#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።
#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን። ማንበቡም፤ ማድመጡም የተፈራ ትግሉማ እንዴት ይደፈር???? ትናንትና በቅኔው ጎጃም በወበራ አዝመራ በመከወን ላይ የሚገኙ ትንታጎቹ የኢትዮጵያ ጉሮሮወች የጎጃም አርሶ አደሮች በፋሽስት አነጋዊ ኦህዴድ መንግሥት ሠራዊት በግፍ በባዕታቸው መረሸናቸውን ኢኤምኤስ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አለማፈራቸው ይገርመኛል። ሰሞኑን በርሊን ጀርመን ነበሩ አሉ። የገረመኝ ከውጭ ጉዳይ ሚር አንሰው ኢትዮጵያ ምድር ላይ አቀባበል የተደረገለት የጀርመን መንግሥት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን የጀርመን ካንስለር በክብር አቀባበል እንዳደረጉላቸው፤ እንደተቀበሉ አዳምጫለሁኝ። ቅጣቱ የህሊና ይመስለኛል ለጎግ ማንጉጉ የኢትዮጵያ የፕሮቶኮል አልቦሽነት። የሆነ ሆኖ ህዝቡን በድሮን የሚጨፈጭፍ ፍፁም ጨካኝ፤ ገበሬው እርሻ እንዳይሠራ ማዳበሪያ የከለከለ፤ በእርሻ ወቅት በባዕቱ ሄዶ ጦርነት የገጠመ፤ ልጆቹ ከ12993 በላይ ለ12ኛ ክፍል ፈተና አትቀርብም ብሎ የቀጣ፤ ስንት አሳር አይተው ተምረው ዩንቨርስቲ የገቡ የአማራ ልጆችን ድብዛ ያጠፋ፤ ያሠረ፤ ያገተ፤ ያንገላታ፤ በመድፍ የፈጄ፤ በራህብ የሚቀጣ፤ በማደህዬት የሚበቀል፤ መጽናኛ የዕምነት ቦታወቹን ያረከሰ፤ ህዝብ ወቶ ለመግባት ዋስትና መስጠት የተሳነው #ቁልል በበርሊን መገኜት ዓይን በጥረጨው ማሸት ብሂሉ በውን የተገለጠበት ሂደት ነበር። በጣም የሚገርመኝ አቶ ቀን፤ ባላንባራስ ሳምንት፤ ደጃዝማች ወራት እንዲህ አረመኔን ከረባት እና ገበርዲን አጎናጽፈው አደባባይ ማዋላቸው ብቻ ነው። ለዚህ የሰገዱ ኑዛዜወች ደግሞ አደግድገው አገልጋይ ሆነው ማይክ ጨብጠው መገኜታቸው ነው። 1) የተመረተ የእግዚአብሄር አዝመራ የሚያነድ፤ 2) ያለን የሚያራቁት በቅናትም የሚዘርፍ፤ 3) ቅርስን በበቀል የሚያወ