እርገት ላይ ስለለው ኮሮና - በኢትዮጵያ። #እፍታ። 14.12.2019
እርገት ላይ ስለለው ኮሮና - በኢትዮጵያ።
#እፍታ።
ስለ ኮሮና መከላከል ማሰብ ቅንጦት ይመስለኛል። ከአዕምሮ ከተሰደደ ቆዬ።
#ትርታ - በፋታ።
በሸኜነው ሳምንት እማከብራቸው ዶር ልያ ታደሰ ብቅ ብለው በኮሮና ዙሪያ ያለው ጥንቃቄ ማነስ፣ ማገገሚያ ክፍሎች እዬሞሉ ስለመሆኑ ገልጠዋል። አስፈሪ የሆኑ ጭንቀታቸውን ነግረውናል።
በፈጣሪ ቸርነት እንጂ እንደ ሁሉም ነገር ድብልቅልቅነት የሚተርፍ ነፍስ በኢትዮጵያ ቢኖር የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ካቢኔ ብቻ ነበር። ያው እሳቸው እና ባለቤታቸው የማስክ ሞድም ላይ ናቸውና። ሌላው የደን ተከላው ኮሮናን ሊከላከል እንደሚችል እኮ አዳምጠናል።
ይህም ብቻ ሳይሆን የሰኔው፣ የጥቅምቱ ግርግር ኮሮናን ዌልካም ያለ ፕሮጀክት ነበር።
በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመላ ኦሮምያ ያን ያህል መሬት እዬተደበደበ ማዕት አውርድ ሲባል፣ በርከት ያሉ ወገኖች በገፍ ሲዘርፍ፣ ሲያዘርፍ፣ ሲገድል ሲያስገድል፣ ሲያሳድድ፣ ሲሳዳድ፣ ሲያነድ፣ ሲያወድም፣ ሲነቅል፣ ሲያፈልስ ኮሮና ኢትዮጵያ ውስጥ ተኖ ወይንስ አርጎ ይሆን?
የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፍወርቂን ጉብኝት አስመልክቶ ስለወጣው ህዝብስ ምን እንበለው? ሌሎችንም የድጋፍ ሰልፎችን በገፍ አይተናል፣ ካለ ጥንቃቄ። በተፈጥሮ አደጋ፣ በአንበጣ፣ በጎርፍ በውኃ ሙላት ኢትዮጵያ ስትናጥ ስለቅድመ ጥንቃቄ አጀንዳ ነበርን?
ጦርነቱን አቶ ሴኩትሬ እኛው ጀመርነው ብለውናል። ብዙ ድካም ስላቃለሉ እኔ አመሰግናቸዋለሁ። ዳግሚያ ሽሜ ብያቸዋለሁ። እንዲህ ዘርግፍ ደጎችን ፈጣሪ አያሳጣን። ምርኩዝ ሸላሚዎች ወይንም ባትሪዎች።
#እም።
… ምንም እንኳን የስሜን እዝ ቀሪ ክፍል ቀድሞ በበራሪ ፁሁፍ የሚገደሉት ዝርዝር ደርሶን ነበር፣ ዝግጅቱ ዓመት ሁኖት ነበር ባሉት ልክ የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ጉዳቱን ለመቀነስ ቢያንስ የኮሮናን ቅደመ መሰናዶ አይደለም የቁስ የህሊና የሆነውን ነገር ሳዬው ምንም ነበር።
ቀውሱ የታጨ ነበር። ሊቀንስ የሚገባ ህዝብ እና ትሩፋት አለ። እዛ ፍል ጦርነት መተከል እና ኦሮምያም ቀዝቃዛ ጦርነት።
#ጦርነት ላይ ያለች አገር ስለ ኮሮና ስጋቱ? ኦ!
መሬት ጦር አውርድ ተብሎ ሲደበደብ ባጄ። ሁለት ትዕቢቶች መሸነፍን አንዳቸው መቀበል ተስኗቸው ጦርነት ውስጥ ሲገባ በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር ንፁኃን በገፍ ሲተሙ ለሰከንድ ኮሮና ታስቦ ነበርን?
ከስሜን እዝ ተፈናቅለው ወደ በዬዳ የሄዱ የሠራዊቱ አባላት አይደለም ለኮሮና ለዕለት ልብስ የነበራቸው እንብዛም ናቸው። ድንገተኛው ሱናሜ የበዬዳ፣ የደባርቅ ህዝብ በተለመደው ደግነቱ ሲቀበል ኮሮና ኢትዮጵያ ውስጥ ያረገ ይመስል ነበር።
የጎንደር፣ የወሎ፣ (የአፋር) የትግራይ ሆስፒታሎች ኮሮናን ወይንስ ቁስለኛን ማንን ማስቀደም ነበረባቸው?
ለሎጅስቲክስ የተሠማሩ፣ ለዘገባ የሄዱ ጋዜጠኞች፣ ሁኔታው አስገድዷችው ወደ ጦርነቱ ዘው ያሉት ወጣቶች፣ ገበሬዎች፣ ፋኖዎች፣ ኢብን የልዩ ኃይል አባላት በአዕምሯቸው ውስጥ ኮሮና ስሩዝ ነበር።
አስግቶኝ በዚህ ጉዳይ ብቻ ፅፌ ነበር ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ልዩ ግብረ ኃይል እንዲያደራጅ። ሰሚ የለም። የህዝብ ቁጥር የመቀነስ ፕሮጀክትም ያለ ይመስለኛል ውስጡን ስፈትሸው።
ጦርነቱ ያፈናቀላቸው የአገር ውስጥ እዛው ለዛው ስደተኞች፣ ወደ ውጭ የተሰደዱት 100 ሺህ ሳይደርስ ይቀራልን? እራሱ ሱዳን መቀበሏ የሚደንቅ ነው ስደተኛን።
ለምን ቢባል ከኮሮና ስጋት አንፃር ብዙዎች ደንበራቸውን ዘግተዋልና። ግሪክ ውስጥ ያለው የስደተኛ ካንፕ በኽረ ችግሩም ይኽው ነው።
#ኃላፊነት ከአልቦሽ ሲጋባ።
ኃላፊነት የሚሰማው የክልል ይሁን የማዕከላዊ መንግሥት አስተዳደር ተገዶም ይሁን ወዶ ጦርነት ውስጥ ሲገባ ለዛውም 100 የማይሞሉ ሹማምንትን ለመያዝ ሁለመና ሲገበር፣ ሃግ የሚል የሚቆጣ፣ የሚገስጥ፣ የሚፈራ አንድ ቀንጣ ቅዱስ ጠፍቶ ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ ተፈጠረ። ይህ ሁሉ አሳዛኝ ትራጄዲ ተፈጠረ። አዝናለሁ። እንደ መዝናኛ የቆጠሩት እንደነበሩ ሳይ ሰውነታችን ውስጥ የጎደለ ንጥረ ነገር አለ።
ሠራዊት የአገርም በለው የምንም ወገን ነው። የሰው ልጅ ነው ድሉ እንጂ የተገበረው ድቀት ዕውቅና የለውም። አዝናለሁ።
ሠራዊቱ ወደ አማራ ክልል ሲተም ህዝቡ ሲቀበል፣ ሠራዊቱ ሲበተን ህዝቡ ሲቀበል፣ ትግራይም ሆድ ሆና ስታስተናግድ ኮሮና ኢትዮጵያ ምድር ምን ጥሎት¿¡
አሸነፍኩ እያለ የሚያሽካካው መስቀኛው ቲም ታዬ ከላይ ጀምሬ ላነሳኋቸው ዝርክርክ፣ ዝልግልግ ህይወት ከምን ይመደብ ይሆን ?
ኮሮና ተቀምጦ መላ ኦሮምያ በሞት፣ መላ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሞት፣ ማይካድራ በሞት፣ ትግራይ፣ ኦሮምያ፣ ቤንሻንጉል በመፈናቀል ሲናጡ ኮሮና ኢትዮጵያ ላይ ቅብዕ ቅዱስ ተቀብቶ አርጎ ይሆን?
#ምርጫ እና ቀለጤው የኢትዮጵያ ኮሮና።
ዶር ልያ ታደሰ ትጋት ላይ ነበሩ። ትጋታቸው ተግ ብለው እሳቸው ወደ ጓዳ የገዳ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ወደ አደባባይ የወጣበት መንገድ ትራጀዲ ነበር።
ገና ህሙማን ጥቂት ሳሉ ምርጫ ተራዘመ፣ ሞት ሲጨምር ምርጫ እንደሚኖር ታወጄ። ለምን? የፋክክር ቤት ስለሆነች ኢትዮጵያ።
ህወሃት ኮሮና ምርጫ ለማራዘም ምክንያት አይሆንም ሲል እንደልቡ የሆነ ምርጫ አካሄደ፣ የዓለም የዜና አውታራት ዘገቡብት፣ ያን ያዬ የአብይዝም መንግሥት በሳምንት ውስጥ የተሟላ መሰናዶ አለኝ፣ በዚህ ዓመት ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ ሚዲያ ላይ ሸቀጥ ፈሰሰ። የልጆች እንድርቺ እንድርቺ።
በነገራችን ላይ ማህበረ ኦነግም ምርጫ አልሳተፍም እያሉ ነው ኦነግ እና ኦፌኮ፣ ምክንያታቸው ወጥም ልዩነትም አለው፣ ኦፌኮ ዘፍጥረትን ደምሳሹ አመራር አካሌ እስር ላይ ነው ሲል ኦነግ ደግሞ በጠቅላዩ ጉብኝት አልሸባብ እና ኦነግ ሊደመሰሱ ይገባቸዋል የሚለው አመክንዮ አባት ኦነግን አስከፋ መሰል።
ምንም እንኳን ማስተባበያ ኦነግ ሸኔ ለማለት ነው ተብሎ በአፍ ወለምታ ይስተካከል ቢባልም።
#ቧንቧ ውኃ እንደምን?
ለእኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ መንግሥታዊ ይሁን መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም የቧንቧ ውኃ ማለት ነው። የእኔ የሚለው የሌለው በቻርጅ ብቻ የሚሠራ።
ሲከፍቱት ጠቅላዩ ይከፈታል፣ ሲዘጉት ይዘጋል። ሰብዕዊ መብት ኮሚሽንን አገላለፁ ለጊዜው አይመለከትም።
#ጦርነት + ኮሮና= ምርጫ?
በእርግጫ - በልግጫ - በፍጥጫ - በልጣጭ ? አናውቀውም። ውሳኔው የአንድ ዕጣ ነፍስ ድንጋጌ ነው። የአጤ አብይ ድንጋጌ እንበለው።
ልግጫ - ፍጥጫ - እርግጫ በቀደመው ህወሃት መራሽ የምርጫ ሂደት በዬዕርሱ የሠራሁበት ነው። ደጉ ሳተናው እና ዘሃበሻ ይገኛል። ሥርጉተ ሥላሴ ብላችሁ ብትጎጉሉት ማለት ነው።
#የአሁኑ ደመመን ነው።
አሁን በኦህዴድ መራሹ በጉራጁ ኢህአዴግ ከዛም በባሰ ሁኔታ ነው ኢትዮጵያ ያለችው።
ምርጫው ቢካሄድ በህሊና ኢትዮጵያ በተመሰጠ ዕንባ ውስጥ ሆና ሦስት ሰኔዎችን፣ ሦስት ጥቅምቶችን አስባ የእኔ የምትለው ርዕሰ መዲና አልቦሽ ይሆናል። መራራ ነው። ግን ህሊና ይለማመደው።
የአዲስ አበባን የምርጫ ሁኔታ የሚወስነው፣ ዕቃው የሚከፋፋለው በኦሮምያ ክልል መንፈስ ልክ ነው።
ይህ ፋክት ነው። አዲስ አበባ ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ድርጅት፣ ግለሠብ በኦሮምያ መሥፈርት ልክ ነው። ይህን አምኖ መቀበል ግድ ይላል።
ሰነዳዊ አይደለም ግን አዲስ አበባ ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ በኦሮምያ ሥር ናት።
ኢትዮጵያ በምርጫ ታሪኳ አይታው የማታውቅ፣ አፍሪካም ገጥሟት የማያውቅ የርዕሰ መዲና የባለቤትነት ባለ እርስትነቷን ተነጥቃ፣ ተቀምታ በአልቦሽ የምታካሂደው ምርጫ ይሆናል ከተካሄደ 2013 ምርጫ። የትግራይን ዝንቅ መንፈስ ትቼ ማለት ነው።
#ክወና።
#የ2013 ምርጫ እና ዕጣው።
ዕጣ በመጣጣል ላይ ነው። ከዚህ በላይ መሄድ አያስፈልገኝም። ቅኔ ነው ልባሞች ፍቱት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/12/2020
ሰው መሆን ለሰማዩም ለምድሩም ህግጋት መገዛት ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ