ስክነት የሚጠይቁ አመክንዮወች አሉ ለአማራ ፖለቲካ። መርገብገብ አያስፈልግም። ችኮላም!

 

ስክነት የሚጠይቁ አመክንዮወች አሉ ለአማራ ፖለቲካ። መርገብገብ አያስፈልግም። ችኮላም!
ትርትትሩ የኦነግ ፖለቲካ ሊያሸብረው ወይንም በቀውስ በጀት ሊያሰምጠው አይገባም። በስክነት፣ በመደማመጥ በለመደበት የዊዝደም ልቅና መራመድ ይጠይቃል።
እርግጥ ነው መሪ የለውም። ነገር ግን ችግሩ በራሱ ጊዜ መሪ ይፈጥራል ጠብቁት። ብስጭት አያስፈልግም። የሚስፈልገው አይደለም የድምፅ ምቱን አዬሩን እራሱን ማድመጥ።
አቅምን አላግባብ አለማባከን። በማይረቡ አቲካራዋች ጊዜን አለማጥፋት። አማራነትን መሰነቅ። ውስጥነትን በውስጥነት ማዋሃድ። መሆን በመሆን ማስተናበር።
ከተራ ግርግር መውጣት። ለፈንጠዝያ ጊዜ አለመስጠት። በረጅሙ ማሰብ። ለዘለቄታ መሥራት። ለታሪካችን፣ ለትውፊታችን ቀናዕይ መሆን። "የቤትህ ቅናት በላኝ" ያለውን የንጉሥ ዳዊትን ቃለ ህይወት መመስጠር።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/12/2021
አማራ ሆይ! የደምህ ዋጋ ታሪክህን አሳልፈህ አለመስጠት ነው።No photo description available.
 
 
 No photo description available.No photo description available.No photo description available.
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።