07.11.2021#የአማራ ማዕልቱ አልተፀነሰም።

 

#የአማራ ማዕልቱ አልተፀነሰም።
ማዕልት ቀንና ሌሊት ማለት ነው።
#ወጥ አማራ የተፎካካሪ ፓርቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የድርጅት ማናጀር፣ ሚኒስተር፣ የበጎ ሰው ተሸላሚ ዓይናችሁ አይቷልን?
ስለዘኔወማስሬ መልካም ዜና ከሐበሻ ዩኒቲ አዳምጫለሁ፣ አጭር መልዕክት ነው። አብይን ያመነ ጉም የዘገነ ነው። በዛ ስፈላሰፍ ነበር ያደርኩት። ተስማምተዋል ይላል ዘገባው። ከሆነ ጥሩ ነው። "በሬ ሆይ" እንዳይመጣ።
አንድ እግር ዱር ቤቴ አንድ እግር ከተማ ይሁን አማራን መሪ አልባ ማስቀረት የግንቦትወአብይዝም ታላቁ የዘመኑ ፕሮጀክት ነው።
የኢህአዲግ የግንባሩም ተፎካካሪ የሚባለውም ሊሂቁ የተነካ የለም ሲሾም ሲሸለም፣ የበጎ ሰው ሽልማት ሲሰጠው፣ የቦርድ አባል ሲሆን፣ ሚኒስተር ሲሆን ድርጅቱ ዕውቅና ሲሰጠው፣ በዶላር ሲደጎም፣ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ እንዲያውቀው መድረክ ሲመቻችለት አይተናል። አስተውለናል። ይህን ዕድል በርቁቅ መንገድ ያገኙትን አይተናል።
የአማራ ሊሂቃን ሲሳደድ፣ ሲታሰር፣ ሲታገት ይህ ነው እንቅልፍ ነስቶኝ ያደረ። ለምን? አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ አቶ ኃይለማርያም ደሴ ይንጎራደዳሉ? የቀደሙት የብአዴን ሹመኞች ከሥልጣን ገሸሽ ተደርገው አሉ እነ ገዳ ንጉሱ ጥላሁን እነ አቶ አዲሱ ወዘተ ……
ዶር አንባቸው መኮነን የምስጥ ሲሳይ ሆኗል እስከ ቲሙ። ሁለት አባል ያለው የዶር አረጋይ በርሄ ፓርቲ በዕውቅና የአባይን ፕሮጀክት ይመራል። አቶ እስክንድር ነጋ ለ12 ጊዜ ከቲሙ ጋር ታስሮ ካልገደልነው ብለው በተራ ወንበዴ እዬተገለገሉ ነው ዶር አብይ አህመድ።
20 ዓመት ተደራጅቶ አዲስ ኃሳብ በማፍለቅ የማይታክተው፣ ግን በጠራራ ጠሐይ የሚዘረፈው የኢትዮጵያ ዕድል ፈር ቀያሽ የሆነው ኢዴፓ ዲስማንትል ሆኖ የዶር በዬነ ጴጥሮስ ፓርቲ ተሹሞ ድርጅቱ ቀጥሏል። ጫካ የነበረው ኦነግ እና ግንቦት 7 እንደ አቅማቸው የሚርነት ቦታ አግኝተዋል።
ኦፌኮም ተቆላምጦ መሪው መኪናም፣ ቤትም ተሸልመው። የክት እና የዘወትር የቦርድ አባል ሆነው። በይፋ እና በአደባባይ የኦሮምያ የሽግግር መንግሥት ከኦነግ ጋር መሥርቶ ህገ ወጥ ሳይባል ቢዛ ተሰጥቶት አሜሪካ ይንጎራደዳል።
የአማራ ልጆች ወገናቸው በግራ በቀኝ በኦህዴድ መራሹ የጫካ ክንፍ ኦነግ በህወኃት፣ መተከል በጉምዝ እዬተሰቃዬ መንግሥትን በሞቴ ልገዝ ሲል አዝማችህን ልሰር? ልክሰስ?
ሰላሙን ልወክ? የኔታ አቻም እንደዘገበው 10000 ሺህ የሰለጠነ በትኖ ያልሰለጠነ ክተት፣ ጎንደር ማይፀምሪ፣ ዋልድባ፣ ዛሪማ እያለበት ወሎ ዝመት?
የአማራ ልጅ በቀዩ እንደ ቅጠል እዬረገፈ ከስሜን አሜሪካ የመጡ የኦነግ ልጆች በዶላር ሲንፈራሰሱ እስር ቤት የባጁት፣ በኤርትራ በርኃ የባጁት መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና አርበኛ ዘመኔ ካሴ ወደ ሞት እንሂድ ባሉ ኳራንቲ አስገብተን የሃሳብ ጥበባችሁን ካላገትን ብለው ይታገሏቸዋል።
አማራ ወደዬት ይሂድላቸው። በአንድ ወቅት በድፍረት ይሞግቱ የነበሩ ርትዑ ዶር ደረጀ ዘለቀ ምን እንደዋጣቸው አላውቅም። ለዚህ ነው እኔ የአማራ ቀኑ አልተፀነሰም የምለው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/11/2021
አማራ አልቆ የሚቀር ህዝብም አገርም ካለ ይታያል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።