ህሊናዊነት ሲያቃትት በአንድአፍታ ሚዲያ። #ጠና #ያለ #መርኃዊ #ሙግት በፓርቲ አወቃቀር። 14.12.2020
ህሊናዊነት ሲያቃትት በአንድአፍታ ሚዲያ።
#እፍታ።
አቁነጠነጠው ማህበረ ኦሮሙማ። አሽሙሩ "ትዕቢቱን አስተነፈስነው፣ ቀመሳት ዓይነት ነው" በማን ላይ ቁመሽ ነው ነገሩ።
"መደመር" የመድሎት ቅጂ፣ "መደመር" የሦስተኛ አማራጭ መንገድ ተቀረጣጥፎ፣ በኮፒ ራይት ዝርፊያ ተወራርዶ ስለመሆኑ የፖለቲካ ሊቃናቱ ሲናገሩት ቆይተዋል። የምናዬውም ይኽው ነው በቃላት ቢሽሞነሞንም።
አሁን እንኳን የዚህ ሁሉ ድቀት መሠረቱም አንድ ኃላፊነት የሚሠማው ሙሉ መንግሥታዊ አካል በብዙ ወዘተረፈ ባለሙያ የሚያሰናዳውን በአንድ ሰው የህሊና ቅባዕነት መንጭቶ የሽግግር ሰነድ ተዘጋጅቶ የሚቀበለው በመጥፋቱ ነው።
ለእናንተ ለማህበረ ኦሮሙማ ቀላል ነው የዚህ ሁሉ ህዝብ ሞት፣ ስደት፣ የአገር ኃብት ውድመት፣ የቂም በቀል መፈልፈል፣ የሥነ - ልቦና ጉዳት። ጨካኞች።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ዘመንን አንብበው ጉዳት በሚቀንስ መልኩ፣ በትንሽ የመሸነፍ ኪሳራ አገር እንዲተርፍ ሰነድ ተዘጋጄ። ለሽ ብሎ የባጀው ሁሉ ባትቶም መሰናዶ ጀመረ የፋክክር በሚመስል መልኩ።
… ያ ብቁ፣ ብጡል፣ ጥበብ ህሊና ደግሞ የአቶ ልደቱ አያሌው ነው። አሁን ያ ዝርክርክ፣ ያ ዝልግልግ፣ ያ ዝርግፍግፍ የኦህዴድ የትቢት ግብረ ኃይል ከአቅም ተቆጥሮ ለእሱ ጥብቅና መቆም ዝልብነት ነው።
ምን አለውና ኦህዴድ? ቢነሳ ቢወደቅ አንድ ሰው ነው ያለው፣ ያም አንድ ቀን የታሰበው በሌላው ቀን በጥሰት መጪታ ሲያሽካካ፣ ሲያውካካ።
#"የብልፅግና" #ንቀት ስለተባለው።
ምን አቅም ኑሮት ፋከራ እንደ ተጀመረ መሳቂያነት ነው። የአንድ አፍታ አነብናቢ አቅሙ ካለው እኔን ይምጣ እና ይሞግተኝ። ለመሆኑ ብልፅግና የሚባል የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያ አላትን?
መልስ ~~~ #የላትም። በሌለ ነገር ንቀትም፣ ግነትም የለም። እንዴት? እንዴት ማለት ጥሩ ነገር ነው። እስቲ ከልቁ ዳንኪራ ተውጥቶ መርኃዊውን ቲወሪ እንፈትሽ - ተመጥኖ።
#የፓርቲ መሠረታዊ ሠነዳት።
1) #ደንብ --- የአባላት መብት እና ግዴታ፣ የዓርማው ትርጓሜ እና ውስጠቱ የሚዘረዘርበት። ጠቅላላ የፓርቲው የህሊና መስመር ጭማቂ በኪስም መያዝ የሚችል።
2) #ፕሮግራም ---- የፓርቲው ዓላማ እና ግብ የሚይዝ፣ የፖሊሲ ማህፀን ልበለው። እጥር ምጥን ብሎ የሚጋጅ ማኒፌስቶ።
3) መሪ ዕቅድ ከደንቡ እና ከፕሮግራሙ ተጨምቆ የሚሰናዳ አቅጣጫ አመልካች መኃንዲስ። እጥር ምጥን ያለ ማኒፌስቶ።
3.1 የአጭር ጊዜ ዕቅድ (ከ1 ወር እስከ 1 ዓመት)
3.2 የረጅም ጊዜ ዕቅድ (ከ5 ዓመት-10 ዓመት)
3.3 የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ፣ ዬአጭር ጊዜውን እና ረጅም ጊዜውን የሚያይዝ ሊንክ ወይንም ድልድይ ልንለው እንችላለን ።
4) የውስጥ መመሪያ ዝርዝር የአካላቱን ተግባር እና ኃላፊነት የአፈፃፀም ሂደት የሚገልፅ። ከደንቡ፣ ከፖሮግራሙ እና ከመሪ ዕቅዱ ተጨምቆ የሚዘጋጅ ደጎስ ያለ ሰነድ።
ሦስቱ መሠረታዊ ሠነዶች በብሔራዊ ጉባኤ ብቻ ይፀድቃሉ። ደንቡ፣ ፕሮግራሙ፣ እና መሪ ዕቅዱ። የሚሻሻሉት፣ የሚለወጡትም በብሔራዊ ጉባኤ እንጂ በአጤ አብይ የህሊና ዳንቴል ጉባኤ አይደለም።
የሆነ ሆኖ #የውስጥ መመሪያው ግን በፖሊት ቢሮ ሊዘጋጅ፣ ሊፀድቅ ይችላል። ሊሻሻልም።
#የብሔራዊ ጉባኤ ተግባር እና ኃላፊነት።
1) የመወያ አጀንዳን ማፅደቅ።
2) የመክፈቻ ንግግርን ማድመጥ እና በሰነድነት ማፅደቅ።
3) ሪፖርት ማድመጥ፣ ማፅደቅ።
3.1 የፖሊት ቢሮ ሪፖርት፣
3.2 የኦዲት ኮሚሽን ሪፖርት፣
3.3 የቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርት፣
2) የፓርቲ መሠረታዊ ሰነዶችን ደንብ፣ ፕሮግራም፣ መሪ ዕቅድ ተወያይቶ ማፅደቅ።
3) የአሥመራጭ ኮሚቴን መምረጥ።
4) የማዕከላዊ ኮሜቴን መምረጥ።
5) የቁጥጥር ኮሚሽንን መምረጥ።
6) የኦዲት ኮሚሽንን መምረጥ።
7) የማዕከላዊ ኮሜቴ አባላትን፣ የቁጥጥር ኮሚሽንን፣ የኦዲት ኮሚሽንን አካላት መምረጥ ብቻ ሳይሆን ግድፈት ፈፅመዋል ሲልም ያሰናብታል።
በደንቡ ውስጥ አብሮ ቢፀድቅም ዓርማ የማፅደቅን ኃላፊነትም የብሔራዊ ጉባኤው ብቻ ነው።
#የማዕከላዊ ኮሜት ኃላፊነት እና ድርሻ።
1) ማዕከላዊ ኮሜቴው ጉባዔው እስኪበሰብ ድረስ የጉባኤውን ሙሉ ሥልጣን እና ኃላፊነት ተክቶ ይሠራል። ሪፖርትም ያቀርባል።
2) የፖሊት ቢሮን ይመርጣል።
3) የፖሊት ቢሮውን ኃላፊነት ያልተወጡትን፣ ያርማል፣ ካልሆነም ያሰናብታል።
4) በፖሊት ቢሮ ስብሰባ የቁጥጥር እና የኦዲት ኮሚሽን ሰብሳቢዎች ድምፅ አልባ ሆነው ይሰበሰባሉ።
5) የማዕላዊ ኮሚቴው ተጠሪነት ለብሔራዊ ጉባኤ ብቻ ይሆናል።
#የፖሊት ቢሮ ኃላፊነት እና ተግባር።
1) የፖሊት ቢሮው ተጠሪነቱ ለመረጠው አካል ለማዕከላዊ ኮሜቴ ብቻ ይሆናል።
2) የፖሊት ቢሮ የራሱን ሥብሰባ አድርጎ ሰብሳቢውን፣ ምክትሉን፣ ፀሐፊውን እና የሌሎች የሥራ ዘርፍ ኃላፊነቶችንም ይደለድላል።
#የቁጥጥር እና የኦዲት ኮሚሽን።
የቁጥጥጥር ኮሚሽን በፓርቲው የውስጥ አደረጃጀት፣ አፈፃፀም ዲስፕሊን ተኮር ተግባራትን ሲከውን፣ ኦዲት ኮሚሽን ከፋይናንስ፣ እና ከሎጅስቲክስ ጋር ያሉ ሁነቶችን ይከታተላል።
ይህም ማለት ቁጥጥሩ በሰብዕና መንፈስ ውስጠት፣ ኦዲት ቁስ ተኮር አፈፃፀምን ይከታተላል ማለት ነው።
የኦዲት ኮሚሽን፣ የቁጥጥር ኮሜሽን፣ ማዕከላዊ ኮሜቴ የሚመረጡት፣ የሚሰናበቱት በጠቅላላ ጉባኤው ብቻ ነው። ተጠሪነታቸውም ለብሔራዊ ጉባኤ ነው።
#ኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽናት።
ሁለቱ ኮሚሽናት የራሳቸውን ስብሰባ በማድረግ ሰብሳቢ፣ ምክትል እና ፀሐፊ ይመርጣሉ።
#አወቃቀር። ከታች ወደላይነት።
መሠረታዊ ድርጅት የሁሉም መሠረት ነው። ማንኛውም አካል የሚመረጠው፣ በዬደረጃው የሚወከለው ከመሠረታዊ ድርጅት የቀጥታ ምርጫ ይሆናል። ከታች ወደ ላይ። የወረዳ፣ የዞን፣ የክልል ደግሞ በውክልና ምርጫ ይከወናል።
#ሂደቱ።
መሠረታዊው ወረዳን፣ ወረዳው ዞኑን፣ ዞኑ ክልሉን፣ ክልሉ ብሄራዊ ጉባኤ ይፈጥራሉ። እንደ አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ያሉ ከተሞችም እራሳቸውን ችለው ለብሄራዊ ጉባኤ ይወከላሉ።
#የአንድ አፍታ ሚዲያ ኩርፍርፍ ቅርሻ።
አቶ ልደቱ አያሌውን አንድ አፍታ ሚዲያ የከሰሰበት "ብልፅግና" አቅም የለሽ ብለው አቃለዋል ነው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ደግሞ ብልፅግና የሚባል ፓርቲ የለም ባይ ነኝ።
ማቃለል ወይንም ማግነን ሲኖርህ ነው። አብይዝም የሚባል የኢማጅኔሽን መንፈስ ግን አለ። ልቅ የሆነ። የፓርቲ አደረጃጀት፣ አመሠራረት መርኾዎች የማያውቀው።
ስለሆነም ግልቢያ ላይ ያለው አንድ አፍታ ሚዲያ ፓርቲ ማለት የገዳ የፋቲክ ማህበር ማለት እንዳልሆነ ሊረዳው ይገባል። ቀድሞ ነገር አዴፓን የትናንቱ የትኛውም ድርጅት ሊናገረው አይችልም፣ መኢህአድ ግን ይችላል።
"ብልፅግና" የጠቅላይ ሚኒስተሩ የህሊና ዳንቴል ነው።
"ብልፅግና" የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የህሊና ዳንቴል ነው። እሳቸው እራሳቸው የፓርቲ አመሠራረት ህጉን አያውቁትም። ፈፅሞ አያውቁቱም። ችግሩ ይህ ነው።
እንዲማሩበት ከዚህ ቀደም የምርጫ ቦርዳቸው እንደ ጨነገፈ ስፅፍ ፅፌላቸው በማግሥቱ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደው #መሪ ዕቅድ አፀደቅን ብለው ሲንደፋደፋ እኔ እስቅ ነበር። ያም ህገ ወጥ አካሄድ ስለሆነ። መሪ ዕቅድ በብሔራዊ ጉባኤ ብቻ ነው የሚፀድቀው።
አንድ የፖለቲካ ድርጅት ዲስፕሊኑን ከሞል ሄደህ አትገዛውም። መርህ አለው ሁለንትናዊ፣ ስክነቱ በሂደት ነው የሚመጣው።
#በታሪክ አንድ አባል የሌለው "የብልጥግና" ፋገራ።
ለኮረፍራፌ ለአንድ አፍታ ሚዲያ ልነግረው የምሻው መሥራቹ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ "የብልፅግናቸው" አባል እንዳልሆኑ ላርዳው።
አባልነት በፈቃደኝነት ቢሆንም የፓርቲ ደንብ አልባ፣ የፓርቲ ፕሮግራም አልባ አባልነት የሰማይ ቤት ጁስ ማለት ነው። አይኖርም እንደ ማለት።
ጉባኤ ሳይካሄድ ደንብ፣ ፕሮግራም፣ መሪ ዕቅድ አይፀድቅም። እነኝህ ከሌሉ አባል ብሎ ነገር የለም። በልቅነት የፖለቲካ ድርጅት አይፈጠርም። ፈፅሞ።
#ለመሆኑ እነ አያፍሬ፣
ማለም ይቻላል። ህልመኛ መሪ ስላሉ። አረብ ኢምሬት፣ ዱባይ ህልማቸው ነው። ግን የፓርቲ ምሥረታ የዳንኪራ ምሽት ቤት ምድጃ አይደለም። ህግ አለው። ጠንካራ ሥርዓት አለው፣ ወግ አለው፣ የፖለቲካ ድርጅት ምሥረታ ጤዛነት አይደለም።
#ጥረቱ።
እስከ አሁን በማን ይሁን በማን የተመሠረቱ የፖለቲካ ድርጅቶችን የዶግ አመድ አድርጎ የአጤ አብይን አሻራ መትከል ነው የሽምቅ ውጊያው። መርኽ አልባ የፖለቲካ ድርጅት አይሰነብትም። ሲፈጠር ያረጠ ነው። ለፓርቲ ህይወት ዲስፕሊን ዘቡ ነው።
ለዛውም ከአቶ ልደቱ አያሌው በተቀዳ፣ በተዘረፈ "የመድሎት" ፍልስፍና። ሃቁ ቢያንቃችሁም ዕውነቱ ይህ ነው። ስለዚህ አጋጣሚ እያሸተታችሁ ማጉራቱን ተግ አድርጉት።
* ምራቂ!
"የብልጥግና" አባላትን በሚመለከት አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ። አንድ ባዶ የጭነት መኪና እሰቡት። ቀለሙ ግራጫ እንበለው።
ሁለተኛ የጫነ ቀለሙ ውኃማ እንበለው። የሆነው የውኃማ ጭነት ወደ ግራጫማው ተገለበጠ። የኢህአዴግ 7 ሚሊዮን አባላት እና አካላት ወደ "ብልጥግና" ተዛወሩ። በጅምላ።
ሦስቱ የኢህአዴግ የግንባሩ አባላት እንዳሉ ሲወሰዱ እህት በሚል ሲሾመነሞን የነበረው ገመናም እንዳለ አባሉን ይዞ ተቀላቀለ።
ቤንሻኔጉል ጉምዝ፣ ጋንቤላ፣ ሐረሬ፣ አፋር፣ ሱማሌ። የቀረው የህወሃት ነበር የጦርነቱ ሚስጢር ይህ ነው። ግጥምጥሞሽ።
ፓርቲ ይህን ሂደት አይከተለም። የፓርቲ አመሠራረት የገብያ ውሎ አይደለም እና። ለአባልነት እራሱ #የእጩ አባልነት ጊዜ አለው። አሁን ያሉት ብልጥግናዎች የኢህአዴግ አባላት እና አካላት ናቸው።
አቶ መለስ በአጤ አብይ መተካካት። ሥም ብቻ ነው የተለወጠው። ውልቅልቅ። ሙሩቅሩቅ። ሩጫው የኮፒ ራይት ነው። የሥም ተከላ። ጊዜው ሲደርስ ይናዳል። ለዚህ ነው 50በ60 የመደመር ዳንቴልን #ያረጠ ያልኩት። ያልቦካ ምርጊት።
#ክወና።
ከላይ የዘረዘርኳቸው የመርህ ፕሮሲጀሮች ቅንጣት ታክል የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የህሊና ዳንቴል "ብልፅግና" አያሟላም። ለዚህ ነው እኔ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴን እያልኩ እምጠራቸው።
#ብልፅግና እያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ሲናገሩ ይገርመኛል። ጋዜጠኞችም ይገርሙኛል። መርህ ተኮር ሙግት ከመርህ መነሳት አለበት።
የችግኝ አሻራ አለ፣ ያን መቀበል ይቻላል፣ የፓርክ አሻራም አለ የቀደመን ነቃቅሎ እራስን መኮፈስ እሱም ይሁንልህ ኦሮሙማ ይባል ለዛውም የታሪክ፣ የጥበብ፣ የትውፊት ባለሙያዎች ሳይማከሩ፣ የፓርቲ አመሠራረት ግን እንዳሻህ፣ እንደልብህ ይሁንልህ ማለት እራስን መናድ ነው።
አቬቶ አንድአፍታ ሀተታ አንባቢ ሙግት ካሰኜህ ና እና ግጠመኝ። እኔ።
አይደለም "ብልጥግና የፕሮቴስታንት ኢንፓዬር "ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አለ ብዬ አላምንም። እሱም አቅቶት ወድቆ ስላዬሁት። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
14/12/2020
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ