"አግዚአብሄርን አመስግኑ።"

„አግዚአብሄርን አመስግኑ።“
„እግዚአብሄርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና።
 ለአምላካችን ምስጋና ያማራ ነውና።“
መዝሙር ፻፵፮ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪


ከሥርጉተ©ሥላሴ
 07.11.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዝሻ
"በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን!"

ውዶቼ እንዴት ናችሁ ዛሬ ደግሞ ተነስቶብኛል። እቸከችከዋለሁኝ።
  • ·      ንዲህም ሆነላችሁ …

አዲስ ብርሃናማ የምሥራች ሰንበት ላይ አዳመጥኩኝ። ሰንበትንም በሰላም አሳለፍኩኝ ሻማዬን ቦግ አድርጌ። ምክንያቱም ዕለታዊ ዜና መስማት የምፈልግበት አንድ አውደ ምህረት ስላለ። ያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አህታዊነት ቀጣይነት ጉዳይ ነው።

ሃይማኖታዊ ጉዳይ ከነባቢት በላይ ነው። ብዙ ሰው ተቋም የለውም ጥገናዊ ለወጡ ሲል አዳምጣለሁኝ። በመንፈሳዊ ህይወት የሁለቱም ሃይማኖቶች የእስልምና እና የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለማስማማት አንድ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ እና የተከወነው ተግባር ለመንፈሳዊ ህይወት ታላቅ ተቋማዊ ውጤት ነው።

አላዛሯ ኢትዮጵያ እግዚአብሄር / አላህ አላ ብላ ስለምታምን ተከታዮችም እልፍ ስለሆኑ በዚህ ዘርፍ የተከወነው ዕሴታዊ ትውፊታዊ ተግባር የቆሰለውን ታሪካችን ደግሞ የፈጠረ ነው ማለት ይቻላል። ሁለት ትልልቅ ባላዎች አሉት ጥገናዊ ለውጡ። ጸሎቱም ነው በተከታታይ ከሞት ከተቃጣ መከራ ጠ/ሚር አብይ አህመድን በዬጊዜው እዬታደጋቸው ያለው። ጸሎት /ደዋው ከተወረወረ ሰይፍ ይታደጋል።

የቅድስት ኦርቶዶከስ ብጹዕን አባቶች በዬሚገኙበት ውጭ አገር አይናችሁ ጥርሳችሁ ከሚባሉበት እንክብካቤ እና ቁልምጥ ወጥተው ወደ አገር እንገባለን ብለው ሲወስኑ ከአንድነት በላይ ምንም ስሌለ ብንፈልገውም ከሄዱ በኋዋለ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ስጋት ግን አልነበረም ብለን መዋሸት አይቻልም። እኔ ሰፊ ስጋት ነበረብኝ። ምክንያቱም ሴራ መከራችን ነውና።

ይህም ሆኖ የቀደመውን መለያዬት አኔ ለሰከንድ አስቤው አላውቅም። 
ይህ የሆነበት ምክንያት የእኔ አቅም ሳይሆን እራሱ ፈጣሪ የሰጠኝ ንጹህ መንፈስ መታመንን እንደ ቀበለው አደረገኝ። በውጭ ባሉትም አብያተ ቤተክርስትያናት የመሰቀል ባዕል አከባበር በአንድነት ስለመከበሩ የውጩ አንጎል በነበረው ኮለንቮስ ኦህዩ እንደ ነበር አዳምጫለሁኝ። 

አሁን ደግሞ የጥቅምት መዳህኒተ ዓለምን በሚደንቅ ሁኔታ በአንድ ላይ መከበሩን ሰማሁኝ። ብዙ ሃይማኖታዊ ዓለም አቀፍ ውሳኔዎችም የሚያልፉት በዚህ በተባረከ ቦታ ነበር። የበደለን መለያዬቱ ነበር። አሁን በአኃቲ መንፈስ እጅግ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ባዕሉ ተከብሯል። የማሃል፤ የአገር ቤት፤ የውጪ ብሎ ነገር የለም። ተመስገን!

ከባዕሉ አከባባር ጋር ከኢትዮጵያ የቆዩ ብጹዑ አባት ስለነበሩ በጉባኤው ላይ እጅግ የሰማይ ታምር የሚመለስል እንክብካቤ አገር ቤት እንዳለ ነው መረጃውን የሰጡት። ብፁዕናን አባቶቻችን ደስ ብሏቸው በሐሴት እንደሚኖሩ፤ መጠለያቸው፤ መሃያቸው የተሟላ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁኝ። 

የጠ/ሚር ቢሮም የተገባውን አትኩሮት እና ክብር በጉልህ መፈጸሙን ተረድቻለሁኝ። አገር ቤት የነበሩት ብጹዕን አባቶቻችንም እንዳ አባት አደሩ በትውፊታችን ልክ በድንግል እና በንጽህና ውህደቱን ተቀበለው በባለቤትነት ስሜት እየተጉ ስለመሆኑ መረጃውን አገኘሁ እና እጅግ ሐሴት አደረኩኝ። ተመስገን!

ሌላው እርግጠኛ የሚያደርገው ጉዳይ የሊቀ ሊቃውነቱ የዶር ካሳ ከበደ ከጎን መኖርም እጅግ የሚያስደስተኝ የማምንበትም ጉዳይ ነው። ልቤን ጣል እንዳደርግ ያደርገኛል። ለዚህም ተመስገን ነው። 

ልዑል እግዚአብሄር አገራችን ይጠብቅልን። አሜን!


"ወስብኃት ለእግዚአብሄር።"  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።