ሥነ ግጥም።
„አቤቱ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አምጠኝም።
ችግረኛ እና ምስኪን ነኝና።“
መዝሙር ምዕራፍ ፹፭ ቁጥር ፩
ሥርጉተ©ሥላሴ
28.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
መኖር ስንክሳሩ
ሲንር እና ሲከር
ሲለዝብ ሲወይብ
ጥንዝል አቅፎ ሲዞር
ሲያዝል ሲያደናብር
አሉት አሉ መኖር? መኖር ስንክሳሩ
መራራ ስንቅ ሲድር
ሳቅንን ሲያበርር
ተስፋነን ሲቀብር
እንዲህ ሲያደናግር /// ሲያጨማትር
ጥርቅም - ጥንቅር፤ ሲድር
„እኔን“ ሲያጣጥር፤ ሲያሳጥር
ቋሳነን ሲሸርብ
ተሰፋን ሲሰነጥር
ጨለማ ሲያስጨፍር
እኔን ሲያኮማትር
እኔን ሲጠዘጥዝ
አሉት አሉ መኖር?
·
ተጻፈ የካቲት 12 ቀን 2002 ዓም
·
ተስፋ መጽሐፌ ላይ ለህትም የበቃ።
·
እርዕሱ መኖር ስንክሳሩ።
የኔዎ ኑሩልኝ።መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ