ሰማዕት የእኔ ሰው ገብሬ።
የመሆን የእኛ ሰው በመሆን! ከሥርጉተ - ሥላሴ 12.04.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ።) „ነፍሴ በኋዋላህ ተከታተለች፤ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።" (መዝሙር ፷፪ ቁጥር ፰) እንደ መቅድም። ይሄ ጹሑፍ እንደምታዩት በ12.04.2108 የተፃፈ ነው። ይህ ሰማዕት በውስጤ ያለ ነው። ስለ ጀግናው ረ/ አውሮፕላን አብራሪ በጻፍኩበት ወቅት አብሬ የኔ ሰው ግብሬ እና የሰማዕት የሽብሬን ደስአለኝን ሠራሁት። በዛን ሳምንት ደግሞ ቅኑ ሳተናው ድህረ ገጽ አብዝቼበት ነበር። ከ እኔ ጋር መሥራት ከባዱ ነገር እኔም አይደክመኝ ሰውንም ይደክመዋል ብዬ አላስብም። ስለሆነም በተከታታይ ቀናት ላይ የእኔ ከ4 በላይ ጹሑፍ ብራናው ላይ ሲለጠፍ ለህሊና ዳኝነትም ከባድ ነው። ይገባልም። ተግ በይ በማለት ልጓም ማበጀት። ለእኔም ለጤናዬ የተገባ ነው። ተቆጣጣሪ ከሌለኝ በጣም ነው ሥራ እማበዛው። በዛ ላይ የእኔን ጹሑፍ ማተምም በፈተና ውስጥ ያለ ቀራኖዮ ነው። ጽናቱ እራሱ ይገርመኛል የሳተናው። የሆነ ሆኖ ጹሁፍ አብዝቼ በላኩበት ወቅት ተልኮ ዕጣ ያልወጣለት ስለነበር ዛሬ በእኔው ብሎግ ላይ መለጠፍ አሰብኩኝ። የሰማዕቷ ሺ ብሬም ይቀጥላል። ቢያንስ ለዛሬ ቀን ያደረሱ የትናንት ጀግኖችን፤ ሰማዕታት፤ ቅዱሳንን ማሰብ የተገባ ስለሆነ። መንፈሳቸው ይወቅሰናል። ውስጣችነንም በእሳት ነበልባልም ይገርፈዋል። ይቀጣዋል። ቀን እዬወጣ ስለሆነ በዚህ ቀን መውጫ ላይ ሰማዕታቱን ማሰብ የህሊና ጉዳይ ነው። ያን ጊዜ እንደ ዛሬው ሃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ስላልነበረን ደመ ከልብ ሆኖ የቀረ ሰማዕት ነው