ትእግስት ሲያልቅ እንዲህ ፍቅር ይሰደዳል። አማራ አምሯል!
„በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽው፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም።“ (ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫)
23.12.2016
(ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ)
ማን ሲተኛ!
መነሻ ጎንደር የአማራ ተጋድሎ ህሊና!
የአማራ ማንነት ተጋድሎ ሰብል!
ገድለ የአማራ ተጋድሎ!
የሐምሌ አቦዬ ገደል ዛሬን እንዲህ አሳመረው!
28.10.2018
የአማራ ተጋድሎ ነባቢት ባህርዳር!
ዛሬ እንዲህ ...
በኮዳ ሽንት የተረከፈከፈበት ወልድያ ዛሬን
እንዲህ በበቃን እስዋበው።
ቀንበር ተሸካማዊው ደሴ፤
የመከራ ቤተኛው ደሴ።
ተገላዩ ደብረብርሃን!
ዬዬዘመኑ አሳር መመኮሪያ ጎንደር!
ፊት የተነሳው ሸዋ!
አማራነት ጌጥ ነው!
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አትቀመሽ ኃይለኛ ነሽ ——ሽ
አትጠጪ መራራ ነሽ፣
አትዋጭም ጎምዛዛ ነሽ፣
ዕውነት ደፋር ካላገኘሽ
ቃና ዬለሽ ትሆኛ-ለሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽ-ሽሽሽሽሽ ….
· ኣዲሶቹ ፎቶዎች ከዘሀባሻ እና ከኢትዮጵያ ሪጂስተር/ ሳተናው የተወሰደ ነው።
ዕውነት ተሸንፋ አታውቅም – ዬምታሸንፈው በአደባባይ በገላጣ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ሰንበት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ