መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም።
መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም። „የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤ ፈርኦንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቁርናን ሆነች።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ዛሬ ጎልጉል ድህረ ገጽ ገብቼ ነበር። አንድ ጹሑፍ አገኘሁ እና ቀልቤን ስለሳበው አነበብኩት። እኔ ጀርመን ላይ አቶ ሺመልስ አብዲሳ ሲገኙ በምን አግባብ ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር። ስለ አቶ ሺመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት ሃላፊ ስለመሆናቸው በፎቶ የተደገፈ ዘገባ ነበር ጉግል ላይ ያገኘሁት። ካወጡት አስተያዬቴንም ከሥር ጽፌበታለሁኝ። http://www.goolgule.com/shimeles-abdissa/ ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ / ቤት ኃላፊ ለእኔ እጅግ አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ በዛ ወጀብ በበዛበት ጊዜ በጠ/ሚር አብይ እጩነት አቅም ጎን በመሆን ምስክርነት የሰጡ አንድ የኦህዴድ/ አዴፓ ሊሂቅ ቢኖሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ ብቻ ነበሩ። ለቦታውም ምጥን ያለ፤ ክውን ያለ መረጃ በመስጠት እረገድ አቅማቸው አዬር ላይ አንቱ ነበር። አሁን የት እንደ ገቡ አላውቅም። የሆነ ሆኖ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ውስጣቸው ከአቶ አዲሱ አረጋ የተለዬ አቋም እና ምልክታ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ስጋትም ተስፋም ሁለቱም በእኔ ቦታ የላቸውም ። ጊዜ የሚሰጠውን መረጃ ከማድመጥ ውጪ ማድመቅም ማጉላትም ማንኳሰስም በበቃኝ ተከውኗል። ብቻ ያው ኦህዴድ/ ኦዴፓ አንዱን አምጥቶ ሌላውን ቢሸኝ፤ አንዱን ሸኝቶ ሌላውን ቢያመጣ ያው የኦነጋውያን መንፈስ ተጽዕኖ ይለቀዋል ለማለት አይደፈርም። ጊዜ እዬጠበቁ የወጡ ዕውነቶች አሁን ከሆነ ሰብሰብ እንድንል ድርብ እና ድርጁ መል