Nomb 07.2020 ኦ! አትፍረድ።

 

ኦ! አትፍረድ።
ኦ! ፈጣሪ ሆይ እነኛን ቀንበጦች ጠብቅልን። ህይወታቸው ከጨካኞች ታደግልን። አሜን። አንድ ፎቶ አዬሁ። ፎቶ ሾፕ ይሁን፣ ምኞት ይሁን አላውቅም። ከሆነም ምንም የሚያስወቅስ የለውም። በሰው እጅ የወደቀ ከመታዘዝ ውጪ ሌላ ምርጫ የለውም።
የተወካዮች ምክር ቤት በማን ሥር ነው? ስለምን አንደመርም ያሉ የአማራ ሊቃናት ለኮሮና ሞት ተሰጡ? አሁን ቁንጮ ላይ ነው ነገ ወደ ታች ወርዶ አልደመርም ያለሁሉ ካቴና፣ ባሩድ ይበላዋል። ገዳ ውሎው ይኽው ነውና። አትፍረድ ይፈረድብኃል።
ነውም አይደለም ሙግት አያስፈልገውም። ወቀሳም ነቀሳም አያስፈልገውም። ፈጣሪ የፈቀደውን እንደሚያደርግ ማሰብም ይገባል።
እንደ ታሪክ ተመራማሪዎች እኮ ዛሬ ኦሮምያ የተባለው ክልል በገዳ ወረራ የተያዘ ነው። ኗሪውን አስገብረው ቋንቋውን ብቻ ሳይሆን ማንነቱን ገልብጠው ከሰው በታች አድርገው እንደሚገዙት ይታወቃል።
ብዙ ነገር አልገባን አለ እንጂ የባህርዳሩ ሰማዕትነት ይህን ነው የሚነግረን። ባህርዳር ለገዳ ገብራለች። የቀረችው ተገዳዳሪ እቴጌ ትግራይ ነበረች ኦፕሬሽኑ እንደተጠናቀቀ ይሰማኛል።
ህገ መንግሥት የማክበር የማስከበር አይደለም። በህግ የተሠራ ነገር ስላላዬሁ። ህጋዊ መዋቅሩን እራሱ ገዳ አይፈልገውም። ለዲፕሎማሲው ማህበረሰብ አሳቻነት ብቻ ነው ተልዕኮው።
ህግ ማስከበር ሳይሆን ለገዳ ማስገበር እንጂ። ደቡብም የገበረው ሲዳማ ክልል የሆነ ዕለት ነበር። አፋር መሪ ይኑረው አይኑረው አይታወቅም።
ጋንቤላ ፈንጅ እንደዋጠ ነው። ቤንሻንጉል ህብረት የፈጠረ ነው ብቸኛ ፕሬዚዳንቱ ያልተቀዬሩበት ክልል ነው። አመራሩም በዬጊዜው ተጨፍጭፏል። ሱማሌ ከሦስት ተሸንሽና ሙሽርነቷ ያከትማል። 
 No photo description available.
የአዲስ አበባ ወረራም ይህው ነው። የጌዲኦ ታሪክም ይኽው ነው። ቀስ እያለ በመንግሥት ይፋዊ ንቅናቄ የሚሟላው ይኽው የገዳ መንፈስ ነው። አሁን ያለው ግጭትም እነሱ በእነሱ የጎሳ ነው።
ስለዚህ ገዳ አቶ ተመስገን ደስአለኝን አስበህ ይህችን ወጣት ስታስብ አንዱ ፈቅዶ እና ወዶ ለቤተ መንግሥት ሉባ፣ ሌላዋ ተገዳ፣ ታግታ ለጫካው ሉባ ብታድር ለምን ይፈረድባታል? የኢትዮጵያ ካቢኔ ምን እዬሆነ ነው። ዘለግ አድርገህ አስበው ከውስጥህ።
ከሆነ ለወላጆቿ ዓይኗን ማዬታቸው እራሱ መድህን ነው። በህይወት መኖሯ ትልቅ ነገር ነው። እሷ ለሌላም ትፈለጋለች የአማራ ክልልን የጫካው ሉባ ለመጠቅለል መንገድ መሪ ትሆናለች።
ህወኃት ወልቃይት ጠገዴን የወረሰው በወሮ አዜብ መስፍን፣ በኮነሬል ደመቀ ዘውዱ፣ በወሮ ርስቴ ተዘርዝረው በማያልቁ የራሳችን ሰዎች፣ ነበር።
የኩርፊያው ምንጭ መሬት ላራሹ ዓዋጅ እና ደርግ ቁልፍ ተወላጆችን ለመያዝ የወሰደው ግብታዊ እርምጃ ነበር። በዛ ሰዓት ከፊሎቹ ኢህአፓ፣ ከፊሎቹ ኢዲዩው፣ ከፊሎቹ ደግሞ ህወሃትን ተቀላቀሉ። ወደውም ተገደውም።
የሚገርመኝ ታሪክ እራሱን ሲደግም ነው። የሰሞኑ ከትግራይ ጋር ያለው የቤተ መንግሥቱ ሉባ ውጊያም ይኽው ነው። በዚህ ውስጥ መቼ የኢትዮጵያ ወጣቶች ዕድሜያቸው ሳይባክን በፈለጉት ሁኔታ ይኖራሉ ነው ጥያቄ።
ዛሬ ያሉት ሥውሩ ጠቅላይ ሚኒስተር ገዳ አባዱላ ገመዳ ምርኮኛ ነበሩ። ዛሬ ጦሩን የሚመሩት ምርኮኛው ጄኒራል ብርኃኑ ጁላ ምርኮኛ ነበሩ። ጊዜ አጀግኗቸው ጀግናውን የኢትዮጵያ ህዝብ በምርኮኛ መንፈስ የሚመሩት።
እንኳንስ እስክርቢቶ ብቻ የያዙ ቀንበጥ ሸበላዎች ቀርቶ። እዬተሸኜ ባለው ሳምንት 20 አማሮች በዛው በወለጋ ታግተዋል። የእነሱም ዕጣ ይኽው ነው።
ለመሆኑ የታጋች ቤተሰቦች ያለባቸው ጫና፣ ለካቴና መዳረጋቸው፣ ተርፋ የመጣችው ገራገሯ አስምራ ሹምዬስ የት ናት? ለኤርትራ መንግሥት በአደራ ተሰጠችን? የአማራ ወጣቶች ዕጣ ፈንታ እረፍት ይነሳኛል። ሁሉም አይመችም።
ሌሎችስ የት ናቸው? በምን ሁኔታ ይገኛሉ?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ፈጣሪ ሆይ የኢትዮጵያዊነት ዘመን አብቅል። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።