የዘመን ልቅ መንገድ።

የጥገናዊ ለወጡ ውጥንቅጥ
የዘመን ልቅ መንገድ ፈተና።
„በሰው ተፈጥሮ ያለ ሞትን መጠራጠር ፅኑ ነው። 
ከናታቸው ሆድ ከተወለዱት ጀምሮ በሁሉ እናት
 በመቃብር ሆድ እስኪቀበሩድረስ በአዳም ልጆች
 ላይ የከበደ ሞት አለ።“

መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 07.112018
ጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ይህን የጥገናዊ ለወጥ ዝንባሌ የዛሬ ዓመት ደግፌ መፃፍ ስጀምር ዛሬ በዚህ መልኩ ይገኛል ብሎ ብዙ ሰው አላሰበውም ነበር። መልካሙን ነገር ድጠን በትችት ላይ ስለምንባዝን ነው እንጂ ኢትዮጵያ በዘመኗ እኛ ላለንበት ትውልድ በአዎንታዊነት እንዲዚህ ዓመት የዓለም ሚዲያ አመደኛ ሆኗ አታውቅም ነበር። ሐሴታችንም በውነቱ ልክ አልነበረውም። እኔ በግሌ ብዙ ደስታዎችን አግኝቻለሁኝ። 

ቅድስት ኦርተዶክስ ተዋህዱ አህታዊነት ራሱ ገድል ነው። ሁለገብ ውጤቶቹም ህልም የሚመስሉ ነበሩ። ጉልበታም እና ጥበባዊ አቅሙም የሚታመን አልነበረም። ከዬት ተሰጠን እንዲህ ዓይነት ምርቃት ያሰባለ ነበር። ያሰበለም ነበር። 

በሌላ በኩል ያው አሉ ለመባል ብቻ ጥቂት ሰዎች ሥማቸውን ጎላ አድርገው ሲያስጠሩ የነበሩትም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባልነትም አብዛኞቹ እጃችሁ ከምን ሲባል ባዶ እጃቸውን ብቻ አገር ቤት እንደ ገቡ ይታወቃል። ፉከራው ቀረርቶው ማሰናከሉ ግን ሞገድ ላይ የነበረው ጉጉስ የብራና ቋቶች ይመሰክራሉ። ዛሬም አገር ገብተው ቀን ለውጡን መደገፍ ማታ በመናድ ላይ ሲታትሩ የተገኘው ብልጭታ በመጉሸት እና ተስፋ በመቀልበስ ጣረሞት ላይ ይገኛል።

ብሄራዊ ሃላፊነቱን የተረከበው ኦህዴድ /አዴፓ በያዘው ጥንካሬ በእርጋታ መጓዝ ሲገባው በአማካሪ ስስነት፤ በራሱ ውስጥ የተፈጠረው የጦፈ ቅናት አድማ የተፈጠረው ስንጥቅ እና ትርትር አሁን የጥገናው ለውጥ መዳፉ ውስጥ ያለውን የፍቅር የተሰፋነት፤ የመታመን መክሊቱ ሁሉ በራሱ ላይ አደብ አጥቶ የወሰዳቸው እርምጃዎች በሁሉም ቦታ ቀዳዳዎችን እንዲሰፉ፤ ክፈተቶች ከአቅም ውጭ እንዲሆኑ አድርጎለታል።

በትናንትናው የፓርላማ ውሎ ባልተለመደ ሁኔታ የፓርላማ አባላት ሙግት ጠንቶ እንደ ዋለ ዘሃበሻ ዘግቦ አንብቤያለሁኝ። አዳምጫለሁኝ። እጩዎችንም አሻም ብሎ መሞገቱ ተደምጧል። ለመልካም ከሆነ እሰዬው ነው። የራስ ተሰማ ናደው የሴራ ቤተኝነት ከሆነ ግን አደጋው እጅግ ሰፊ ነው። ሰቅስቆ ለመድፋት እዬተሠራ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁኝ እኔ። እንደ አንድ የኩዴታ አዬር ነው እኔ ያዬሁት። 

ምክንያቱ ፈንጁም፤ መፈንቅሉም፤ መርዙም፤ እገታውም አብይን ሊያሰወግድ አልቻለም። አዲስ አባባ ላይ የተፈጠረው ህውከትም ታቅዶና ተሰልቶ ነበር። ይህም ለድል ቢበቃ ሥልጣን ለመንጠቅ አላስቻለውም። የቀረው ፓርላማው ወስጥ ግብቶ መጎርጎር ነበር። ይህም ተሳክቷል ብዬ አስባለሁኝ። ነገ ሌላ ቀን ነውና ነገም ሌላ ገመና እንሰማለን። እኔ በህልሜ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት ቀናትን አላምናቸውም። ከቅርቡ ያሉትን መሰናክሎች ገና ዓይኑን አልገለጠም ጥገናዊ ለውጡ።

በውነቱ የጥገናው ለውጥ መንፈስ በመቀበል እረገድ ቅንነቱ ያላቸው ምን ያህል ነው ለማለት በፐርሰንት ለማውጣት መሬት ላይ የተሠራ ነገር ስሌለ መግለጽ ቢያድግትም ያ የቀኑበት የሚሊዮኖች አብይ የእኛ ነው ድምጽ ግን አፈር ድሜ ማስጋጣቸው የሚታይ የሚጨበጥ አመክንዮ ነው። 

ቀልባቸውን ተገፎ፤ ባዶ እጃቸውን ስቀሩ፤ እርር ኩምትርትር ጭምትርትር ያለው፤ አውጥተው ያልነገሩን ቁስለት መሻሪያውን አግኝተዋል። አሁን እኩል ለኩል ተሁኗል። ያም ቢመጣ ያም ቢሄደ ለውጥ የለውም የሚለው መንፈስ አድማጭ እያገኘ ነው። የተፈለገውም ይህ ነበር። የወጣላት ዓራት ዓይናማ ልዑቅ ሊሂቅ ለማዬት አለመፍቀድ ነበር።
  
የአዲስ አበባ ትርምስ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ያን ታግሶ አሳልፎት ቢሆን ኖሮ የሴረኞች ህልም ባክኖ በቀረ ነበር።  ነገር ግን በአማካሪ ችግር ሺዎች ታሠሩ 5 ቅኖች በአደባባይ ተረሸኑ።  ይህም ታቅዶ የተከወነ ነበር። ሰው አብይን ከመንፈሱ እንዲያወጣ ተፈለገ ተሳካም። በግራ በቀኝ ያ ቅን መንፈስ አጥር ክትር አለነበረውም። 

ፍቅር የሰጠ፤ መታመንን ካለ ክፍያ የሰጠ ህዝብ ከልቡ ከፋው። የፈሰሰ ያልታፈሰ ሆነና አሁን ድርግምግም አለ ሁለመናው። ድርግምግም ስል ያ እንደ ሞገድ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብይ የኛ፤ ገዱ የኛ፤ ለማ የእኛ ያለው መንፈስ ወደ መጣበት ተመለሰ። የሚሊዮን ተስፋውን እንዲቀማ ተሴረ ተሳካም።

መቼም መሪነት ማለት እረኛ ምን አለ የሚለውን በማስተዋል መመርመር ሲችል ብቻ ነበር። ይህ በውነቱ ወና ነበር። ድንብልብል ፖለቲከኞች እና ግባቸው ምን ስለመሆኑ በግልጽም፤ በቅኔም ስጽፍ ነበር የባጀሁት። ነገር ግን አድማጭ አልነበረም። የአብይ ካቢኔ ንጹሃንን አደባባይ ላይ ሲረሽን ትናንትን ነገን ማዬት ተሰኖት ነበር። 

ወንድ ከሆነ ገንዘብ የረጩትን ቢያንስ የቁም እስረኛ ማደረግ ይገባው ነበር። እነሱን እያሽመነሞነ በልተው የማያድሩትን በአደባባይ ረሸነ። ለዚህ ነው እኔ አበክሬ ኮ/ጎሹ ወልዴን አማካሪ እንዲያደርግ ስማጸን የባጀሁት።
  
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ይታወቃል። እዛው አብረው ተኑሯል። ሌሎቹ ግን አይታወቁም። ወደፊትም የአብይ ለማ ካቢኔ ሊያውቃቸው ፈጽሞ አይችልም። የለማ አብይ ካቢኔ እነሱን የሚያውቃቸው ከተሸነፈ በኋዋላ ይሆናል። ወይንም ስልጣኑን ካስረከበ በኋዋላ። ለነገሩ አሁን እኮ የደከመበት ባክኖ ነው የቀረው። ልብ ሸፈተ እኮ። መሬቱን ካለልክ በሆነ በተንጠራራ ዕወቅና ሰጠ አገኛት።

አሁን ስለምርጫ ሲወራ ይገርመኛል። ከዛ ከተደረሰ ነው። የትኛው ድርጅት ነው መደበኛ ሥራ የጀመረው? ማለቴ የቢሮ ነፍስ ያለው መዋቅራዊ እንቅስቃሴ የጀመረው? የፓርቲ ተጋድሎ እንደዚህ ነውን? ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አለን? የቱ? የሚጠበቀው ኩዴታ ያ ካልተሳካ የሽግግር መንግስት ነው። 

በሌላ በኩል የአብይ ለማ ካቢኔን ችግሩ የራሱ ድርጅትም ኦህዴድ/ ኦዴፓ ስለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሊሂቃን ሁሉንም አጥተው ባዶ እጃቸውን እንደ ለመደባቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ በብዙ ሁኔታ ስጽፍ ነበር። 

አሁን ይህን ሰሞኑን ዶር ለማ መገርሳ ይህን በአጽህኖት ሲገልጹት ሰምቻለሁኝ። በጣም ዘግይተዋል። ከእጃችን ሊያመልጥ ነው ሥልጣኑ ፋታ ስጡን ዓይነት ተማጽህኖ ነው የነበረው ዕድምታቸው።„ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ“ ማለት ይህ ነው።

የሳቸው ጥረት የኦሮሞ ድርጅቶችን ማሰባሰብ፤ የኦሮሞ ሊሂቃንን ማሰባሰብ እና ጫና ተጨማሪ በመፍጠር ለኦሮሞ ጥያቄ መልስ ማሰጠት ቀዳሚ ትልሙ ነበር። ግን እርምጃቸው ጥረታቸው ራሳቸውንም ሊያቃጥል ነዲዱ እዬፈተናቸው ነው። 

የውጭ አገር ሃያላን መንግሥታት ሊቆጣጠሯቸው የማይችሉ የውጭ አገር መንግስታትን በራሳቸው ውስጥ አንድ አፈንጋጭ ቡድን ከውስጣቸው ያደራጁን በሎጅስቲክስ በገፍ እዬደገፉ ሲቀናጡ ራሳቸው የፈጠሯቸው አፍንጋጭ ሰውር ድርጅቶች ዓለምን ለማወከም ከአቅም በላይ የሆኑበት ሁኔታ ፕላኔታችን በተለያዬ ዘመን አስተናግዳለች። አሁነ የዶር ለማ ጥረት እና ልፋትም ይህን እዬመሰለኝ ነው።  

አንድ ሰው ከሁሉም ሃብታት በላይ ለመንፈስ ሃብቱ ጠንቃቃ መሆን አለበት። ለመንፈስ ሃብቱ ቀናኢ መሆን ቀዳሚው ተግባሩ ሊሆን ይገባል። ንጉሥ ዳዊት ልብ አምላክ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላይ እንዳለው“ ማለት ነው። ብልህነታቸው የሁለቱም የዶር አብይ አህመድ ይሁን የዶር ለማ መገርሳ የጠበቀኩትን ያህል አልሆነም። ያ ሁሉን የሚሊዮን ፍቅር በራሳቸው የጥንቃቄ ጉድለት ጠንቅ አፈር ውስጥ ነው ያቦኩት። በመቼውም ዘመን ይህን ደግመን እናገኘዋለን ብለው አይሰቡት ኦህዴዶች /ኦዴፓዎች።  

ኦሮምያ ላይ የነበረው ትኩረት፤ ለኦሮሞ ሊሂቃን የተሰጠው ልዩ አትኩሮት እና ለሌሎችም ጎልተው ለወጡ ባለሚዲያ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ባለቤቶች የተሰጠው ዕውቅና ሌላውን ያቀለለ ያንኳሰሰ ነበር። እዛው አብረው ፍዳቸውን ለከፈሉትም የነበረው የአያያዝ ጥብብ በዜሮ የተዛባ ነበር።

ኦሮምያ ክልሉን እራሱ መቆጣጠር አቅቶ ያን ያህል የኢ - ሰብዕዊ ድርጊት ተባባሪ የሆኑ ግድፈቶች ሲፈጸሙ የራስን አካል ለመቆጣጠር፤ ለማጋለጥ፤ እርምጃ ለመወሰድ አልተደፈረም። በሌላ በኩል ከዛው መወቃራቸው ያሉትን ጓዶቻቸው ለበደሉት የቡራዮ ህዝብ እርዳታ አለንልህ ያሉ የአዲስ አባባ ወጣቶች ግን ታገቱ። ፍትህን በዚህ ውስጥ ስታለቅስ ማዬት ራሱን ለገበረ ህዝብ ምን ያህል ህሊናን እንደሚያቆስል ስላለንበት አሰተርጓሚ አያስፈልግም። 

ጥድፊያው የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ እና የሹም ሽረቱ ጉዳይም ሌላው ጊዜውን ያልጠበቀ ጉድ ነበር። ጊዜውን ቢጠብቅም ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው ላለ ሞገድ አይመጥነውም ውርክቡ ሁሉ። ለዛውም ታሪክ እና እውነት ተደፈሩ ሲባልም ከዚህ ግባ የሚባል የጭብጥ አመክንዮ የለም። ምኞት ብቻ እና ቀን ከመስጠት የመነጨ ጉዳይ ነበር። 

ይህን ሲያገኙ ተግተው የሠሩ የሌሊት ወፎች የራስ ተሰማ ናደው ሴረኞች ቀጥ ብሎ የለማ አብይ ውድቀት ዒላማቸው ላይ ሲገባ ትንሽ እሳቤ አድርጎ ያን ዝርክርክ መረጃ እንኳን ገርቶ እርምጃ ለመወሰድ አልተደፈረም። ለበደሉ ለማካሻ ተብለው የቀረቡ የለበጣ ትንዕይነቶች ደግሞ ከልብ የሚገቡ አልነበሩም። 

ቄሮ ተበሳጭቶ እርምጃ ወሰደ ለተበለው ራሱ እኔን ሊያሰምን ከቶም አልታቸለውም አይደለም እንኳንስ ሌላውን። እኔ ያዬሁት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጫካ በሚኖርበት ጊዜ እራሱ ሃውዜን አስደብድቦ ፊልሙን 
ቀርፆ ደርግን እንዳጋለጠው ዓይነት ነው ያዬሁት። በዚህ ወስጥ ግን እነኛ ምንዱብ እናቶች በግራ ቀኝ ሴራ አሁንም የልጅ እና የትዳር ቀባሪ ሆነዋል።

በሌላ በኩል በዝርግ ፖለቲካ፣--- በሴራ በምቀኝነት በሸር እና በተንኮል ለኖረ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ማስተዳደር አይቻልም። ሴራን የሚያከሽፍ የመንፈስ አቅምም ተቋምም የለንም። በዛ ላይ እነ አይደፌ ከማዕከል በሚላክላቸው በጀት አልጠገብነም ያሉ እነ ሳጅኖች ደግሞ መቀሌ ላይ አሉ። 

የለማ አብይ ካቢኔ ዘመዴ፤ ክንዴ ያላቸውም ቢሆኑ ሴራቸውን እንዲህ መረቡን በጣጥሶ መንፈሳቸውን፤ ልባቸውን ለማግኘት የዘመን መንገድ ነው። ልብ ለልብ፤ ግልጥ በግልጥ ግንባር ለግንባር መገናኘት አይታሰብም። ባዶ የምላስ ግርዶሽ ነው የሚደመጠው። ምክንያቱም እነሱም ወንበሯን ይፈልጓታል እና።

ቅን መሆን መልካም ቢሆንም ለሴራ ፖለቲከኞች ደግሞ ቅንነትም ግልጽነም ጅልነት ነው። ግራ ቀኙም ያልተጠቀሙበት ስለመሆኑ እያዬን ነው። ችግሩ ይህ ለውጥ ካሰበው ባይደርስ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ነው? የሁሉም ዓይን እና ህሊና አብይ ተወግዶ ወንበሩ እንጨቱን ሲጓተቱት ሲቦጫጨቁት ብጥስጥስ ብሎ አንድዶ መሞቅ ነው በወል ያለው ዕድምታ። "ከራስ በላይ ንፋስ" እንዲሉ።  

በቃ የሚፈለገው ይህ ነው። የቅኖች ማነስ፤ የአማካሪዎች አለመኖር ያን የ100 ቀን ትንግርት እንሆ ወደ መቃብር ልኮታል። ምክንያቱም የ100 ቀን ትንግርት ልበ ገዝ፤ ህሊና ገዝ፤ ተስፋ ገዝ ነበር። ግን ትውልድን ሲያባክኑ የኖሩት ሽንኮች ዶለቱበት እናም ተሳካላቸው

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ንፋስ እና ወጀብ ብቻ ነው ስንቅ እና ትጥቁ። ቁመናው ደግሞ እፉኝት ነው። ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን የሚያጠፋ። ይህን በውል ተረድቶ ይህ ልቅ እና ዝርግ የሆነ የአያያዝ እና የአመራር ሁኔታ በጥበብ መምራት ሲገባ ያገኙትን እያጡ እንዲሄዱ ከሚታታሩ ሴረኞች በልጦ ባለመገኘት ሴረኞች ባቀዱት ጉድጓድ አብሮ መስመጥ እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።

ሀዘኑ አኔንም ይመለከታል። ምክንያቱም እኔ በግሌ ሌት እና ቀን የደከምኩበት ስለሆነ። አቅሜን አፍስሼበታለሁኝ። ከላ ታዕቅቦ የሚሰማኝን በመግጽ ሞግቻለሁኝ። ነገር ግን ውጤቱ ይኸው አይሆኑ ሆኖ እያዬነው ነው። ልጓም በሌለው ቅንነት የተፈራው ሰብል ሁሉ አረም አራሙቻ በቀለበት። ለዛውም ለማ አብይ ፈቅደው እና ወደው። ምንጣፍ እና ጉዝጓዝ ሆነውለት።

"የትም አይደርሱም" ጉዳይ አሁን የት ደረጃ ላይ እንዳለ ይተወቃቸዋል። አብሯቸው የተጋውን ብአዴንን እንኳን በሌላ ነገር፤ ባልገባ የቤት ሥራ በማጣደፍ እና ፋታ በመንሳት መንፈሱን ብኩን እንዲሆን ነበር የተደረገው። አደብ ጠፋ። የብአዴን አቅሙን በጣም ነበር የፈተኑት ኦህዴዶች /አዴፓዎች። አባከኑት ብአዴንን። የብአዴን ታማኝነት በጣም ነው የታገሉት። ክንዳቸው ማገራቸው ግን ብአዴን ነበር።

የሆነ ሆኖ „አንቺው ታመጭው አንቺው ታሮጪው“ ሆነ እና አሁን የተበተነውን መንፈስ በምን አቅም አሰባስቦ፤ በምን ሁኔታ ገርቶ፤ በምን ሁኔታ ቀጥቶ ወደ መዳፍ ለማስገባት ሌላ ረጅም ፈተና ከፊቱ ተደቅኖበታል የለማ አብይ ካቢኔ።

በመጀመሪያ ምህንድስናውን የብአዴን ጉባኤ በተነበት። የአቶ ደመቀ መኮነን ከሥልጣን ለማግለል የተሄደበት መንገድ መከነበት። አሁን ደግሞ ትናንት ፓርላማው ላይ ሁለገብ ጉልበታም ማፈንገጥ ተደመጠ። ሁለተኛው ክሽፈት ማለት ነው። 

የኦሮሞ ሊሂቃን አክቲቢስቶች ካለልክ መንጠራራራት እና እዬገዛናችሁ ነው መታበይም መዳራሻው ይህን አሳይቶናል። የሌሎችም የእባብነት መንገድ እስተዚህ አድርሶናል። ነገስ? ወፊቱ ትጠዬቅ። ያው ቀድሞ ቢሆን መልካም ቢሆንም፤ አሁንም ቢሆን ኮ/ ጎሹ ወልዴን አማካሪ ማድረግ ይገባል። ሳይዘገይ። ጊዜ የለም።

ነገ የራሱ አዬር ስላለው ይጠበቅ።
የኔዎቹ አዱኛዎቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።