እናት የክት እና የዘወትር ልጅ የላትም ...
ሾጣጣ። „ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 02.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ሾጤ - ሞጤ - ሽም ጤ - ሾጣጤ - ሞጣጤ - ሞጥሟጤ። ሁሎችም ቃሎች ናቸው። ሁሎችም እኩል መብት እና ግዴታ አለባቸው። ሁሎችም የአማርኛ ቋንቋ አባልተኞች ሽሙንሙኖች፤ ሸባላዎች፤ ሸንቃጣዎች ናቸው። ሁሎችም የስዋሰው ቤተኞች ናቸው። ሁሎችም መነሻቸው ከአማርኛ ፊደላት ነው። ሁሎችም ባለድምጽ፤ ባለ ቃና፤ ባለ ደንብ፤ ባለ ጌጥ፤ ባለ ዘለበታዊ ምት፤ ባላ ዜማ ናቸው። እኩል ናቸው ማለት ነው። እኩልነት እንዲህ ሲገልጥ የልብ ያደርሳል። ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ቢሆን ምኞቴ ነው። በመኖር እና በመኗኗር መሃከል ግን መኖር ለሁሉ ተፈጠረ፤ ግን ለሁሉ ለመሆን አቅመ ቢስ ነው። ስለሆነም መኖር ወይ እረኛ ነው ወይ ደግሞ የታገተ ነው። ወይ ደግሞ ዲዳ ነው ወይ ደግሞ ሰውር ብቻ። „አይዋ መኖር“ ተብሎ ሲጠራ „አለሁ ለሁሉም“ ሲል ይደመጣል፤ አንዱን ሲያንጠለጥል አንዱን ሲያፈርጥ አንዱን ሲካለ ሌለውን ሲከውን፤ አንዱን ሲያቆምስ ሌላውን ሲያሰምጥ ብቻ አለሁኝ፤ አኗኗርኩኝ፤ ተኖርኛ ጋር ሆንኩኝ ይለናል ወገኛ በሉት /// አሁም ማን ይሙት አይዋ መኖር አለሁኝ ለሁሉ፤ ሁለማንም ሆንኩኝ ሊል ነውን? አብሶ ለእጣ የለሾች ባለሾጣጣ ዕጣ ፈንታዎች አዳብለኳቸው ቢል ይመረጣል። አይዋ መኖር ግድዬለሽ ነው። አንዱን ሲያገዝፍ ወይንም ሲያስገዝፍ ሌላውን ደግሞ አጫጭቶ ሲያከስም ወይንም ሲያስተንን፤ አንዱን ባለዝናር ሲያደርግ እና አኮፍሶ ሲያስጀግን ሌላውን ትጥቅ አልቦሽ አድርጎ በዳዴ አንበርክኮ ሲያስኬደው አኗናርኩት፤ ከእኔ ወዲያ እኩልነት እና ነፃነት አዳይ ላስር ብሎ