የሥርጉትሻ ቅኔወች። ታይታ የጤዛ ጎፈሬ ነው። ቃል የፈጠረው ሰው በቃሉ ውስጥ መኖርን ፈራው - ሳ? የፍቅር ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ገብተው ሊማሩት የሚገባ ጥበብ ነው።
በራስ ውስጥ ያለ እርቀሰላም ታማኝነት ነው። ቢያንስ ለራስ ፍላጎት እና ራዕይ ታማኝ መሆን።
በመሪነት ውስጥ መታመን ከሌለ ተስፋ አረረ።
ውሸት ጣፋጭ የሚሆነው ሃቅን እንደ ጦር በሚፈራ ህሊና ብቻ ነው።
የካህዲ ህሊና ደብዳቢው እራስ በራሱ ነው።
በመኖር ውስጥ ያለ ድንግልና መታመን ነው።
ለዛሬ ብቻ የሚኖር ሰብዕና ለማግሥት የህሊና ስንቅ የለውም።
እራሱን ያጣ የነጣ።
በሂደት ውስጥ ወጣገባ መኖሩ ላወቀበት የብስለት ማሳ ነው።
ለማድመጥ ያልታደለ የአገር መሪ ዕውቀትን የመቀበል መክሊቱ የነፈሰበት ነው።
ለአዲስ ነገር ብቻ አትጓጓ፣ እርሾ ለሆነው የቀደመ ፀጋም ትኩረት ስጠው። መነሻ የሌለው መድረሻው መሃን ነውና።
ጥልቀት ከሃሳብ ምጥቀት፣ ጥበብ ከማስተዋል ይበቅላል።
በእምታ ውስጥ ያለ ምጣዊ አመክንዮ የእዮርን ደጅ የማስከፈት አቅም አለው።
ፍቅርን ሳቅንነት ያለው ፍጡር ለትውልድ ልዩ የምሥራች ነው።ትኖርበት ፍቅርን መሸመትም ማቅናትም አይቻልህም። ምክንያቱም የድንግልና ህፃፅ ሊኖርብህ ስለሚችል።
በቅንነት ውስጥ ያለ ፅኑ ሰላም የሚህል ዓለም የለም። ቅንነት 13ኛው ፕላኔት ነው።
መልካም ሰው ስለሌላው ቀና መንገድ ይጠርጋል፣ ክፋ ሰው ግን መንገድ ለመዝጋት እንቅፋት ሲተክል ውሎ ያድራል።
መደራጀት አቅምን ማማከል ነው። ስለሆነም የአማራ ልጅ መደራጀትን እንደ መደበኛ የህይወቱ ክፍል ማዬት ይኖርበታል።
ቃል የፈጠረው ሰው በቃሉ ውስጥ መኖርን ፈራው - ሳ?
አጭርነት የአስተሳሰብ ድህነት ብቻ ነው። የሰው አጭር የለውም። የተፈጥሮም አጭር የለውም።
በጭንቀት ውስጥ ጭንቀትን ከማስጨነቅ፣ በጭንቀት ውስጥ ሰባዊነትን ማበልፀግ ብልህነት ነው።
ታይታ የጤዛ ጎፈሬ ነው።
ሩቅ ያለ የምሥራች ባለቤቱ ካላወቀበት ይመንናል።
ፈጣሪ የሰጠውን መልካምነት የሰው ልጅ ገደደው።
የሰው ልጅ ሥጦታው ፈጣሪ/ አላህ የሸለመውን ዓውደ ጊዜ ለቸርነት ቢያውለው ፕላኔታችን ፊቷ አይበልዝም ነበር።
በመከፋት ውስጥ ያለ ቸርነት ምርቃት ነው፣ ችግር ውስጥ እያለ ስለሰው ልጅ እንግልት የሚባዝን የትውልድ አብነት ነው።
በሰው ህይወት ከገባህ ጥንቃቄ ይኑርህ፣ ጥንቃቄ ከጎደለ ሰበቡ የዛን ሰው ጠቅላላ መዋለ ዕድሜ ከንቱ ሊያደርገው ይችላል እና።
ሚዛን ያለው ጊዜ ብቻ ነው።
የፍቅር ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ገብተው ሊማሩት የሚገባ ጥበብ ነው።
የፍቅር ተፈጥሮ ረቂቅ ንጥረ ነገሮች የሰከኑበት ነው። ስለሆነም እንደ ማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ሊመረቁበት የሚገባ የዕውቀት ዘርፍ ነው።
በፍቅር ተፈጥሯዊ ህግጋት ፕላኔታችን መምህር፣ ኤክስፐርት፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ ስሌላት ለእኔ ፕላኔታችን አንገት ያልተሰራለት ሰው መስላ ትታዬኛለች።
ውዷ ፕላኔታችን ልዕልት መሬት አንድም ቀን በፍቅር ተፈጥሯዊ ህግጋት ላይ አጀንዳ ኑሯት አያውቅም። ስለዚህም ነው አስፈሪ የሆነችው።
ንግሥት መሬት በፍቅር ተፈጥሯዊ ህግጋት ተኮር መጋዝን፣ የራዲዮ እና የቴሌቪዥን መደበኛ ፕሮግራም፣ ጋዜጣም ኑሯት አያውቅም። ስታሳዝን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
14.12.2019
Sergute©Selassie
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ