ህግ በራስ ላይ እንዲህ ተፈጻሚ ሲሆን ተስፋ ማደሪያ ይኖረዋል።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

ህግ በራስ ላይ እንዲህ 
ተፈጻሚ ሲሆን ተስፋ
ማደሪያ ይኖራዋል።

„ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።“
ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.02.2019
ከእመ ዝምታ ከሲዊዝሻ።

                                           „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“  
·       መነሻ።

#EBC ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የጉዲፈቻ ልጃቸውን ህጋዊ አደረጉ፡፡


„ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ ዓላማው አድርጎ የተነሳው እሸቱ መንፈስ እንሆ እንደ ማንኛውም ዜጋ በፍርድ ቤት ተገኝተው ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከ5 ወራት በፊት በጉድፊቻ የተረከቡትን ልጃቸውን በህጋዊ ውሳኔ መቀበላቸው ኢቢሲ ዘግቧል። 

ህግን እንዲህ በሁሉ ዘንድ እኩል ተፈጻሚ ሲሆኑበት ተስፋ ማደሪያ ይኖረዋል። ተስፋም መብቀያ ይኖረዋል። ተስፋም ጥግ ይኖረዋል። ተስፋም ትውልድ ይሆናል። የትውልድ የመንፈስ ብክነትም በዚህ መልክ መልክ ቅጥ ለማስያዝ ተግባሩ ትራስ ይሆነዋል።

ትውልድም ከሚሰማው ይልቅ የሚያየውን ስለሚያምነው በሚያምነው ልክ ትውልዳዊ ድርሻውን ለማሳከት ወይንም ለመወጣት ቁርጠኛ ይሆናል። ይህ ከህግ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከሰባዕዊነት አንጻርም በመንፈስ አትራፊ መንገድ ነው። ከሰባዕዊነት አንጻር ብቻ ሳይሆን ከእኛዊነት አንጻርም ተቋማዊነቱ ዝልቅ ነው። ችግርን የእኔ ማለት። አይዟችሁ የማለት። አለንላችሁ የማለት። ብሩክ ቅዬሳ ነው። ተባረኩ።

በዚህ መልክ የተብከነከነው … የተዘባረቀውን … የተስረከረከውን የባከነው ትውልድ መንፈስ ገርቶ መልክ እና ቅጥ ለማስያዝ ይቻላል። ተግባርን መሰረት ያደረገ ርህርህና በፈጣሪ ዘንድም የተባረከ የተቀደስ የጽድቅ መንገድ ነው በሃይማኖትም ዘንድ አንቱ የሆነ ቅኔ ነው። ይህ የተቀደስ ተግባር በቤተ መንግሥት ደረጃ ሲፈጸም የመጀረመሪያው ይመስለኛል በእኔ ዕድሜ።

እንሆ ህፃን ሚሊዮን አብይ አዲሱን ቤተሰብ በአካል ብቻ ሳይሆን በመንፈሰም ህጋዊ ዕውቅናው ተረጋግጦ ተዋህደው። የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለምም በሰባዕዊነት ተኮር የሆነ እና ትትርና ያለው ሉላዊ ዜጋም የዚህ ቅናዊ፤ ደጋዊ፤ ሰዋዊ፤ ተፈጣሯዊ መንፈስ ቤተኛ ነው። 

እንዲህ ያልተለመዱ መልካምነቶች ዛሬ ማዬት በመንፈስ የተጎዳውን፤ ባለቤት አልባውን የኢትዮጵያ ህዝብ የማጽናናት፤ አይዞህ ባይነት መልክቱን ይልክለታል። የተባረከ ተግባር ብርክነቱ ለፈፃሚውም ብቻ ሳይሆን ለአድማጩም ጤና አዳም ነውና።

በመሸኝት ላይ ባለው ሳምንትም ደልዳላዋ ቀዳማዊት እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በጎንደር ለሚገኙ የዓይን ህሙማን ህፃናት ለትምህርት ይረዳቸው ዘንድ የኮንፒተር አገልግሎት እንዲያገኙ ማገዛቸውን ባነሩ ላይ ከተጻፈ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አንብቤ ነበር። ወሸኔ ነው!

ዛሬ ክብርት ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የሴቶች የህፃናት እና የወጣቶች ሚ/ር ክብርት ወ/ሮ የዓለም ጸጋዬ በተገኙበት በመደበኛው ፍ/ቤት በህግ አጋግባብ ጉዳዩ እልባተ አግኝቷል። ሚነስተሯ አብነቱን መከተል ይጋባልም ብለዋል።
ከክበበ ጸሐይ ህፃናት ማሰዲጊያ ህፃንን ሚኒሊዮን አብይን ለማሳደግ የተረከበው የቀዳማዊቷ ቤተሰብ ህጋዊነቱን እንዲጸናለት ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም በፌድራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት 7ኛ የወንጀል ችሎት የህጻናት እና ሴቶች ጉዳይ በተገኙበት በጹሑፍ ጥያቄ ማቅረቡን ነው ነው ኢቢሲ የገለጸው።


እንደ ኢቢሲ ዝርዝር ዘገባም ፍ/ቤቱ ማስረጃዎችን ከተመከተ በኋዋላ ተሻሽሎ በወጣው የቤተሰብ ህግ 213/92 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ክበብ ህጻናት የህጻናት ማሳደጊያ እና ቀዳማዊት እመቤት የተዋዋሉትን ውል መጽደቁን ጨምሮ ገልፃል የኢቢሲ ዘገባ። ጉዳዩን ችሎት ፊት በ አካል ቀርበው የተከታተሉት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የውሳኔውን ግልባጭ ተረክበዋል ሲልም አክሏል ኢቢሰ።

ይህን በሚመለከት በሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፌድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕ/ ክብርት ወ/ሮ ማእዛ አሸነፊም … በተምሰጦ ሂደቱን እና ውጤቱን እንዲህ ገልጸውታል …

 „ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። የአገር መሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፍ/ቤት ቀርበው እንደማንኛውም ዜጋ ጉዳይ ሲያስፈጽሙ አላዬሁም። ስለዚህ የዛሬው ቀን ለአገራችን ፍትህ ሥርዓትም አዲስ ቀን ነው ብዬ ለመውሰድ እፈልጋለሁኝ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው። 

ማንኛውም ሰው ባለስልጣን ይሁን ሃላፊነት ላይ ያለ ሰው ይሁን፤ ማህበራዊ ደረጃው ከፍ ያለ ይሁን ዝቅ ያለ ይሁን ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ቀዳማዊ እመቤት ዛሬ ትምህርት ሰጥተውናል።“ በማለት ገልጸዋል የፍትህ እናት ለመሆን ሃላፊነቱን የተረከቡት ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊም በመቀጠልም በቢሯቸው ብዙ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው ዋናው ግን በህጻናት ላይ መሰራት ያለበት ጉዳይ አብይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

በጥቅሉ ሦስስቱም አንስት ሊሂቃን ይህን መሰል ጥምር ተግባር ለመከወን ችሎት ላይ መገኘታቸው በራሱ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የራሱ የታሪክ መዝግብም እንዳለው ይሰማኛል። ሴቶች በተዳፈነ በተትበሰበሰ መነገድ ያመደረግ አቅማቸው ታዳፍኖ የቆዬውን ያህል እንዲህ ጎኽ ቀዶ የሚዲያ አውራ ሲሆኑ ማዬት ለእኔ ድንቅ ነገር ነው።

በሌላ በኩል ግን ክብርት ወ/ሮ ማዕዛ ካነሱት አንድ ነገር ልከል እኔ እንዲያውም እኮ በተደጋጋሚ ስጽፈበት የነበረው መሰረታዊ ጉዳይ ልጆች በመደበኛ ት/ቤት በህግ ጉዳይ ላይ ትምህርት እንዲሰጣቸው ነው። 

ይህ ቢሆን የወንጀለኝነትን ቁጥር በእጥፍ መቀነስ ይቻላል። እኛ እኮ የአገራችን ህግ ሳናውቅ ነው ያደግነው። ሌላ አገርም እኔ የታዝብኩት ይህንኑ ነው። በፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ ላይ ይህን እንደ አንድ አጀንዳ ነበር የተከተተልኩት ስለበር አቤቱታዬን ስልክም ይህንንም ሁነኛ አድርጌ ነበር። ምክንያቱም የዓለም ግራጫናት ስለሚያሰጋኝ።

ዬትኛውም አገር ልጆች በህግ ዝንባሌ ያላቸው ብቻ ነው ህግ ተኮር ዕድል የሚያገኙት። የእኛ በኮታ ነው። ጭራሽም ዝንባሌ ብሎ ነገር የለም። ብትፈልግ አድርገው ባትፈልግ ፈንግጠው ነው።

የሆነ ሆኖ የእኔ ምኞት ልጆች እንደ ትምህረት አቅማቸው የአጋራቸውን ህገ መንግሥት፤ እና ተያያዥ ህጎችን ቢማሩ ግን የመብታቸውንም የግደታቸውን ጣሪያ አውቀው ማደግ ስለሚችሉ ከብዙ ነገር ግራጫማዋን ዓለምንም ሆነ ኢትዮጵያንም መታደግ ይቻላል። ህግ መማር በራሱ እኮ ሞራላዊ ሰብዕንን መጎናጸፍ ነው።

በህግ ውስጥ ሁሉም ነገር አለ። ራስን ነፃ አድርጎ ከማኖር ጀምሮ። ነጻነት በአግባቡ ከማስተዳደር ከመጠቀም ጀምሮ፤ ትውፊትን ትሩፋትን ታሪክን ማክበርን አክሉ። ህግ ማወቅ በማህበረሰብ ደረጃ ጠቀሜታው እጅግ ሰፊ ነው።

ቢሆን ቢሆን እኔ እንደ ምኞቴ ዓለም ይህን አቅጣጫ ብትከትል ምኞቴ ነው። እያንዳንዱ አገር ልጁን ሲያሳድግ የአገሩን እና ዓለም አቀፍ ህግጋትን እንዲያጠኑ ቢያደረግ ምንኛ ዓለማችን ምልከታዋ በተሻሻለ ነበር። ሚደያዎችም በዚህ ተኮር ትጋት ቢኖራቸው መልካም ይሆን ነበር።

ሌላው ሚዲያ ላይ ብዙም ትኩረት የማይሰጠው የቀዳማዋቷ እምቤት የትትርና ፈለግ ለእኔ ግጥሜም ነው ተስፋዬም ነው። መተኮር ያለበት በልጆች ላይ ነውና። ማግስት ደርቆ እንዳይመጣ ዛሬ ይህ የተደላደለ ተግባር ባለቤት ማግኘቱ እጅግ አበረታች ነው።
·       ለውሽክታ አንድ ነገር ልከል ….

ዶር ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤል ደግሞ ሲያሳዩን እንደባጁት ትግራይ በቀል ኪኖ በዚህ ዘርፍ አዲስ ትወናቸውን ለማዬት ጓጓሁ። የቀረ ነገር የለም። አሜሪካ ባይሄዱም በጠ/ ቤተክህነት ተግኘተው አባቶች እንኳ ደህና መጣችሁ ብለዋል። 

በህዝብ ፊት እየተንጎራደዱ ተቃቅፋዋል ሌላው ክልል ለለውጡ ድጋፍ ባደረገበት ጊዜ እሳቸው ደግሞ የተሰዎ ወገኖችን ምሰል በማስያዝ ሰማዕታት ቀናትን ሲያከብሩ ከህዝቡ በጣም በቅርበት ሆነው ነበር። 

ሥርዓተ ተክሊልም አልቀረባቸውም ያው ብቻቸውን ሆነ እንጂ ፈጽመዋል፤ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ተወካይ በተገኙበት ጉባኤ መርተዋል፤ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን መቀሌ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባርከዋል፤ አባቶች ለሰላም ድርድር መቀሌ ሲገኙ ኮንፒተራውን ዘርጋ አድርገው መግለጫ ሰጥተዋል ለምን ይቅርባቸው፤ ጥምቀትን ራያ ላይ ፍቅር በፍቅር ሆነው በቀይ ምንጣፍ በሰፊ ጥበቃና በልዩ ሰልፍ ትሪኢት ተዘናክተዋል አሁን የቀረ ይህ ነው ደግሞ አንድ የታደለ ህፃን ዕድሉን ቢሰጡት እና ፎቶ ቀጭ ቀጭ ማለቱን ደግሞ ሥርጉትሻ ትጠብቃለች…

በተረፈ ይህ መልካም ዜና አስደስቶኛል፤ ያሰደሰተኝ ሁሉም በህግ ፊት እኩል ስለመሆኑ ስላዬሁበት  ጭምርም ነው። ሴቶችም ጎላ ባለ ተግባር እንዲህ በወል ሲገኙም ሌላው እርካታዬ ነው። አዎና የሚዲያው አድባርም ትጋታቸውን እንዲህ ተከታትሎ ሲዘግብ ደስ ይለኛል። 

„ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“

የቀዳሚዊቷ እመቤት የልብ መንገድ።


የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።