ከታሪክ ማህደር፤ ኮርያ /ከጸሐፊ መስፍን ማሞ።/
እንኳን ደህና መጡልኝ። ከታሪክ ማህደር፤ ኮርያ “እግዚአብሄር አለኝ፣ --- አንተ ልጄ ነህ። እኔ ዛሬ ወለድሁህ። መዝመረ ዳዊት ፪ ምዕራፍ ፯ ጸሐፊ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! መቼም የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ሳይንስ የሚያመራምር እንደ ድንቅና ውስብስብ ልቦለድ ታሪክ ውሉን ለማግኘት ታሪኩ የሚመስጥ በዚህች ምድር ላይ ሌላ መሰል ታሪክ ያለው ሀገር ይኖር ይሆን? በ1950ዎቹ (እአአ) ኢትዮጵያ የምትደዳደረው በዘውዳዊው (ሞናርኪ) ሥርዐት ኢኮኖሚያዊ መሰረቷም ፊውዳላዊ። ያም ሆኖ ከራሷ ጂኦግራፊያዊ ክልል አልፋ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ተቀባይነትና ግዝፈት ያላት ሀገር - ገራሚ ነው!! ለማንኛውም ኮርያ እንዝመት፤ ዘመኑ ከ1950 እስከ 1953 (እአአ) ነው። የኮርያ ጦርነት። በኪም ኢል ሱንግ የምትመራዋ ሰሜን ኮርያ በሲንግማን ሪህ የምትመራዋን ደቡብ ኮርያ ወረረች። ሰሜኖች ኮሙኒስት ደቡቦች ካፒታሊስት ሥርዐት ተከታዮች። ከሰሜን ኮርያ ጎን ቻይና እና ሶቪየት ህብረት በግንባር ቀደምትነት ሲሰለፉ ከደቡብ ኮርያ ጎን ደግሞ አሜሪካና የምዕራብ ዲሞክራሲ ሀገራት ተሰለፉ። በዘውዳዊው የግርማዊነታቸው መንግሥት በፊውዳላዊ ኢኮኖሚ የምትደዳደረው ኢትዮጵያችን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ነበረች። እነሆ ከተመድ መሥራች ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ኮሙኒዝምን ልትዋጋ ከዲሞክራሲያዊ ሀገራት ጎን ተሰለፈች። በ1951 (እአአ) ቃኘው ሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። እነሆም በሩቅ ምሥራቁ ጉደኛ ጦርነት ተዓምረኛ ተዋጊዎች የተባሉት የቃኘው ሻለቃ ጦር የኢትዮጵያን የጀግኖች ማማነት በደማቅ የደም ቀለም በዓለም ዐውደ ውጊያ አስፃፈ። ቃኘው ሻለቃ ጦር በዚያ የጦር ዐውድ በተለያዩ የጦር ግንባሮች