#ህልውና እንዴት ይቀጥል? #መቅድመ ሟተት። 14.12.2019
#ህልውና እንዴት ይቀጥል?
#መቅድመ ሟተት።
የአማራ እና የአማራ መንፈሶች፣ የአማራ እና የአምርኛ ቋንቋ ወዳጆች፣ የአማራ እና የአማራ ወዳጅ ብሄረሰቦች ህልውና እንደምን ይቀጥል? የአማራ ትውፊት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ወግ፣ አስተሳሰብ፣ ጥሪት እንደምን ይቀጥል? በኽረ አጀንዳው ይህ ነው።
ጋንቤላ የተዳፈነ መከረ አለ። አንድ ቀን ይፈነዳል። የሳቢያ ቀውስ ይደራጅለት እና ቀስቱ በአማራ እና በአማራ ወዳጆች እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ይስተናገዳል። ጠብቁት።
#ውቅረ - ሂደት፣
ለቅሶ፣ ድንኳን ተከላ፣ ቹቻ እና ሰኔል ዛሬ ላይ ወግድልኝ እዬተባለ ነው። ይህን ማስቆም ዬሚቻለው በዓለም ዓቀፍ ህግ ብቻ ነው። ህወሃት ስለተወገደ የአማራ እና የወዳጆቹ ህልውና ተረጋገጠ ማለት አይደለም።
የ50 ነቀርሳ ከእነ መርዝ አከፋፋዮች ጋር አብሮ አለ። በውስጥ የጣዖቱ ምስረታ እና ፅናት ህሊና ውስጥ አለ። ኢብን ህገ መንግሥቱ ሙሉ ለሙሉ ቢሰረዝ ሙሉ ፈውስ አይገኝም። መርዙ ከደም ጋር ተዋህዷል።
እሰቡት የሰኔ 15/2011 የጠቅላዩን ንግግር ዓለም ዓቀፋዊ ዘመቻ፣ እሰቡት የባልደራስ ምስረታ እና የጠቅላዩ በሰጨኝን። በሰጨኝ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ላለ አያምርም ብዬ በወቅቱ ፅፌያለሁኝ።
ጠቅላዩ ምን ሲሆን ደማቸው ይፈላል፣ ቱግ ይላሉ ቢባል ነገረ አማራ ሲነሳ ብቻ። ከጠቅላይነታቸው በፊት መንፈሳቸው ርህርህና የዘለቀው ሰውነት ነበራቸው። ቃናው እራሱ አይጠገብም ነበር። የአኖሌ ሃውልት መሥራችነታቸውን ቸል ትሉት ዘንድ ያስገድዳል።
#ፍትኃት ከአሰኜ።
ፍትኃት ካማረ መፍትሄው ከላይ እንደጠቀስኩት በታሪክ ጉዳይ፣ በህግ ጉዳይ፣ በሰባዕዊ መብት ጉዳይ የሚያተኩሩ ቅኖች ሰብሰብ ብለው እርስታችን እንወቅ የሚል ሉላዊ ንቅናቄ መጀመር ግድ ይላቸዋል።
መጤ፣ ሰፋሪ፣ ወራሪ፣ ተስፋፊ፣ ፈንቃይ አፈናቃይ ከሥሩ ለመንቀል እንደ ስፔኖች ልባም ተግባር መከወን ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከመፋተግ።
የወረረ፣ የተስፋፋ፣ ሰፋሪ፣ መጤን የሚዳኛው ዕውነት በህግ አደባባይ መልስ ሲያገኝ ብቻ ነው። ለዚህ ትጋት ያለው ተግባር ቢከወን ከህግ በላይ መሄድ አይቻልም። ሁሉም ልኩን አውቆ፣ እግዚአብሔርን አላህን አመስግኖ ይኖራል።
ይህን ለማድረግ አቅምን ቆጥቦ ግብ እና ዓላማ ነድፎ ሁነኛ ተጋድሎ ማድረግን ይጠይቃል ቅን ደፋር ቢገኝ። ህግ ይዳኜዋል። ሞትም ርጋ ይባላል። መፈናቀልም ርጋ ይባላል። መታበይም ርጋ ይባላል። ትውልድ በአገሩ የኑሮ ዋስትናው በህግ ይረጋገጥለታል።
እርግጥ ገንዘብ ያስፈልገዋል። ሃሳቡን አደራጅቶ ለመምራት ተቋም ከተፈጠረ ሁሉም የአቅሙን ያደርጋል። ዘርህ እዬፈለሰ በዕለታዊ መብተክተክ መፍትሄ አይገኝም።
አንድ ነፍስ ብቻውን በራራ ጥንታዊት ርዕሰ መዲናን ሠራ። በብዙ ድካም፣ በብዙ ልፋት የመገለጥ ዘመንን ዓወጄ፣ ወልቃይት ጠገዴን በሚመለከት እንዲሁ አንድ ነፍስ ዕውነትን አፈለቀ።
ይህን ወደ ተቋም ቀይሮ ህጋዊ መሠረት ማስያዝ ደግሞ ለዘመኑም ለትውልዱም ፍትኃት ነው። እንጨት ተለቅሞ ማሰሪያ ከሌለው ተበትኖ ይቀራል።
የዬኔታ ኃብታሙ መንግሥቴ ተገኜ፣ የዬኔታ አቻምዬለህ ታምሩ የጥናት የፋክት ውጤት ተቀናጅቶ ተቋም ቢሆን መኖርን የማኖር አቅሙ የትውልድ ነው። ዕድሉን ማደራጀት፣ መምራት፣ ማስተዳደር ይገባል።
ለዚህ ነው እኔ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሉላዊ እገዛ ያስፈልገዋል የምለው። ብቻውን አይወጣውም። ፈፅሞ።
አደብ የገዛ፣ የሰከነ በብጥቅጣቂ ድሎች የማይኩራራ፣ በቀል ያላጨው፣ ጥላቻ ያልገሸረው፣ ቂም ያላጠነው ሰውኛ፣ ህሊናኛ ተቋም ያስፈልጋል። ለዚህ አቅሙ፣ ብቃቱ ያላቸው ሊቃናት አሉ።
ኃላፊነቱን ወስዶ ሙያ በልብነቱን ደግሞ የፈጣሪን ፈቃድ ጠይቆ መጀመር የቅዱሳን ተግባር ይመስለኛል። ይህን መከራ የሚዳኜው ዓለም አቀፍ የችሎት አደባባይ ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ሊቃናት አጋጣሚውን ካገኙ ጥላቻቸውን በተለያዬ ድርጊታቸው ይገልፁታል። የአማራ ልጅ ደግሞ የተገባውን ያህል የህሊና መሰናዶው ትጥቅ እንብዛም ነው። በዚህ ያለቅሳል፣ በዛ ይሸልማል። ጉራማይሌ ወይንም ዝብጠት።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/12/2020
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ