የአዳማ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ እና ዕድማታው።
ማሰብ። „ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ጩኸቴንም ሰማኝ።“ መዝሙር ፵ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute© Selassie 14.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ህዝባችን ኑሮው ይህ ነው። · መነሻዬ ይሄ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=A3yNyvpAVh0 #EBC ለሁለት ሳምንታት በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልተገኙት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተገባልን ቃል አልተከበረም አሉ፡፡ እጅግ የሚገርሙ ነገሮች በዬ ዕለቱ ይደመጣሉ። የአዳማ ዩንቨርስቲ የሳይንስ እና የቴክኖሊጂ ተማሪዎች ለሁለት ሳምንት የዘለቀ የትምህርት ማቆም አድማ መትተዋል። ጥያቄቸውን አዳመጥኩት። ግን እዬተማሩ ማቅረብ አይቻላቸውም ነበርን? ደግሞስ አሁን ኢትዮጵያ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሆና ምን አለ ከችግሯ ጎን ቢቆሙ እንደ እጩ ሊቅነት። ከቶ እነዚህ ምንዱባን ምን ይበሉ? https://www.youtube.com/watch?v=kuGKmclKGT8&t=207s የፍትህ ሰቆቃ - በኢትዮጵያ ሲፈጸሙ በነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ተሰራ ዶክመንተሪ። ለኢትዮጵውያን ልብ ቢሰራልን ኖሮ አሁን ባለው የአብይ ሌጋሲ ላይ ምንም ጫና ባለመፍጠር ያ የጭራቅ ዘመን እንዳይመለስ መትጋት ነበር። ለነገሩ "በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር" ሆኖ ዓለም አይታው በማታወቅ ፍጥነት ሁሉ ነገር ፍርስርስ ሳይል በነበረው ሁኔታ በስክነት እና በተደሞ ወልጋዳውን በማረቅ፤ ጎባጣውን በማቃናት፤ ጠማማውን በማረ