#በሰወች አትከፋ። ሰወች ሰወች እንጂ መላዕክ አይደሉምና። 14.12.2021

ምስል
  #በሰወች አትከፋ። ሰወች ሰወች እንጂ መላዕክ አይደሉምና።      ለቅንነት ስስታም አትሁኑ። አትሁኑ ስል ትዕዛዝ ሊመስልብኝ ይችላል። እርግጥ ነው አለቅነቴ ቆፍጣና ነው። እዚህ ላይ ግን እይታዬ ነው። ቢሆን ብላችሁ ውሰዱልኝ።   ግን ለቲም ወርክ ምቹ ነበርኩኝ። ለኮማንድ ፖስት ወታዳራዊ ያልሆነ ለፖለቲካ አደራጅነት ለምሳሌ የማህበራት ብሄራዊ ጉባኤ ወይንም፣ የፖለቲካ ድርጅት ብሔራዊ ጉባኤ ወይንም የፌድራሊዝም ብሄራዊ ጉባኤ ሊሆን ይችላል ኮማንድ ፖስቱ ላዛ መሪነት ምቹ ነኝ። የሰነድ ስርጭት፣ የመመሪያ ስርጭት ወዘተ ማዕከላዊ መምሪያ ማለት ነው ኮማንድ ፖስት፣ ለሆነ የዘመቻ ሥራ ማዕከላዊ ሆኖ ከተለመደው የተለዬ አስተዳደር እንደማለት። ጉዞም እንደዛው የተለዬ ተልዕኮ ያለው እንደ ማለት።    ዬሆነ ሆኖ ሥራ ህይወቴም አገሬም ነው። ታምሜ ስቀር ህመሜን የሚያበረታው ያ ነው። ከሥራ ገበታዬ መለዬት ህመሜን ያበረታዋል። #ሰው መሆን እና መስጠት።   ለሰው ልጅ ሁሉንም ትሰጡታላችሁ። ስንጥር ነገር ግን ሊያስከፋው ይችላል። አይከፋችሁ። አይጭነቃችሁ። ሰው መላዕክ አይደለም እና። እንደ መፅሐፈ ሄኖክ የወደቁ መላዕክት ናቸው የክፋት ምንጭ ይላቸዋል።    የሆነ ሆኖ ለአጭርም ይሁን ለረጅም በምንም ይሁን በማንም እግዚአብሔር ፈቅዶ ከሰው ጋር ትገናኛላችሁ። ከሰው ጋርም ላይሆን ይችላል ከአመክንዮ ጋርም ሊሆን ይችላል።    ስስታም አትሁኑ ውስጣችሁን በገፍ ስጡት። ሁለመናችሁን ገብሩለት። ያ የገበራችሁለት ነፍስ ይሁን አመክንዮ በቅፅበት ሊለያችሁ ይችላል። አትደንግጡ። ስታገኙት ይህ ሊሆን እንደሚችል ሁልጊዜ እሰቡት።    ሰው ሰው ነው። መላዕክ አይደለም። አመክንዮም ጊዜ ይጥለዋል፣ ጊዜ ያነሳዋል። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጆኖሳይደርነት ተሰርዞ "ጀግናችን"

#ሰዋዊነት ከምድራዊ ሥልጣን እና ክብር በላይ ነው! #ሰባዕዊነት ከምድራዊ ልዕልና ልቅና በላይ ነው ህገ መንግሥቱ እዮራዊ ነውና! 14.12.2021

ምስል
  #ሰዋዊነት ከምድራዊ ሥልጣን እና ክብር በላይ ነው! #ሰባዕዊነት ከምድራዊ ልዕልና ልቅና በላይ ነው ህገ መንግሥቱ እዮራዊ ነውና!     ኢትዮጵያ ያላችሁ የሰባዕዊ መብት ቀዳማይ ሞጋች ካፒቴኖች ባልደረባችሁን ሄዳችሁ አይታችኋት ይሆን? አቤቱታዬንስ የት አደረሳችሁት? መልስ እሻለሁ። #ይድረስ ለማከብረወት ለዶር ዳንኤል በቀለ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር። አዲስ አበባ፣ #ይድረስ ለማከብረወት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ካሉበት። #ይድረስ ለማከብርህ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች አዲስ አበባ። ጉዳዩ ስለ ሊቀ ትጉኃን ጋዜጠኛ እና የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ባልደረባችሁ ወሮ መዓዛ መሐመድ ይመለከታል። ስለ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በአካል ስለምታውቋት ብዙ ድካም አያስፈልገኝም። የሁላችን በርደን የተሸከመች ብቁ ናት። እኔ እራሴ የእሷ መንፈስ ልቆ ከወጣ ጀምሮ ያለኝ የውስጥ መረጋጋት ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። የውስጤ፣ የልቤ የሆነች የተግባር ልዕልቴ ናት። የአይዟችሁ ንግሥት ናት። የሃሳብ ፍሰቷ የድፍረት ልኳ፣ የግልፅነት አቅሟ እራሴን ያገኜሁባት፣ ያዬሁባት ህይወቴ ናት። በወጣትነቴ እኔ እሷን ነበርኩኝ። ለዚህም ነው እረፍት በሚያስፈልገኝ ወቅት እስሯን ስሰማ ደንግጬ ፌስቡክ የገባሁት። እርግጥ ነው የጋዜጠኛ ታምራት ነገራን ስሰማ ደንግጬ ነበር። የእሷ ከሴትነቷ አንፃር፣ ወጣትነቷ ታክሎ ከምትወስደው መጠነ ሰፊ የኃላፊነት እና የተጠያቂነት አድማስ አኳያ እጅግ እጅግ አስደንጋጭ ነበር እስሯ። እረፍት አይሰጥም። አይዟችሁን የሸሸው ኦህዲድ መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ አንድ ቀን ለዚህ ሁሉ ሺህ ህልፈት ብሔራዊ ሰንደቅ ዝቅ አድርጎ ማውለብለብ የተሳነው ከንቱ ካቢኔ እሷ እና ቲሟ ግን ብዙ በጣም ብዙ ድንቅ ደግ ተግባራትን ፈፅመዋል። ያ ከንቱ

ኢትዮጵያዊነት ፈተናውን እንዲያልፍ ከተፈለገ።

ምስል
  ኢትዮጵያዊነት ፈተናውን እንዲያልፍ ከተፈለገ።   1) የአማራን ህዝብ ሰቆቃ ለመርዳት የተለያዩ ተቋማት ተከፍተዋል። ጋዜጠኛ አበበ በለው የሚያስተባብረው የገዘፈ አካል አለ፣ ጥቂቶቹ … 1.1አሁን በቅርቡ የሰማሁት የተሰው የፋኖ ልጆችን ለማሳደግ በነፍስ ወከፍ የተጀመረ ቤተሰባዊ ፕሮጀክት አለ። በማስተዋል የተያዘ። ስኬታማ የሆነ። 1.2 በመንግሥት የሚመራ ለሰራዊቱ የሚሆን ሌላ ፕሮጀክት አለ። 1.3 በእነ አርበኛ ዘመነ ካሴ የሚመራ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክትም አለ። ሁሉም የአቅሙን፣ የሚችለውን፣ የወደደውን መርዳት መብቱ ነው። በመንፈስ ይሁን በመዋዕለ ንዋይ። በፀሎት ይሁን በሃሳብ። ብቻ ችግር መጋራት። የቻሉትን ማድረግ። በፁሁፍም የምርምር ተግባር የከወኑት የኔታ ፕ/ ኃብታሙ ተገኜ እና የኔታ አቻም የለህ ታምሩ ዘላቂ የአማራ እርስቶችን ህጋዊ ዕውቅና እንደ ስፔኖች ለማስመለስ ዩንቨርስቲ ከፍተዋል። መፍትሄውም እሱ ነው። በሌላ በኩል የአማራ ጉዳይ ለራሱ ለአማራ ልጆች የተተው ነው የሚመስለው። አራት ዓመት ሙሉ እዬታከተም ነው። ሌሎችም በተለያዬ ፎርማት የበኩላቸውን የሚያደርጉ እንደ ቀደምቱ ሞረሽ ዓይነቶቹም አሉ። 2/ በአፋር በአቶ ጋህሳይ የአፋር ሚዲያ ኢንፎርሜሽን ሚዲያ ማዕከል መሥራች ወይንም ሴንተር እንዳለ በጋዜጠኛ አበበ በለው ቴሌቪዥን አዳምጫለሁ። እነሱንም ማበረታታት ያስፈልግ ይመስለኛል። የአማራ ተጋድሎን በፈጣሪ በአላህ ፈቃድ በአፋር አናብስት ባይደገፍ የዛሬው ቀን ያበቃ ነበር። ይሰበር ነበር። ስለሆነም። አፋሮችን በሃሳብ፣ በሞራል፣ በተስፋ መርዳትም ያስፈልጋል። የሚችልም በአቅም። 3) የነገሌ ቦረና ጉዳይ ነው። የኦነግ ፖለቲካ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው መጠነ ሰፊ የማጥቃት መከራ ጋር ይህን ሃሳብ ሳነሳ የሚኮሰኩሳችሁ ሊኖር ይችላል። በእኔ በራሴ በግል ህይወ