የፊደላት ለዛ /ሥነ ግጥም/

„የባሪያቱን ነፍስ ደስ አሰኛት፤
አቤቱ ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁና።“

መዝሙር ምዕራፍ ፹፭ ቁጥር ፬
ሥርጉተ©ሥላሴ
28.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
                     
ምላስ - በሩህ
       ይ .... ደላላል።
አፍ - በህይወት
       ይ .... ንጋግዳል።
ዘመን - በዕብለት
       ያ .... ተራርፋል።
እፍኝ - በህዝብ
       ይ ..... ቀላልዳል።
ጭብጥ - ነሺ
       ጥጋብ ይላል።
እርስ - በእርሱ
       ይ .... ማማል።
እርስ - በእርሱ
       ይ .... ቃረናል።
መላው ሁሉ
       ይ .... ወላልቃል።
ትርምስምሱ
       ያኔ ያልቃል።
ዕውነት በጊዜው
       ይ .... ደምቃል።

·         ሥጦታ ... ዕውነት ህይወታቸው ለሆነ ወገኖቼ በሙሉ።
·         ተስፋ መጽሐፍ ለህትምት የበቃ። 1985 ዓ.ም ድል ገብያ ገብርኤል -
·         አዲስ አበባእርእስ ጭብጥ ነሺ።
·          
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ሰንበት ቸር ወሬ ያሰማን ፈጣሪያችን።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።