ዬነገረ ዶር ለገሠ ቱሉ መንገድ ሌሎቻችሁ ትማሩበት ዘንድ ነውና አትበሳጩ። #ፋኖ ለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴላችን ነው። ይህ ዛሬ የተፃፈ አይደለም የታገልኩበት መሥመሬ ነው። ዛሬ ጄኒራሉ በርከትከት ሲል ከፍሬ መልስ በጎደለ ላይ ማተኮር የስንዱዋ ሥርጉትሻ አነባቢ መንገዷ ነው።

ዬነገረ ዶር ለገሠ ቱሉ መንገድ ሌሎቻችሁ ትማሩበት ዘንድ ነውና አትበሳጩ።
#ፋኖ ለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴላችን ነው። ይህ ዛሬ የተፃፈ አይደለም የታገልኩበት መሥመሬ ነው። ዛሬ ጄኒራሉ በርከትከት ሲል ከፍሬ መልስ በጎደለ ላይ ማተኮር የስንዱዋ ሥርጉትሻ አነባቢ መንገዷ ነው። 
 
 
"አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን።"
(መዝሙር ፴፱ ቁ ፲፫)
 
 May be an image of 1 person, newsroom and text
ዬሰሞንን የዶር ለገሰ ቱሉን ንግግር አደብ ገዝቼ አዳመጥኩት። የመልስ መልስ ለመስጠት አይደለም ቁም ነገሩ። ተያያዥ ጉዳዮች ወፍ ካወጣቸው ላነሳቸው እችላለሁኝ።
 
በኽረ ጉዳዬ የ፬ ኪሎ መንበር የምታልሙ፤ ይህም ባይሆን በተለያዬ ምክንያታዊ ገጠመኝ ህዝብ እናነቃለን፤ ባለፈም ህዝብ እንመራለን፤ እንዲያም ሲል ኮኦርድኔተር ነን፤ እንዲሁም አቅጣጫ ነዳፊ ነን የምትሉ ሁሉ ምን ተማራችሁበት ከዚህ መሰል ወጣ ገባ፤ ጠራጠሮ ሰብዕና፤ ከዚህ መሰል የኃላፊነት ቦታ ካለ የኢትዮጵያን አንደበት ከወከለ ሰው????
 
በመሪነት ላጫችሁ ይሁን ለታጫችሁ ሁሉ በዶር ለገሰ ቱሉ ቦታ እራሳችሁን አስቀምጡ እና እኔ ብሆን ብላችሁ እራሳችሁን እስኪ መዝኑት። እኔን አይመለከትም። ከዬትኛውም ተቋም ይሁን ተጽዕኖ ፈጣሪ ጋር ግንኙነት ዬለለኝ፦ በመቆጠብ እና እራስን በመግዛት ለራሴ ጥሪ፤ ለተፈጠርኩበት መልዕክት የምታትር ባተሌ ነኝ እና። ዕውቅናው #አይገጠግጠኝም#ውዳሴውም #አያሻቅለኝም። ለዬትኛው የኃላፊነት ቦታም እራሴን አጭቼም አስቀምጬም አላውቅምና።
#ሂደት እና ግጥምጥሞሹ።
ዶር ለገሰ ቱሉን እያዳመጥኩኝ አሁን መድረክ ላይ፤ ሚዲያ ላይ ያሉትን ወገኖቼን ሁሉ በዕዝለ ህሊናዬ ሳስስ ነበር። ምክንያቱም የዚህ መከረኛ ባለቤት አልቦሽ ትውልድ ሮል ሞዴል ምንጩ፤ አቅጣጫው ውሉ ስለሚጠፋኝ።
 
ይህም ብቻ ሳይሆን እምንፈቅደው አዲስ ሥርዓት ቢወለድ ዋዜማውን ሳስብ ይጨንቀኛልና። ከንፍሮ ጥሬ የሚያወጣው አምላክ ካልታደገን በስተቀር ቀልብ የሚርፍበት፤ ሞገሱ እና ማዕረጉ ሰብዕናው ለዚያች ታላቅ አገር ኢትዮጵያ ልኳ?????
 
በሚተቸው፤ በሚብጠለጠለው፤ በሚቃለለው ውስጥ እራስን ማዬት፤ እራስን በሚገራ ሥነ - ምግባር ማሟሸትም ይገባል። አደብ ያጡ፤ ያልሰከኑ ኃሳቦች እና ለጋ የኃላፊነት ጉጉት መስዋዕትነቱን ያገዝፈዋል፤ አግዝፎታልም፦ ዬተስፋ ጊዜም ያራዝማል። አራዝሞታልም። ባልተያያዙ፤ በቅጡ ባልታሹ ግጥምጥሞሽ ሂደትም አሳሩን ሲበላ አስተውላለሁኝ። 
 
ማስተዋል የዕድሜ ጉዳይ አይደለም። በመማር የሚገኙ ክህሎቶች ቢኖሩም፤ መማሩ ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን መጥኖ ካልተገኜ ብላሽ ነው። ልፋትም ዕሴት የሚኖረው በያዝ ለቀቅ፤ ወጥኖ በመተው ሳይሆን የያዙትን አድምቶ ለስኬት ማብቃት መቻል ነው የትውልድ አብነትነት። በስተቀር ልፋቱ የውርንጫ ድካም ይሆናል።
 
#አቤቶ ኦነጋዊ ልሳን። 
 
ወደ ዶር ለገሰ ቱሉ ዬሃሳብ እንዝርት ስመጣ አሁን የናቁት አቅም ለሳቸው ከረባት እና ገበርዲን ያበቃ ትንታግ ማህበረሰብ እንደሆነ ልነግራቸው እሻለሁኝ።
 
የሚገርመው ውክልናው በዚህ በሚዘባበቱበት ዬአማራ ህዝብ ሆኖ ነው እሳቸው ነጋ ጠባ በፋስ አናት አናቱን የሚከተክቱት። በባሩድ የሚቀቅሉት። የሳቸው መንግሥት ፍም አፋፍሞ እዬቀቀለው የሚገኜው ማህበረሰብ ዛሬን ለእነሱ የባረከ፤ ሙሉ ድምፁን የሰጠ ቅዱስ ህዝብ ነው።
 
መመካት ባያስፈልገኝም እንዲህ አንገት ከማያስደፋ ጨዋ እና ቅን ህዝብ በመፈጠሬም አምላኬን አመሰግነዋለሁ። ከሁሉ ሁሉ የምህረት እና የይቅርታ የኔታ ስለሆነ።
 
ቂም እና በቀልን ስለሚጠዬፍ። ዘረፋ እና ቅጥፈት ሃራሙ ስለሆነ። መከራውን ችሎ ተፈጥሯዊነትን ምራኝ ፈርኃ እግዚአብሄር እና አላህን ባርከኝ ስላለ።
 
ቁጭ ብሎ የሰቀለው ጨካኝ ማህበር ይህን ያህል እዬቀጠቀጠው በተፈጠረበት የሰው ልክነቱ ብቻ ተጋድሎውን ማድረጉ ያስደምመኛል። ሱባኤዬም ነው። ቅዳሴዬም ነው። ማህሌቴም ነው። አማራነት ይሁን ፋኖነት ውስጠ ቅኔዬ ነው። ጭምትነቱ የኔታዬ ነው። ደግነቱ ጉልላቴ ነው። 
 
በሌላ በኩል ……
 
ሲያንሰው ነው አማራ አሁን የደረሰበት የመቁረጥ ደረጃ 100 ዲግሪ ፋራናይት መድረሱ። በህይወት እያለሁ እኔን ማታለል አይቻልም። እንዴት ወደ ሥልጣን እንደመጣችሁ ከቅንጣቱ አመክንዮው እስከ ገዘፈው ሂደት በሙሉ አቅሜ የተሳተፍኩበት ነገረ ኩነት ነው።
እንኳንስ ዶር ለገሠ ቱሉ ዶር አብይ አህመድ አሊ ይሁኑ ኦህዴድ ከነመፈጠራችሁም ማንም አያውቅም ነበር። ኦነግ ከሆነ ዕድሜ ለግንቦት 7 ይበል ለወግ ያበቃው እሱ ነበር። 
 
የአማራ የማንነት እና የህልውና ዘርፈ ብዙ ትግሎችን ገርቶ ነው ከዚህ ዬተደረሰው። ዛሬ በአንድ ድምጽ ግሎባሊ ሰርክ፤ ቀንና ሌሊት አማራ አውራ አጀንዳ ነው።
 
የታገልነውም ፍላጎታችን ነጥሮ ይወጣ ዘንድ፤ የፊደል ገበታ ይሆን ዘንድ ነበር። ተጋን አሁን ላለበት ደረጃ ሠርተን ደርሰናል። የጀመረውን ሳይቋጭ ሲታገለን የነበረን ሁሉ ከጎናችን ማሰለፍ ችለናል። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" 
 
በዚህ አጋጣሚ ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው፤ ህብር እና የሲዊዲን የአንድነት የራዲዮ መሰናዶን ከህሊናዬ ላመሰግን እሻለሁኝ። አማራ ማለት ወንጀል በነበረበት ጊዜ ሁሉ ወጀቡን ታግሰው ፁሁፋችን ሲያትሙ፤ ድምፃችን አክብረው ሲያሰሙ የነበሩ ለእኔ ቀንዲሎቼ ናቸው።
ትግላችን #ዛሬኛ አይደለም። ተጋድሏችን አፍለኛ አይደለም። በቅደም ተከተል የጉዟችን ስልት እና ስትራቴጅ በግል ነድፈን የምንተጋ አለንበት። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ #የአዘቦት ሥራ አይደለም።
 
ከህይወታችን ጋር የተዋህደ የሙሉ ጊዜ መደበኛ ሥራችን ነው። ሥራችን ለለት አይደለም። ለዛሬ 10/15/20 ዓመታት ተተኪወቻችን ስለሚኖሩበት ሰላማዊ የተደላደለ ህይወትም ጭምር ነው። በደላችን ምንጩን፤ የመፍትሄ አቅጣጫውን ተዳብሎን ሳይሆን ከውስጡ ውስጣችን የሆነ አንቱ መሥመራችን ነው።
 
የአማራ ልጅ ሆነ አማራን የሚከብሩ ብቁ ኢትዮጵውያን የምር መራራ ትግል ማድረግ ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችንም በጋራ ይጠበቃል። ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ዶር ለገሰ ቱሉ እራሳቸውን ነው #ያዋረዱት። 
 
ቅንጣት ነገር ለአማራ ልጅ የሳቸው ዛቻ፤ ፍጥጫ እና እርግጫ ከጀመርነው የቆረጠ እና የነጠረ ተጋድሎ ከመንገዱ አያወጣውም። እኔ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ። ተደማጯ ብዕሬ ሁሉንም የማድረግ አቅም አላት። የተዘጋ በር ታስከፍታለች። የተከረቸመ ህሊና ቧ ታደርጋለች።
በሌላ በኩል በመላ ኢትዮጵያ አማራን የመንጠር ተግባር አልበቃ ብሎ ህወሃት ቆርምሞ በሰጠው ባዕቱ መቆሚያም መቀመጫም አልሰጥ ብሎ ጥጋቡ ማህበረ ኦነግ አላስችል ብሎ ለፈጠረው ጦርነት ህዝባችን እራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱ ስለመሆኑ ዬተገባ ነው።
ሌላው በእጽህኖት እምገልፀው መሠረታዊ ጉዳይ ከእንግዲህ የአማራ ልጅ በስማ በለው ሊመራ አይችልም። #ፈጽሞ። ተጫኝም አያስፈልገንም።
 
ግርባው ብአዴን በአቶ ተፈራ ዋልዋ፤ በአቶ በረከት ስሞዖን፤ በአቶ አዲሱ ለገሰ፤ በአቶ ደመቀ መኮነን፤ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ ወዘተ ያንዘላዘለው ዘመን በድል ይደመደማል። አሁንም በመንፈስ ልዕልና ላይ ነው እምንገኜው።
 
ትርፋማ ነን። እስኪ ሚዲያው ሁሉ ይዳሰስ አማራ፤ አማራ፤፦ፋኖ፤ ፋኖ ጠረኑ ይህ ነው። አማራነትን የተጠዬፋ መንፈሶች ሁሉ ፈቅደውና ወደው ወደ ቋታችን እዬተመሙ ነው። ይህ ደግሞ የድርጊት ኮከከብ ያበሠረው የዬምሥራች ብሥራተ ዜና ነው። የተስፋ ዋዜማ ላይ እንገኛለን። 
 
ዬአማራ ልጅ ሙሉ ዘመኑ ሥልጣኑን እያሻገረ የሚቀጠቀጥበት ዘመን ከእንግዲህ አይኖርም። ዛቻው፤ መስቃው፤ ዘር ማጽዳቱ፤ ወረራው እና ጫናው በሰከኑ፤ በማይንቦጀቦጁ፤ እዩኝ እዩኝ በማይሉ የአማራ ልጆች ተጋድሎ መልክ ይይዛል። 
 
ጭንቀቴ የአማራ ህዝብ በተሰጠው ልክ የመሆን አቅሙ በሚያስተጓጉሉ #ቱማታወች እክል እንዳይገጥመው ብቻ ነው። ትልቁ ሥራ ተሠርቷል። የኦነግ ኢትዮጵያን ሃይጃክ ያደረገበት መንገድ እና የአቅሙ ልቃቂትን ለክቶ ዕውቅናው በልኩ እንዲሆን ማድረግ ነበር ትጋታችን። ይህ ተከውኗል።
 
በሌላ በኩል የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ልቅናው ከመሪወቹ በላይ መሆን በራሱ ጊዜ የራሱን መሪወች መሬት ላይ ፈጥሯል። ተመስገን።
 
የአማራ ልጅ በዝብሪት እና በፋክክር ጊዜውን የሚያጠፋ ሳይሆን መራራውን ጽዋ በድፍረት መሬት ላይ እዬተጋፈጠው ይገኛል። እጅግ የሚያስደምም ብቃቱ ቀደም ብለን ለተጋን፤ ምሥክርነታችን ለሰጠን ሰብዕናወች አንገት አስደፊ እንዲይሆን አደርጎታል። 
 
የአማራ ሚሥጢር #ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያ ሳይንስ፤ ህግ፤ ፍልስፍና፤ ዕውነት፤ ዩንቨርስ ወዘተ ናት። ስለሆነም ቀና መንገዱ እና ስኬቱ እምዬ ናትና ከሚሥጥሩ የወጣን ዕለት እንወድቃለን። ስለዚህም ጥንቃቄ በብርቱ። 
 
በሌላ በኩል በግራም በቀኝም፤ በፊትም በኋላም የሚወራጩ፤ የሚግረጨረጩ ኩነቶች ሊረባብሹ አይገባም። በአማራ ጉዳይ ያሻውን ያሻውን ይበል። እኛ ሥራችን ላይ እናተኩር። በእኛ ተጋድሎ ሰጪም ነሺም፤
 
ቀዳሽም ቆራሽም ሆኖ የሚገሰግስ ካለ አይቶ እንዳላዩ ማለፍ ነው። ጊዜ አታባክኑ። ታንቲራ አትግጠሙ። ሙያ በልብ እንደ ባለ ቅኔወቹ ጎንደሬወች አባባል መሆን ነው። 
 
መንጠራራት አያስፈልግም። ጥድፊያም አያስፈልግም ተረጋግቶ የራስን ድርሻ መወጣት መርኃችን ሊሆን ይገባል። እኛ እራሳችን ትምህርት ቤት ልንሆን ይገባል። ምስጋናውን፤ ውዳሴውን ለፈጣሪ እንስጥ። የእሱን ታምራት አንጋፋ፤ አንዳፈርም። 
 
በተረፈ ትጥቃችን እንዲጠነክር፤ ያለው ሥርዓት ዘነዘናው እንዲታይ ላደረጉት ለዶር ለገሠ ቱሉ እና ለኦነግ ሊቃናት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ማለት እሻለሁኝ። ከልቤ።
 
ንግግሮቻቸው ያዝናኑኛል። ምን እንዳለን ስለማያውቁ፤ ምን እንደምንችልም ስለማይረዱ። እኛ አማራወች ሳይለንት ማጆሪቲው ውስጥ የምንገኜው ምን እንዳለን እናውቃለን። ምን እንደምንችል እናውቃለን። 
 
ምን እንደሚፈቀድልን እንረዳለን። ምን ደግሞ እንደማይፈቀድልን አሳምረን እንረዳለን። እኛ አደራጅተን መሪ ነን ባዩ በገፍ ሲተም እኛ ወደ ጓዳችን #በክብር እንገባለን። ከእሪካ ሪካው፤ ከውቂ ደብልቂው፤ ከቦክሱም የለንም። ሥራችን ነው መሪያችን። ተግብረን #ሹልክ ነው። ይህ ኃይል ሙያ በልብ ነው። 
 
ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ግዛው ዬEMS ላይ ለኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ቦታውን የሚመጥን ሰው ፍለጋ ሲያማትር አዳምጫለሁኝ። አታሳጡን አይነት። ጥግንግን እና ለብለብ አክትሟል። አጭሩ መልሴ #የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ ነው። ይህ ሥርዓት ኢትዮጵያን አይመጥንም። አሰርውሃውም፤ ልቅላቄውም አያስፈልግም። 
 
እምታገለው እኔ በግሌ ለሥርዓት ለውጥ ብቻ ነው። የትኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባይታዋር የማይሆንባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች። ብቃት ብቻ አገሬን እንዲመራት እሻለሁኝ።
 
ሰውኛ ብቻ እናቴን እንዲመራት እሻለሁኝ። ተፈጥሯዊነት ብቻ እምዬን እንዲያስተዳድራት እሻለሁኝ። አጽናኝ መንፈስ የኢትዮጵያ አድባርን እንዲቃኝ እሻለሁኝ። አይዟችሁ ገዢ እንዲሆን እመኛለሁኝ። ለዚህ ደግሞ በዝምታ ውስጥ ያለ እምቅ አቅም ኢትዮጵያ አላት። ያ ዕምቅ አቅም ኢትዮጵያን ለማዕረግ እንዲያበቃት እተጋለሁኝ።
 
አማራን በሚመለከት ልካችን ስለምናውቅ፤ የመብታችን እና የግዴታችን ጣሬያ እና ግድግዳ #አሳምረን#አስምረንም ስለምንረዳ #ሞግዚት ወይንም ቤቢ ሲተር አያስፈልገንም። በስማ በለው አማራን ከእንግዲህ መምራት አይቻልም እንኳንስ መስቃ እና ዛቻ። ህዝባችን ታሪኩን ያውቃል። 
 
በታሪኩ ልክ የአባት አደሩን መሬት ላይ እዬከወነ ነው። እኛም ውጪ በቀደመ ብቃት ድርሻችን እዬከውን ነው። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል። ሰው ኖረ የሚባለው ለህዝብ ሲያገለግል ብቻ ነው። አገልጋይነት በተለይ በነፃ ሲሆን ደግሞ መታደል ነው።
 
እኛ የአማራ ልጆች መመጣጠን ያልቻለው ከኦነግ ጥብቆ የአመራር አቅም ብቻ ነው። ማንነታችን #ተውሰን፤ ወይንም ማንነታችን #ተወርጀነው ሳይሆን ከውስጡ ውስጥ ሆነን ኑረንበታል። 
 
ማንነት በገብያ ህግ አይተዳደርም። በራስ የመተማመን አቅማችንም ዝቅም፤ ከፍም ሳይል በልኩ ለልኩ ተመጥኖ ተመጣጥኖ የተፈጠረ ምጥን መረቅ ነው። ለዚህም ነው በዚህ ሁሉ ወጀብ ማህል ተከርክመን፤ ተቆጥበን ኢትዮጵያዊ አማራዊ ብሩህ ቀለማችነን በሞገስ ያስቀጠልነው። ትፈሩናላችሁ። ይገባልም። 
 
#መከወኛ ለማህበረ ኦነግ ለእነ ዶር ለገሠ ቱሉ ለእርገት።
 
በመጨረሻ የወሮ ታደሉ ለቅሶ ትናንትና፤ ከስምንት ዓመት በኋላም ከኦህዴድ ነበር፤ ዛሬም ሚሊዮን ወ/ሮ ታደሉ ፈጥራችኋል፤ የኦሮሞ እናቶችንም ደም ዕንባ ታስለቅሳላችሁ ዬገመናችሁ መሸፈኛ እና ማነጣጠሪያም እያደረጋችሁት ነው። 7 ልጆችን ፀንሳ፤፦ በድህነት ወልዳ ያሳደገችን እናት ከመግደል በላይ ምን ልታተርፋለት ይሆን እነ ማህበረ ኦነግ? ማት እና ምጣቶች። 
 
አገር የምትመሩ አትመስሉም። ውኃ በቀጠነ መርበትበት ነው። ድንጋጤው ውጥንቅጣችሁን ያወጣል። በመጨረሻ ቢያንስ አስተካክለው ማንበብ ይችሉ። እራሱን ችሎ ለመናገርም ክህሎት ይጠይቃል። ያረጠ ሰብዕና ነው እኔ ያስተዋልኩት። ተቋማችሁም ማረጡንም።
 
ንግግር እኮ ታለንት ነው። እርግጥ ነው በሥልጠና ክህሎቱን ማምጣት ይቻላል። ለእርስወ ሁሉም አልተሰጠውም። እንደሚያውቁት ከረባትም ገበርዲንም ንግግሩን ሊፈጥም አይችልም። ያለልኩ ሽብሽቦ ነው የሆነው ሁለመና። ጥብቆ። ከውስጠወት ያለውን የጥላቻ እና የበቀል ድፍድፍንም አጉርፈውታል። ኩርፍርፍ።
 
በንቀት ጀመራችሁ በንቀት ዘቀጣችሁ፣ ነገ ደግሞ ያነኮሩትን አስታራቂ ወይንም አዝማች ሆነው ይመጣሉ ጠቅላያችሁ። 
 
"ጎለመስሁ፤፦አረጀሁም
ፃድቅ ሲጣል፤ ዘሩም
እህል ሲለምን አላዬሁም።"
(መዝሙር ፴፮ ቁጥር ፳፭)
 
ክብረቶቼ እንዴት ናችሁልኝ? ሸበላ ሰንበት። ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
(5/11/2023)
 
ምን ያህል እንደተጓዝኩ አላውቀውም፤
ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም፤
አለማወቄን ስጠይቀው፤ አለማወቁን ገለፀልኝ፤
ተስፋን እጠብቃለሁኝ።
 
ከመጀመሪያው ተስፋ መጽሐፌ ሽፋን ላይ የፃፍኩት ነው። ንብረትነቱ የራሴ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።