እልል በል አማራ!
እልል በል አማራ! ከሥርጉተ ሥላሴ 10.06.2010 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „እሱም ጥበብንና ምክርን ይገልጥለታል፣ የተሠወረውን ይገልጥ ዘንድ ያሳስበዋል።“ („መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፯“) አንተ እናት ሆዱ እግዜሩን አማኙ፣ አንተ አንጀት አራሹ ትህትናን ተናኙ፣ አንተ ቅን ወተቱ ፍቅርነን ተመኙ፣ ስትሞላ የሰው ጓዳ ስትድር ጠጋኙ፣ አንተኑን እራስተህ ለሌሎች ሥንኙ ። እልል በል አማራ አንተ መከረኛ፣ እልል በል አማራ አንተ አሳረኛ፣ እልል በል አማራ እዬሞትክ ተረኛ፣ አንተ አናጋች በመሆን ለጋስ ተረብኝ፣ አልቀህ ባታልቅለት ለዘመን ወረተኛ፣ ቀንህ ጆሮ ገዛ የአብን ሁነኛ! እኔስ እልሃለሁ ከልቤ ታድሜ፣ እኔስ እልህለሁ ከውስጤ አስቀምጬ፣ እኔስ እልሃለሁ ድምጼነን ሰጥቼ፣ ከእንግዲህ ጅልነት አውልቀህ ጣል ብዬ። አንተ ገራገሩ የዘመናት ትንግርት፣ አንተ ብሩኽ ማዕልት የመቻል ትዕይንት፣ አንተ ግማደኛ የእንትዬ ትፍስህት፣ ስትጋፋ የኖርክ የደሙ ግብረኛ፣ ለባድማ ትውስት፣ ምን አትርፈህ ከቶ ከማገዶ ትርሲት? መሸከም ብቻ እንጂ የዕንባን መፈለጥ። አልል በል አማራ ደስ ይበልህ ከቶ፣ አቅምህን ብልሃትህ ሁሉነን አካቶ፣ የህልውና አብራክ መኖርህ ታክቶ፣ በብርሃና አገር ጨለማህ በርክቶ፣ የለህምም ተብለህ በእሬትም ተቦክቶ፣ ሃምሌ 5 መጣልህ የድል ብሥራት ተግቶ። እልል በል አማራ አንተ የማዳን ቀኑ፣ እልል በል አማራ አንተ የቀደምት - ፊ