#በሰወች አትከፋ። ሰወች ሰወች እንጂ መላዕክ አይደሉምና። 14.12.2021

 

#በሰወች አትከፋ። ሰወች ሰወች እንጂ መላዕክ አይደሉምና። 
 
 No photo description available.
ለቅንነት ስስታም አትሁኑ። አትሁኑ ስል ትዕዛዝ ሊመስልብኝ ይችላል። እርግጥ ነው አለቅነቴ ቆፍጣና ነው። እዚህ ላይ ግን እይታዬ ነው። ቢሆን ብላችሁ ውሰዱልኝ።
 
ግን ለቲም ወርክ ምቹ ነበርኩኝ። ለኮማንድ ፖስት ወታዳራዊ ያልሆነ ለፖለቲካ አደራጅነት ለምሳሌ የማህበራት ብሄራዊ ጉባኤ ወይንም፣ የፖለቲካ ድርጅት ብሔራዊ ጉባኤ ወይንም የፌድራሊዝም ብሄራዊ ጉባኤ ሊሆን ይችላል ኮማንድ ፖስቱ ላዛ መሪነት ምቹ ነኝ።
የሰነድ ስርጭት፣ የመመሪያ ስርጭት ወዘተ ማዕከላዊ መምሪያ ማለት ነው ኮማንድ ፖስት፣ ለሆነ የዘመቻ ሥራ ማዕከላዊ ሆኖ ከተለመደው የተለዬ አስተዳደር እንደማለት። ጉዞም እንደዛው የተለዬ ተልዕኮ ያለው እንደ ማለት። 
 
ዬሆነ ሆኖ ሥራ ህይወቴም አገሬም ነው። ታምሜ ስቀር ህመሜን የሚያበረታው ያ ነው። ከሥራ ገበታዬ መለዬት ህመሜን ያበረታዋል።
#ሰው መሆን እና መስጠት።
 
ለሰው ልጅ ሁሉንም ትሰጡታላችሁ። ስንጥር ነገር ግን ሊያስከፋው ይችላል። አይከፋችሁ። አይጭነቃችሁ። ሰው መላዕክ አይደለም እና። እንደ መፅሐፈ ሄኖክ የወደቁ መላዕክት ናቸው የክፋት ምንጭ ይላቸዋል። 
 
የሆነ ሆኖ ለአጭርም ይሁን ለረጅም በምንም ይሁን በማንም እግዚአብሔር ፈቅዶ ከሰው ጋር ትገናኛላችሁ። ከሰው ጋርም ላይሆን ይችላል ከአመክንዮ ጋርም ሊሆን ይችላል። 
 
ስስታም አትሁኑ ውስጣችሁን በገፍ ስጡት። ሁለመናችሁን ገብሩለት። ያ የገበራችሁለት ነፍስ ይሁን አመክንዮ በቅፅበት ሊለያችሁ ይችላል። አትደንግጡ። ስታገኙት ይህ ሊሆን እንደሚችል ሁልጊዜ እሰቡት። 
 
ሰው ሰው ነው። መላዕክ አይደለም። አመክንዮም ጊዜ ይጥለዋል፣ ጊዜ ያነሳዋል። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጆኖሳይደርነት ተሰርዞ "ጀግናችን" ተባለ እኮ። 
 
ዕልፎች መንገድ ላይ፣ ሺወች መቃብር ውስጥ፣ ሺወች ካቴና ላይ፣ ሚሊዮኖች ጠኔ ላይ፣ ተፈጥሮም ዕንባ ላይ ሆነው።
አያችሁ አመክንዮ እራሱ እንደምን ትቅማጥ በትቅማጥ እንደሆነ። እሳቸውን ሞጥሮ የሚቃወመው ህወኃት ገፍቶ እንዲመጣ፣ ኦነግ አቅም እንዲያገኝ ፈቀዱለት አብይዝም ይሻለኛል እንዲባሉ። 
 
በዚህ መሐል የድል አጥቢያ አርበኞቻቸውን ይዘው ብቅ አሉ። ምርጫ አሳጡት ዜጋውን። በማን ይፈረድ?
#የሆነ ሆኖ ለዬትኛውም የገጠመኝ ትስስር …
 
ግልፅነታችሁን ስጡት። ንፁህ ድንግልናችሁን መግቡት። በራሱ ጊዜ መጥቶ በራሱ ጊዜ ሲሄድ በተቀበላችሁት ልክ በውስጣችሁ አስቀምጡት። ያን ክብሩን አትንፈጉት። 
 
አመክንዮው ይሁን ሰብዕናው የተከፋባችሁን አልገለፀላችሁም ስለዚህ እናንተ በቦታው እንደ ተከላችሁት አፅድቁት። ከጥሪያችሁ አትጉደሉ። መልካምነት አትራፊ ነው።
 
ቅንነት የበረከት እልፍኝ ነው። ፍቅራዊነት የውስጥ ሰላም ነው። የሰው ልጅን ይሁን የምታከብሩትን አመክንዮ በውስጣችሁ ባኖራችሁት ቁጥር የአቅም ፏፏቴ፣ የውስጥ ሰላም ፏፏቴ፣ የፀጋ መንበር በውስጣችሁ ፀንቶ ይሰፍናል።
 
ብቻ አቅዳችሁ አታስከፋ። አቅዶ የሰው ሰላም ማወክ ዲያቢሎስነት ነው። ለሰው ልጆች የውስጥ ሰላም ተጠንቀቁ።
ያስከፋችሁ ከመሰላችሁ ፈጥናችሁ ይቅርታ ጠይቁ። ዕድሉን ከሰጣችሁ ተከፋሁ ባዩ። ካልሰጣችሁ የእናንተ ጉዳይ አይደለም። ጠብቁት።
ተመልሶ ከመጣ ወቀሳ አያስፈልግም። በፍቅር ተቀበሉት። ፍቅር ቂመኛ አይደለም። ፍቅር የምህረት ደጀሰላም ነው። ፍቅር ስላችሁ በተቃራኒ ፆታ ያለ ሊመስላችሁ ይችላል። ወይንም የሰው ለሰው ብቻ። እእ። 
 
የአመክንዮም ሊሆን ይችላል። የዝማሬም ሊሆን ይችላል። የድምፅም ሊሆን ይችላል። የፏፏቴም ሊሆን ይችላል።
በህሊና ድንግልና ለሚፈፀም ለማታውቅት መከፋት፣ ላልተነገራችሁ ቅሬታ እናንተ ተጠያቂ ልትሆኑ ፈፅሞ አትችሉም እና አይጭነቃችሁ። ውስጣችሁን አትረብሹት።
 
ብቻ በማናቸውም ጊዜ እና ሁኔታ ንፅህና ጎዳናችሁ ይሁን። ድንግልና- ቅንነት - ግልፅነት - አክብሮት - የወረት ያልሆነ፣ ባተሌ ያልሆነ፣ ፍፁም ታማኝነት ለዬትኛውም ግንኙነት ይኑራችሁ።
 
ለዬትኛውም ግንኙነት ዕውቅና እና አትኩሮት ስጡት። የእኔ በሉት። የውስጥ አድርጉት። በትርፍነት አትዩት።
ኢትዮጵያን የሚመሯት ችግራቸው ይኽው ነው። ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆሩም መውጣት ያልቻሉት ዳገት ይህ ነው። ውስጣቸውን ሲያገኙ አያከብሩትም። ይንቁታል ወይ ይተውታል።
ብቻ እናንተ ለተሰጣችሁ ኑሩ። በቅንነት ሁሉንም አስተናግዱ። ለተሰለፋችሁበት ዓላማና ግብ ታማኝ ሁኑ።
ይህን አድርጋችሁ፣ ይህንም ሁናችሁ፣ ሁሉንም ሰጥታችሁ ለሚመጣው ማናቸውም ነገር በፀጋ ማስተናገድ ነው። ሰው ሰው እንጂ የሰማይ መላዕክ አይደለምና።
ብቻ ከእናንተ አይጉደል። የሰጣችሁ የላይኛው ይዳኘዋል። ጊዜም ያነጥረዋል። ደግነት ወርቅ ነው እያማረበት እንጂ እዬወዬበ አይሄድም።
ቅንነት እዬፈካ እንጅ እዬበለዘ አይሄድም። ታማኝነት እያለመለመ እንጂ እየዛገ አይሄድም። ሥርጉተሰብለህይወት ትናትም ዛሬም እሷ እሷው ናት። በልጅነት የሚያውቋትም በሙሉ ዕድሜም እንደ ተፈጠረችበት አለች እንዳለች።
በዚኽው ትዘልቃለች። የዛሬ 10 ዓመት ዕድሜው ከሰጣትም ይችው ናት አቋሟዋ።
#እኔን ሳዬው እንደ መከወኛ። "ምራቂ።"
በተፈጠረችበት ልክ ናት የእኔነት እሷ። አትከለስ - አትበወዝ። አንድ ተፈጥሮዋ። አንድ ሰብዕና። መታመን።
የሰው ልጅን በልኩ ማክበር። እምታምንበትን ዓላማ እና ግብም በመታመን መዝለቅ ማዝለቅ። በቁጥብነት መኖር።
በፍፁም ታማኝነት በተዕቅቦ ኑሮን መምራት። ለዕንባ ዋናተኞች የግንባር ሥጋ መሆን። በነፃ ማገልገል። ድብቅ ብሎ መኖር። እዩኝን መሸሸት።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/12/2021
እራስን ሳይሸሹ መኖር የመሰለ የመኖር አውራ የለም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።