ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወረቂ ሳቁ!
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወረቂ ሳቁ! ከሥርጉተ ሥላሴ 08.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳) እንኳን ደስ አለዎት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ። ከታናሽ ወንድመዎት ጋር በድንግልና እና በንጽህና እንዲህ በሰላም፤ በቅንነት እውነተኛ ከሆነው የደም እና የሥጋ ግንኙት በእትብት አሃታዊነት እንኳንም ለመገናኘት አበቃዎት። ዕውነት ለመናገር ከእንዲህ ዓይነት ሰናይ ቀን ጋር ለመገናኘት በመብቃተዎት ዕድለኛ ነዎት። እንኳን ደስ አለዎት ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ። ይህችን ቀን ሲጠብቁ ስንቶቹ አለፈዋል። ይህ እንግዲህ በዝምታዎት ውስጥ ያለውን አንድ ጸሎት አሳይቶኛል። መሻተዎትን ፈጣሪ ሰምተዎታል። ቀሪ ጊዜዎትም የሐሴት፤ የሰላም፤ የፍቅር፤ የሳቅ፤ የፈገገታ፤ የውስጥነት እርካታ እንዲሆንለተዎት እምኛለሁኝ። የባከኑ ጊዜዎች ሁሉ ለማማካከስም የግኝኙነቱን መስምር በመጠናከር ተጨማሪ የምሥራችን እንሰዘማ ዘንድ ለዛ ያብቃን ቀሜን! መልካም የውጤት የስኬት የልብ ለልብ ጊዜ። ከኤርትራ ጋር በጋብቻ ሆነ በማናቸውም ሁኔታ የትውልድ መሠረት የሆኑትን ልጆች የወለዳችሁ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እናቶች አንኳን ለዚህ ቀን ልዑል እግዚአብሄር አደረሳችሁ አደረሰን። እንኳን ደስ አለዎት ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ! ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ የተወለዳችሁ ልጆች ሆይ! እንደገና በመወለዳችሁ እናንተም እንኳን ደስ አላችሁ! ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እንዳይለያዩ አብረው መከራቸውን እንዲታገሡ ልጆቻቸሁን ለገበራችሁ የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ! እንኳ