ጎንደር አደብ መግዛት አለበት። ሰላሙንም መጠበቅ ግዴታው ነው።
ጎንደር ልብ ይግዛ!አደብም ይኑረው!
„ሃሌ ሉያ።
እግዚአብሄርን በመቅደሱ
አመስግኑት።“
በሃይሉ ጠፈር አመስግኑት።“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
07.11.2017
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን ስለተበተነው የውሸት ወረቀትና እና ስለሰሞኑ ጉዳይ የተናገሩት 28,02,2011
አሁን ከሆነ ኤቢ አድበርታይዘመንት የሚያዘጋጃቸውን ቅንብሮች እከታተለሁኝ። ተመስገን ብያለሁኝ። ነገረ ጎንደር ነገረ ሥራው መከረኛ ስለሆነ መረጃዎች ጭጭ ሲሉ ይጨንቀኛልና። በመንግሥት ደረጃም ከሚዲያም የተገለለ ነው ጎንደር። ጎንደር የሚፈለገው ኧረ ጎራው ሲፈልግ ብቻ ነው። አሁንም ጫና በጠ/ሚር አብይ አህመድ ላይ እንዲኖር ስለሚፈለግ ሲጯጯኽ አዳምጣለሁኝ።
የአብይ ለማ መንፈስም ለጎንደር ቀልቡን መስጠት ይኖርበታል። አሁን የተመረጡት ከንቲባ ዶር ሙሉቀን አዳነ ልክ የሱማሌው ችግር በተፈታበት መንገድ አይነት ነው። የዚያን ያህል መንፈስ በገፍ ሊሰጠው ይገባል። ብአዴንም ዕድለኛ ነው እንዲህ አይነት ብረት መዝጊያ ሊሂቅ ጎንደር ላይ ማግኘቱ።
የጎንደር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አደና በተለያዩ ወቅቶች ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እና ንግግር አዳምጫለሁኝ። ለሁሉም እኩል አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ቅን ሰው መሆናቸውን ከንግግራቸው መረዳት ችያለሁኝ።
የጎንደር መዘጋጃ ቤት ለዘመናት መጋጃ ቤት ሲባል ነው የኖረው። አሁን እንደ ዕድል ሆኖ እንደዚህ ንግግራቸው እና ልሳናቸው ሊደመጡ የሚናፈቁ ከንቲባ መገኘታቸው እኔን እራሱ ገርሞኛል። ተዬት ተገኙ ሁሉ ብያለሁኝ።
የሥነ መንግሥት ክህሎት ባላት በጎንደር ከተማ እንዲህ የሰከነ ሰው ዕድለኛ ባለቤት ስትሆን የታምር ያህል ነው እኔ የምመለከተው። እርግጥ ነው ራሳቸውን ከማንኛውም ጥቃት ለመጠበቅ ጠንቃቃ መሆን ይገባቸዋል ብዬም አስባለሁኝ። አላገኛቸውም እንጂ ባገኛቸው እምነግራቸው ይህን ነበር። ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም።
ዛሬ አንድ መግለጫ ሰጥተዋል። ጎንደርን ለማወክ አዲስ ጥንስስ መኖሩ የሚታወቅ ነው። ጎንደር ሰላም መሆኗ የሚነስታቸው የህሊና ሪህዎች አሉና። እንደ አዲስ አባባው ሁሉ ጎንደርን በመንፈስ ማተራመስ የታቀደበት ጉዳይም ነው። ምክንያቱም በይትበሃል የቆዬ ነገር አለ። „ጎንደር ምን አለ“ መባልን።
እንዲያውም ከአንዳድ የጎንደር ስብሰባዎች እንደ ታዘብኩት ከውጭ ወደ አገር የገቡት ሳያቀሩ የጎንደሬውን መንፈስን ተርትረው እና በትነው ወደ መጡበት እንደ ተመለሱ ሁሉ አዳምጫለሁኝ። ተወላጁም ለወላጆቹ ሰላም ያልሳሳ ሌላው በምን ተዳው ይህን ጉዳይ በባለቤትነት ይረከብ?
የቅማንት ተወላጆች ጎንደሬዎች ያልገባቸው ነገር ውጪ አገር ይሁን አገር ውስጥ ያለው ማዕቀብ ሁሉ „ጎንደሬነት“ ነው። ጎንደሬ ሲባል ሁሉም ጸጉሩ ነው የሚቆመው። ጎንደሬ ቅማንት ይሁን አማራ አጋው ይሁን ቤተ እስራኤል ዕጣ ፈንታው አንድ ነው። መገለል፤ በክፉ መታዬት፤ ትቢያ መልበስ፤ መታገድ ብቻ ነው።
ይህን እኔ በስማ በለው ሳይሆን ስለኖርኩበትም ነው የምነግራችሁ። ጎንደሬነት አለርም ነው በዬተገኘንበት ቦታ ሁሉ። ቀይ መስመርም ነው ጎንደሬነት። ለምን? እነሱም ያውቁታል እኛም ስለምን እንደምንገፋ እና እንደምንፈራ አሳምረን እንተዋወቃለን።
የሆነ ሆኖ በላይ እና በታች ጋይንት፤ በስማዳ እና በአፈርውሃናት፤ በወረታ እና በሊሞ ከምክም፤ ባገፋት እና በማክሰኝት፤ በጠዳ በእንፍራንዝ፤ ደንቢያን ይዞ ጎርጎራ፤ አለፋ ጣቁሳ ደልጊ እና በተንከል፤ ገለድባ እና ሰራባ፤ ጫቆ እና አዳኝ አገር፤ ዳዋ እና ቋራ መተማ የሖንስ ከተማና ማጠቢያ፤ ላይ እና ታች አርማጭሆ ወገራ እና ስሜን እስቴ እና ፋርጣ ሁሉም በአንድነት መምከር ያለበት ጉዳይ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ሊመጣለት እንደማይችል ማወቅ እንዳለበት ነው።
የጎንደር እናት ለዬዘመናቱ የልጅ ብርንዶ ስታቀርብ ማገዶ ሆና ኖራለች። ሰላማቸው ተጠብቆ የኖሩት ናቸው ዛሬ የለሙ የሚባሉት፤ መሪ የሚሆን ልጅም ማድረስ የቻሉት። የሁሉን መከራ ተሸክማ የኖረችው ጎንደር ግን ሌላው ሲማር ሲመራመር ሲሞሸር፤ ሲያገባ፤ ሲወልድ እሷ ከፈኝ ያለውን ሁሉ እንደ እናት አቅፋ ባዕቷን የጦርነት ቀጠና አድርጋ ዕንባዋን ቋጥራ ልጆቿን ቀብራ እና ለአንጋችነት አስልፋ ነው የኖረችው።
በስንት ውጣ ውረድ ብቅ ስንል ደግሞ አንገት አንገታችን ነው በሰይፍ እና በገጀራ። ስንት ፍዳ ስንት ሰቃይ ስንት አሳር እንዳለ ከሥርጉተ በላይ ገላጭ ማመሳካሪያ ቋሚ ምስክር የለም።
ለዬዘመናቱ በማገዶነት፤ ለዬዘመናቱ የሰው ስንቅ እና ትጥቅ በማቅረብ ሁሉንም እንደ አመሉ ሸክፋ አደራ ያወጣቸው ጎንደር ከአብይ መንፈስ የተሻለ ጌጥ ከቶም የላትም። የዛሬን ሳይሆን የቀደመውን የመንፈስ እርስትነት በዚህ ንግግር ከልብ ሆኖ ማድመጥ ይገባል። ይህን እኔ የዛሬ ዓመት የጻፍኩት ነው። ያን ጊዜ ሥማቸውም በወጉ ያልጎላ ነበር።
ስለሆነም ለዚህ የሰላም ዘመኑ ጎንደር እራሱ ዘብ መቆም ግድ ይለዋል። ዘመናት ወራታታ ቀናት ያልፋሉ ትወልድ ግን አያልፍልም። ስለዚህ አንድነቱን ጠብቆ የኖረ ህዝብ የኖሪዎችን ደህንነት በመጠበቅ ሰላሙን በመሳቀጠል ረገድ ራሱ መትጋት አለበት። ለውጡ እኮ የራሱ ነው።
ጎንደር ራሱን ገብሮ ያመጣውን ለውጥ በሳንክ ማበላሸት መቅበር አይገባውም። ከሁሉ በላይ የጎጃም ውላታስ በምን ወቄት ሊመለስ ነው? ጎንደር ሆይ ናፈቀህን የ27 ዓመት የእነ አቦይ ስብሃት የሰቀቀን ዘመን? ናፈቀህ ሆይ የነሳጅን በረከት የመቀበር የሴራ ደቦ? ናፈቀህን ወይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የግዞት የጎንደር እና የጎንደሬነት የመሰረዝ የረጅም ጊዜ ትልም?፡
ለቅማንትም ቢሆን ከጎንደር በላይ፤ ከታሪኩ በላይ፤ ከትውፊቱ በላይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴራ እና ሸር ከበለጠባቸው ራሳቸው ያውቁታል።
መጪው ዘመን ቢከፋ ለእነሱ እንጂ አማራ እንደሆነ ላይለያይ በመንፈስ አንድ ሆኗል። ውጪ አገር ያለውን ሞገድ ቢያዩት እጅግ የሚገርም እና የሚደንቅ ነው። ዕድሜ ለጎጃም ባለቅኔዎች። ያ የመከራ ጊዜ ታልፏል። ቀሪው ጊዜ ለአማራ ደግሞ አንገቱን ላይደፋ አባቶቹ ባቆዩት አገር እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ዛሬ በስማ በለው ሳይሆን ወጣት ሊሂቃኑ ተግተውበታል። እኛም አንተኛም። ወጣት ሊሂቃኑ ትንታግ ናቸው። ለተጋድሏቸው ባለቤት ሁነውታል። አሁን አቶ ጋሻው መርሻን ያደመጠ?
የአብን አመራሮች ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት-
አማራ ቴሌቪዥን የነበራቸው ቆዩታክፍል፡-አንድ
የአብን አመራሮች ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት-
አማራ ቴሌቪዥን የነበራቸው ቆዩታክፍል፡-ሁለት
Published on Oct 30, 2018
እሚጠቅመው የወረቱን ጤዛማ ነገሩን፤ ዕለታዊ ድሎት እና የሳሙና አረፋ ጉዞውን ተወት አድርጎ በስክነት ማሰቡ እና አደብ መግዛቱ ነው ለቅማንት ማህበረሰብ የሚጠቀመው። አገር ለማፈረስ የቅማንት ማሀብረሰብ ምክንያት ባይሆን ይመከራል። አባቶቻችን ያሰተማሩት ይህን አይደለም። ሚስጢር ከሚቀዳበት ባዕት ዛሬ ራስ በራስ መጨፋጨፍ አፍረት ነው ለዛውም ለወያኔ ሃርነትን የጭካኔ አሰተዳደር ባንዳነት ተሰልፎ። ውርዴትም ውርዴም ነው።
እነሱ ለወልቃይት ለጠገዴ ለራያም አልሆኑም እንኳንስ ለእናንተ። ማተበ ቢሶች ናቸው። ይህን የገድ መንገድ ብትገፉት፤ ብትቀናቀኑት ቀን ራሱ መራራ ጽዋ አስገድዶ ያስጎነጫችኋል። ምርጫው እንደ አባት አደሩ አብሮነት በስተቀር ደግሞ የሰማዩን ቁጣ መቻል ነው። መነጠል፤ መለዬት አድማ፤ መፍቀድ ከሰውነት ተራ ያወርዳል።
በተረፈ በተረፈ የጎንደር ህዝብ እኔም አሳምነው ጽጌ ነኝ ብሎ ጎረቤቱን፤ አካባቢውን መጠበቅ ግዴታው ሊሆን ይገባል እላለሁኝ። ስክነት - አደብ እዮባዊነት እንደ ተፈጥሯችን መሆን ይገባል። ቅኔነትን አንበደርም እኛ።
Mayor of Gondar: Dr Muluken Adane – SBS Amharic
· ስለ ጎንደር እኔ የጻፍኩትን ከአርኬቡ እንዲህም ብትታደሙበት ይበጃል። በ2014 የተጻፈ ነው ዘሃበሻ ደጉ አትሞልኝ ነበር።
መታገስን ያወቀበት ካሰበው ይደርሳል።
የኔወቹ ኑነሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ