ሥርዓት አልበኝነት ክብር ሳይሆን ውርዴትም ውርዴም ነው።
ጨካኝነት ወደ እንሰሳነት የመቀዬር ዋዜማ ነው። „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትነ የክርስቶስ ብርሃን ረድኤቱ አልተገለጠልንም፤ ክርስቶስም ለኛ አልተወለደልንም።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መቅድም። በምንም ሁኔታ ጭካኔ ዓይን ሊሰጠው አይገባም። በምንም መስፈረት አረመኔነትን ዝም ልንለው አይገባም። ወንጀልን ወንጀል ስለመሆኑ ልናወግዘው እንጂ ልንከባከበው ወይንም ግርዶሽ ልንሰራበት አይገባም። ሰባዊነት ነው ሰውን 'ሰው' የሚአሰኘው። የሚያደርገውም። ርህርህና ነው ሰው የሚያሰኘው። አዘኔታ ነው ሰው የሚያሰኛው። የሰው ልጅ ከርህርህና፤ ከአዘኔታ ወጥቶ ጭካኔ መሪው ካደረገ ያ ሰው ወደ እንሰሳነት ተለወጧል ማለት ነው። ከአዕምሮውም የጎደለ ነገር አለ ማለት ነው። እንደ ሰው ማሰብ ከልተቻለ ወደ እንሰሳነት የመለወጥ መለያነት ነው። ሰው መሆን ማለት እኮ ከእንሰሳ ዓለም መለዬት ማለት ነው። በሌላ በኩል እናት የምትባል ልዩ ፍጥረት አለች። ሁልጊዜ እናት ልጇ ጎልማሳ ሆነ አዛውንት ልጇ ለእሷ ሁልጊዜ እምታዬው ልክ እንደ ህጻን ነው። እናት አብሶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ባላባራ የዘመናት ጦርነት የልጅ ብርንዶ አቅራቢ ናት። መፍትሄ ለሌለው ማናቸውም በትረ ስልጣን ልጇኝ ስትገብር ኖራለች የኢትዮጵያ እናት። እናት የኢትዮጵያ እናት እንጨት ለቅማ ሽጣ፤ ኩበት ለቅማ ሽጣ፤ እንጀራ ጋግራ ሽጣ፤ በቀን ሰራተኝነት ተቅጣራ ላቧን አንጠፍጥፋ፤ የሰው ፊት ገርፏት ወጥታ ወርዳ፤ የረባ ልብስ ሳይኖራት፤ የረባ የለማ የጣመ ሳትመገብ፤ አንጀቷን አስራ፤ ሙሉ ቀን ስትባትል ውላ ስትባትል አድራ፤ ዓመት ይዞ እስከ አመት በታከተ እድል ፍዳዋን