ከማን የተማሩትን፨ የኦሮሞ ፖለቲካን ጎለጎታ እየላኩት ነው፨ "#ሸለፈታም።" የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አዛዥ ጠቅላይ ሚር #አብይ #አህመድ። "#ማበሳበስ። ስድ አደግ" ጄኒራል #ብርኃኑ #ጁላ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም። ሁለት ቁንጮወች ወደ ጅራትነት አሰኛቸው።
ከማን የተማሩትን፨ የኦሮሞ ፖለቲካን ጎለጎታ እየላኩት ነው፨
#በር እኔን ስለመግለጽ።
ፊልዴም አይደለም። የማይመለከተኝን ዘርፍ አልነካካውም። መከላከያን በሚመለከት ዝምታዬ ከመቃብር የሚከብደውም ለዛ ነው። ኢኮኖሚ ዘርፍንም ትውር እማልልበትም በዚህው ሎጅክ ነው። ሁሉም ዘርፍ ባለሙያ፤ ኤክስፐርት ፈላስፋም አለውና።
#የማህበረ ኦነግ ካሪክለም ጠያፍ ቃላትን መዳፈር።
የማህበረ ኦነግ የአይዲኦሎጂ ካሪክለም ግን ይገርመኛል። ማህበረ ኦነግ በፖለቲካው ዘርፍ በብሄራዊ፤ በአህጉራችን በእማማ አፍሪካ፤ በምዕራብውያን እና በአውሮፓውያኑ እንደዚህ ዘመንም ከፎቅ የተፈጠፈጠበት ዘመን ያለ አይመስለኝም። በታሪኩ ኦነግ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥት #አራጦ እንዲመራ፤ በትረ ሥልጣኑም ያለ ከልካይ ተሰጥቶት በወርደ ጠባቡ ቁመናው ኢትዮጵያን መምራት ተስኖት በዚህ መልክ ወድቆ ማዬት ጊዜ ራዲዮሎጂነቱን አስመስክሯል።
ዛሬ ስለ አጤ ጊዜ ቅኔነትም ልከልለት። አወን! ጊዜ #ቅኔም ነው። አጤ ቅኔ ቅኔውን በተሰጠው ልክ እንዲህም ይዘርፈዋል። ለቅኔ ማህበረ ኦነግ ስለማይችሉት ሲዋጉት // ሲወጉትም በበታችነት ስሜት ሲናውዙም፤ ኮሽ ባለ ቁጥር ሲደነጋግጡ እዚህ ደርሰዋል። በሌሉበት ቦታ ሁሉ መልካሙን ነገር ሁሉ በፀርነት ፈርጀው ሲፈሩትም፤ ሲመነጥሩትም ኑረዋል። ታሪክ በቀደመ ህዝብ፤ አገርም በቀደም ህዝብ ዊዝደም ይሠራል።
ኢትዮጵያ አንጡራ ጠላቱ የሆነው ማህበረ ኦነግ በእኛ ያልተመጣጠነ የታማኝነት ልዩሥጦታ በስል በሱሴ ስለገቡ፤ ዕምነት ብስለት አናሳነት ዕድልን ጠቅልሎ ሰጥቶ በጠላት እጅ ኢትዮጵያ እንደገባች ይሰማኛል። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ማስተዋል ነስቶን፦ ያን ሁሉ ድካማችን አባክነን፡ በትነን ኦነግ ሠራሽ ሊቃናት ታምነው #ቅኒት ኢትዮጵያን እንዲበልቷት አሳልፈን ለጲላጦስ የሰጠነው እኛው እራሳችን ነን።
"አያያዙን አይተው ሸክሙን ይቀሙታል" የሚለው የጎንደሮች ቅኔ የተሰወረባቸውም በፍርሻ ላይ አብረው ፌስታውን ሲያስነኩትም ባጅተዋል። ከዚህ ያላከለኝን አምላኬ አመሰግነዋለሁኝ። ከኢንጂነር ስመኜው በቀለ ግድያ ቅጽበት በኋላ ቅንጣት አቅም አላቀመስኩትም ለኦህዲዳዊው ኦነግ አመራር። ፈጣሪ ይመስገን። አሜን።
አማርኛ ቋንቋ ውስጥ እጅግ ፀያፍ ቃላት አሉ። ህልው ሆነው ግን በማስተዋል ሊገሩ፤ ሊረሱም የሚገቡ፤ ልንጠቅምባቸው የማይገቡ። ከዚህ በላይ ሁሉም ሙያ የራሱ የሆነ የአነጋገር ኤቲክስ አለው። በመሪነትም ለመሪነት የሚገቡ እና የማይገቡ፤ ልኩ የሆኑ እና ልኩ ያልሆኑ አገላለፆች አሉ። አገላለጽ ፕሮቶኮል አለው። መሪነት መመረጥ ነው። መሪነት ቁጥብነትን በቅጡ ማስተዳደር ነው። መሪነት ሮል ሞዴልነት ነው። መሪነት ትውልዳዊነትም ነው። መሪነት የትምህርት ተቋምነትም ነው። መሪነት ጨዋነት ጭምትነትም ነው። መሪነት ታላቅ ኃላፊነትን እና ተጠያቂነትን በመስተጋብር ያዋሃደ ትሁት ሙያም ነው ለእኔ።
መሪነት መርኃዊነትም ነው። መሪነት እራስን ገስፆ መገኜትም ነው። መሪነት #መታረምን መቀበልም ነው። መሪነት አገልጋይነትም ነው። መሪነት መከበርን ማክበርም ነው። መሪነት የአገርን ሉዓላዊነት ሞገስ እና ማዕረግን በአኗኗር በአገላለጽ፤ በአቋቋም፤ በአረማመድ፤ በአነጋገር፤ በሁለመና #ላቂያነትን ማሳዬትም ነው። መሪነት ላቂያነትም ነው።
ፕሮቶኮል እርሙ የሆነው ልቁ የኦሮሙማ ኦነጋዊ አመራር መታበዩም ተችሎ፤ ጭፍጨፋውም ተችሎ፤ መዝለግለጉ ተችሎ፤ እራሱን ለመግለጽ ታርሞ እና ታርቆ መቅረብ የተሳነው የዘመን ቁልቁሊት ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ባልተገራ ንግግር መሪነት?? ኦ! አምላኬ። ይህ አንደበት ከውጩ ማህበረሰብ ጋር እንደምን ሲኳኳን ባጄ???
የኢትዮጵያን የአዬር ኃይል በዓል አከባበር አስመልክቶ ቅድመ መሰናዶ እና የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በሁለት ክፍል ያብራሩት ጄኒራል ብርኃኑ ጁላ በአማራ ፖለቲካ ኡራኖስ ላይ እንደባጁ ተረድቻለሁኝ። ብናኝዕውቀትም የላቸውም። ለህወሃት በትረ ሥልጣን ሽኝትም ሥር ነቀል ምክንያታዊው ተጋድሎ እሳቸውን ለዚህ ቁንጮነት እንደ አበቃም አያውቁም። ባልተያዬዘ እና እርስ በእርሱ በሚተረማመስ የፖለቲካ አቅም ድንኳን ውስጥ እንደሚገኙ ብቻ ሳይሆን ለክህሎታቸው እራሳቸውን ፈተና ላይ ያስቀመጡበትን ንግግር ወደ ሦስት ጊዜ አዳመጥኩት። ገመና ብለው ይሻላል።
የሚገርመው ከሦስት ጊዜ ላላነሰ "#ማበሳበስ" የሚል ቃል ተጠቅመዋል። አንድ አገሮች በሽሚያ ኑልን እያሉ የሚፎካከሩበት የጦር ኢታማጆር ሹም፤ በዚህ እጅግ ፀያፍ ቃል ተሽሞንሙኖ ሲቀርብ ከማዬት በላይ ለኦሮሞ ፖለቲካ ዕዳ ያለ አይመስለኝም። ያቃለሉት፤ የተዘባበቱበት፤ ያጣጣሉት፤ በመስቃ ያንቆጠቆጡት፤ ያዋረዱት ማህበረሰብ እና የአማራ ፖለቲካ፤ ስለማያውቁን አለማወቃቸውን አመሳጥረውልናል። መልስም መስጠት አልፈልግም።
እኔን የሚጨንቀኝ ትውልዱ ከእንዲህ ዓይነት አቅልም፤ አደብም፤ ጨዋነትም፤ፕሮቶኮል ከተዛነፈበት የጦር ኢታማጆር ሹም #ሰብዕና ምን ይማራል ነው ጉዳዬ። አገርም ህዝብም "ማበሳበስ" በሚል ቃል ሊጠቀስ፤ ሊብራራ ከቶም አይገባም። ችግሩ ያለልኩ የተሰፋ ሽብሽቦ ሆነ እና ጋዳ ሆነ እንጂ።
#የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥስ???
ሁለተኛው ጉዳዬ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ከሆኑት ሌኮ አብይ አህመድ አገላለጽ ነው። "#ሸለፈታም።" አድራሻው ለማን ይሆን የሚለው የዕለቱ አጀንዳዬ አይደለም። "#ሸለፈታም።" ቃሉ በጎንደሬወች አማርኛ ያልተገረዘ ማለት ነው።
#ስለ መገረዝ በስሱ ……
እኔ ባደግኩበት ጎንደር ሴቶችም ወንዶችም ይገረዛሉ። በሴቶች በኩል #የማርያም #ግርዝ የሚባል አለ። የማርያም ግርዝ ሴት ልጆች አይገረዙም። በተረፈ ግን ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችም ጎንደር ይገረዛሉ። እዚህም ሲዊዝ ሻፍሃውዘን በሚባል ክልል ባለ ሆስፒታል መገረዝ ለሚፈልጉ ተባዕት ወንዶች ግርዛት እንደሚደረግላቸው አውቃለሁኝ።
መገረዝ ለሴቶች የባህል ድክመት ተደርጎ ዘመቻ እዬተደረገበትም እንዳለም አውቃለሁኝ። ግርዛት ከሃይማኖት ጋር የተሳሰረ ዶግማዊ ግዴታ እንዳለበትም ይታወቃል። ይህን ከዚህው ላይ እረፍት ውሰድ ብዬ ላቁመው።
#ልዑለ ፒኮኩ መሪ። ፒኮክ ሊቀ መላዕክት ተደርጎ በአማኞች ዘንድ ወደ ኢራቅ ይወሰዳል። እዛም ወስደውናል።
የሆነ ሆኖ ፦፦፦፦ ሌኮ አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። የዓለም ሰላም ሎሬትም ተሸላሚም ናቸው። ትዝ አላላቸውም ይህን ንግግር ሲያደርጉ። እጅግ በታበዬ ጉልበታም አገላለጽ ነበር ያቀረቡት። ለዛውም በውራጅ የአዬር ላይ ትርኢት። ወዳጅነታቸው ምክንያታዊ ነው። ዓላማ እና ግብ አለው። አይደለም እኛ ዲፕሎማሲው ማህበረሰብም ተረድቶታል።
ይህም ይሁን የታላቋ አገር ኢትዮጵያ መሪ ጭራሽ በመሪ አንደበት አደባባይ ቀርቶ በህይወት ዘመኑ ከአንደበቱ ጋር ሊዛመድ የማይገባ ቃል አውጥቶ በድፍረት "#ሸለፈታም" ሲሉ ማድመጥ ይሰቀጥጣል። መገረዝ ባህሉ ያልሆነ የትኛው ማህበረሰብ ይሆን??? አማራ??? እእ። ባህሉ አይደለም። በሌላ በኩል የብልጽግና ወንጌላቸውም ይህን ፀያፍ አገላለጽ ሲጠቀሙ እንደ ፓስተርነታቸው፤ ቀዳማዊ እመቤት ዘማሪ ወሮ ዝናሽ ታያቸውም ይህን ያልታረመ አገላለጽ ቁጭ ብለው እያዳመጡ ሲያጨበጭቡ ሳይ ኃይማኖቱም መሪነቱም አልቦሽ ሆኖ ታዬኝ። መለሞጥ።
ለነገሩ ሥርዓት? ሞራል? ኤቲክስ? ትውፊት? የመንግሥት አመሰራረት ሂደት እና ሙያው? መሪነት እና ተመሪነት በምናብ መሆኑ ከወላጆቻቸው ከአቶ ሌንጮ ለታ እና ከዶር ዲማ ነጉ የተማሩት ስለሆነ ያንኑ ተከትለው መንጎዳቸው አይደንቅም። አያስደነግጥም። ዘመን በመጣ ቁጥር ካፖርት እያስተካከሉ የኢትዮጵያን የተስፋ ጉዞ ያደናቀፋ እንቅፋቶች ባሉበት ይህን ማዬት ግድ ሆኗል።
ልጅ አሳዳጊውን ይመስላልና። ብዙም የማህበረ - ተንታኞቻቸው፤ የቤተ ኦነግ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂወች፤ ፈለገ ሌንጮወች ኦነግ ገብ ሚዲያወች ከጨዋዊ አስተምህሮ ጋር ተፋተው ነው የሚፈጠሩት። የታረመ የታረቀ ሥርዓት ያለው አይቼም፤ አድምጬም አላውቅም። ስሜታዊነቱም የጉድ ነው።
#ቢያንስ……
ያ ግርማው ሰንደቅ በነበረው ባዕት፤ የአፍሪካ አንከር፤ የጥቁር ህዝብ የፊደል ገበታ የሆነችን አገር ኢትዮጵያ፤ ካለ ቦታው፤ ካለ ባዕቱ ጥቁር አንበሳ ተገኝቶ አሳሩን አዬ። አሳሩንም በላ። በአፍሪካ የመጀመሪያውን #ሽምቅ ውጊያ ያስተማረው ጥቁር አንበሳ ካለልኩ ተቀርቅሮ ቅስሙ እንዲህ ተሰበረ። መሪነት ቁሞ ቀር ሆነ ……
ክብረቶቼ እንዴት ናችሁልኝ??? አጤ ፌቡ ጊዜዬን ቆጥቦ እያገዘኝ ነው። የዛሬ አራት ዓመት የፃፍኩትን ስለሚያመጣ እንዳይበዛ በማለት ነው እምታገሰው እንጂ። መፃፍ ለእኔ ትምክህት አይደለም ሥጦታውን ማክበር ነውና የቧንቧ ውኃ ያህል ቀሊል ጉዳይ ነው። ፍጥረተ ነገሬ ለመፃፍ የተፈጠረም ነው። እኔ እራሴ መፃፍም ነኝ። በጣም ብዙ ፁሁፍ ነው ያለው። ግን በዚህ በባከነ ዘመን የሰከነ ትውልድ ለመፍጠር መትጋት ሲገባን ዝምታን ንገሥ ግድ ሆነ። በሌሎችም ያልተረጋጉ ፖለቲከኞች ሂደት ተደሞ ተመረጠ።
#ምክሬ።
አደራ መድረክ ላይ ያላችሁ ወገኖቼ ከዚህ መሰል ጠያፍ አገላለዝ ጋር እንዳትዛመዱ። ብዙ መናገርም ነው ገደል የሆነው። አንድ የአገር የጦር ኃይሎች ኢታማጆር ሹም እንደምን ከሁለት ሰዓት በላይ ተራኪ ይሆናል? ኮሚኒኬሽኑ ሲመጣም ያው የታሠረ አንደበት፤ ክፍለ ጦር ላይ ሲወረድም እንዲሁ ……አንድ የአገር መሪስ የማይክ ድንኳን ሰባሪነት 365 ቀናት ሙሉ ይሆናልን? ሁልጊዜ ንግግር ብቻ …… በዚህ መሃልስ የሚያርቅ አንድ ኦነጋዊ አባል እንደምን ወና ይሁን?
*****እርገት ይሁን በየኔታ ሥንኛት ………
እሳት ወይ አበባ መድብለ ግጥም መግቢያውን ብቻ ገጽ 139 ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን እንደፃፈው
"እና፥ እንደ እኔ እና እንዳአንቺው፥ የውበት ዓይኑን የታወረ
እግረ ሕሊናው የከረረ፥
ባህረ- ሃሳቡን ያልታደለ
የውበት ዓይኑ የሰለለ
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥ አበባ እኮ አይደለም አለ።
ያልታደለ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
መሸቢያ ምሽት፤ ሸበላ ሌሊት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/12/2023
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ