መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም።

መሆኑን ሳይ አልደነቀኝም።
„የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤
ፈርኦንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው
 ድንቁርናን ሆነች።“

ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፲፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
07.11.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።



ዛሬ ጎልጉል ድህረ ገጽ ገብቼ ነበር። አንድ ጹሑፍ አገኘሁ እና ቀልቤን ስለሳበው አነበብኩት። እኔ ጀርመን ላይ አቶ ሺመልስ አብዲሳ ሲገኙ በምን አግባብ ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር። ስለ አቶ ሺመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት ሃላፊ ስለመሆናቸው በፎቶ የተደገፈ ዘገባ ነበር ጉግል ላይ ያገኘሁት። ካወጡት አስተያዬቴንም ከሥር ጽፌበታለሁኝ።

ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት ኃላፊ
ለእኔ እጅግ አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ በዛ ወጀብ በበዛበት ጊዜ በጠ/ሚር አብይ እጩነት አቅም ጎን በመሆን ምስክርነት የሰጡ አንድ የኦህዴድ/ አዴፓ ሊሂቅ ቢኖሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ ብቻ ነበሩ። ለቦታውም ምጥን ያለ፤ ክውን ያለ መረጃ በመስጠት እረገድ አቅማቸው አዬር ላይ አንቱ ነበር። አሁን የት እንደ ገቡ አላውቅም። የሆነ ሆኖ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ውስጣቸው ከአቶ አዲሱ አረጋ የተለዬ አቋም እና ምልክታ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም።
ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ስጋትም ተስፋም ሁለቱም በእኔ ቦታ የላቸውም። 
ጊዜ የሚሰጠውን መረጃ ከማድመጥ ውጪ ማድመቅም ማጉላትም ማንኳሰስም በበቃኝ ተከውኗል። ብቻ ያው ኦህዴድ/ ኦዴፓ አንዱን አምጥቶ ሌላውን ቢሸኝ፤ አንዱን ሸኝቶ ሌላውን ቢያመጣ ያው የኦነጋውያን መንፈስ ተጽዕኖ ይለቀዋል ለማለት አይደፈርም። ጊዜ እዬጠበቁ የወጡ ዕውነቶች አሁን ከሆነ ሰብሰብ እንድንል ድርብ እና ድርጁ መልዕክት ልኮልናልና። በትግራይ ሊሂቃን በኩልም ያዬነው ይኸው ነው። የወንድ ልጅ እናቱ አንድ ናት እንደ ተባለው ነው እያዬን ያለነው እውነት እውነት ነው።

ሾላኪው ከሊቅ እስከ ደቂቅ እዬሆነ ነው። ውይይቶችን የእኔ ብሎ ለሚያደምጣቸው፤ ጹሑፎችን ጉዳዬ ብሎ ለሚታደምባቸው ቅን ዜጋ 
ብዙ ሰው እዬሾለከ መሆኑን ልብ ብሎ ማስተዋል ይቻለዋል። የራስ ጉዳይ 
ሲሆን ማጣፊያው ሲያጥር እዬተመለከትን ነው።

የሚበጀው በተደሞ - በትእግስት - በአርምሞ እዮባዊነትም ሰንቆ ማዬት ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ አብይ ሚሊዮን ፍቅር ሲያገኝ ለኦሮሞ ታሪክ ስለመሆኑ አልገባቸውም። ለድርጃታቸው ለኦህዴድ እንደ ገና የብሥራት ልዕልና የአዲሳዊነት ዜና ቀለማም ምዕራፍ ስለመሆኑ አልታያቸውም። እንዲያውም ገዝግዘው ለመጣል ከራስ ተሰማ ናደው ሴረኞች በላይ ራሳቸው ራሳቸውን ታግለው ያን የሚሊዮን ፍቅር የዶግ አመድ ነው ያደረጉት።
ኦህዴዶች ያልጋባቸው ነገር ቅብዕ የፈጣሪ መሆኑን ነው። አብዩ አንድ ነገር ቢሆን መስሏቸው ነው እንጂ ቦታውን ሊያጡት ይችላሉ። ሌላ የተቀባ ሰው ብቻ ነው ሊይዘው የሚችለው። ቅብዕ የሰው ሥራ ሳይሆን የፈጣሪ ብቻ ነው። አሁን ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ከሦስት ወር በፊት የዚህ ቦታ ተቀቢ ስለመሆናቸው ማን አሰበው። ጠ/ሚር አብይ አህመድም የዛሬ አመት እኔ አብይ ኬኛ ብዬ ስነሳ ከዚህ ቦታ ይደርሳሉ ያለ የለም። ቅብዕ የእሱ የአንድዬ ነው … ሰው ሰራሹ ዳንቴል ሴራው ብቻ ነው።
አሁንም ሹመቱ ከኦህዴድ / ኦዴፓ ስለመሆኑ እኔን አይጨንቀኝም። የሚጨንቀኝ ከአገር አልፎ የአፍሪካ ኩራት የተባለው ብቃት እና አቅም በራሱ ጊዜ ጥበብ አንሶት ከሁሉ ጋር በድክመት እኩል ረድፍ መገኘቱ ብቻ ነው። 
አጃቢውም፤ ዘበኛውም፤ ደህነንነቱም እነሱው ናቸው፤ እነሱው ደግሞ ከሴራ እና ከአመጽ ከደባ እና ከሸር አልታቀቡም። ስለሆነም በዬጊዜው አዲስ አጃቢ፤ አዲስ የደህነንት ሰው ሲለወጥ እናያለን። በአንድ ጉዞ ያዬነው የደህነነት ሰው በሌላኛው ጉዞ አይደገምም። ምክንያቱም መታመን ኦህዴድ/ ኦዴፓ አምጦ መውለድ አልተቻለውም። ከኦነጋውያን ራቁቱን ከቀረ ህልም ጋር መፋተት አልተቻለም። የአሁኑ የሹመት ሁኔታም ከዚህ በተለዬ ሁኔታ አላዬውም። አይሞቀኝም አይቀዘቅዘኝም።
ከ66ቱ የሴረኞች ተመክሮ ራሱን ያላገለለ፤ ያን ተጽይፎ ያልተነሳ ማንኛውም እንቅስቃሴ ከግብ አይደርስም። ያ የ66ቱ የሴራ ዶኮተሪን ለማንም ለምንም የሚጠቀም አይደለም። ብኩል ነው። የነቀዘ ነው። መሃን ነው። 

አዲስ ብቁ እሸት መሪ ማውጣት አይችለበትም። ብቁ መሪም ከወጣ ለማጥፈት ሌት ተቀን ነው የሚባትለው። ትወልድን በመልካም ነገር መትከል አልተፈጠረበትም ግራው። እማዝነው አዲሱ ትውልድ ከዚህ መሰል አረንቋ ወጥቶ እነሱን ግራዎችን በልጦ መራመድ አለመቻሉ ብቻ ነው። እስቲ አዲስ ወጣት ብትሉ አታገኙም። ያው ዕድሜ ልካቸውን እነሱው ናቸው ቁልፉንም በሩንም ከርችመው የያዙት። 

እኔ አሁን የወሰንኩት ጊዜ የሚሰጠውን ውጤት መጠበቅ ብቻ ነው የሚበጀው። መታመን ከራስ ቤት በላይ ማሰብ እጅግ ከባድ ነው። መታመንን ለማግኘት ደግሞ መቅደም የሚገባው የራስ ታሪክ እና የራስ ዕሴት ሳይሆን የህዝብ እና የአገር ዕሴት እና ትውፊት መሆን ነበረበት። ግን አልሆነም።
ቅኖች ጥቂት ናቸው። ቅኖች ጥቂት መሆናቸው ብቻ አይደለም ችግሩ ቅኖችን የማቅረብ እና የማድመጥ ችግርም አለብን። ይህም ብቻ አይደለም ቅኖች እንደ በደለኛ መገለላቸው እና እንዲከስሙ መደረጉም የአላዛሯ ኢትዮጵያ መከራ ነው። ይህን ለማስታረቅ ከወጀብ ከንፋስ በቀል ሞሻሪዎች፤ ለዝና እና ለክብር የሳሙና አረፋ ከመትጋት ውጪ ቅኖችን በአደብ የመፈለግ አዲስ መንገድ ገና አልተጀመረም።  
ደርግም የወደቀው እኮ በዚህ ነው። ቅኖች ይሳደዳሉ አድመኞች ሴረኞች ክብር እና ዝና ያገኛሉ። በዚህም በጎ ነገሮች እዬደረቁ ሳያፈሩ ቀሩ እንጂ ከልብ ሆኖ ለተከታታለው እኮ እጅግ ብዙ መልካም ነገሮች ነበሩበት በዚያ ሥርዓት ውስጥ። ብቁ ሰዎች ነበሩት። ብልህ ሰዎች ነበሩበት። ሊቀ ሊቃውንታት የሥም ሳይሆን ሥር ያለው ህብረ ቀለም የነበራቸው ዓራት ዓይናማ ነበሩበት። በጥረታቸው ነው ሊሂቃን የሚባሉት። መሬት ላይ ተፈትነው ተፈትሸው። እኔ እኮ ከልቤ የሚገባ ነገር እዚህ ውጭ አገር የሌለው እነዛን አራት አይናማ የፖለቲካ ድርጅት አካላት አውቅ ስለነበር ነው። እኔም የፈጠሩኝ እነሱው ናቸው።
ብዙ ደከመው ነው ሰውን በፖለቲካ አቅሙ አሟልተው የሚቀርጹት። ዋነኛው ጎላቸው ሥራ አገራችን እንዲሆን አድርገው ነው የሚገነቡንሰርተን አንደክም። ታግለን አንሰለችም። ተስፋ ቆርጠን በራችን ዘግትን አንቀመጠም። ፊት ለፊት ላመንበት ጉዳይ ወጥተን መሞገት እና መፋለም አንዱ የድፍረት ቀረጻቸው ነው።
በዬደቂቃው ትግላቸው ሰውን የማነጽ ላይ ይታትሩ የነበሩ ሊሂቃን ነበሩበት ኢሠፓ። ግን እነሱም ተገፊ ነበሩ። ለሁሉም ሳይሆን ለዛር ሳይተርፍ ፈለሰ ፓርቲው እራሱ። ሁሉንም ይዞ መርከቡ ሰመጠ። ለዛ ዕውቅና እና ልቅና ደግሞ የአገር ሃብት ፈሶበት ነበር። ብክነት። 
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ብክነት ብቻ። አሁን የተፈለገው እንደዛ እንዲሆን ነው። የብክነቱን መንገድ ጀምረነዋል። ነገ የራሱ ቀን ስላለ ይታያል ጉዱ።
ትውልድ በቅንነት እንጂ በሴራ ፓለቲካ አይበቅልም።
የኔዎቹ ኑሩልኝ ማለፊያ ጊዜ።  



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።