#የአብሽ ቡና።

 

ዕለተ ሰንበት እናትነት በቅንነት ለውስጥነት።
#የአብሽ ቡና።
ስለአብሽ የጀምርኩት ነበር።
ዛሬ ይከወናል።
ግን እንደምን አደራችሁ? ደህና ናችሁን?
#አብሽ እና ቡና።
አብሽን ጭልጋ ገበሬ መንደር እንደቡና ሲጠቀሙበት አይቻለሁኝ። መንደሩን አልጠቅሰውም።
ቡናው እዬተቆላ አብሹ ተጨመረ። ልኩን አይተው አወረዱት። ጠረኑ ስርንቅ ነበር። ተወገጠ። ተፈላ። እኔም ታደምኩበት። በጣም ይመራል። ብልኃት ይኖረዋል። የጤና ትሩፋት። እዚህ መጥቼ የተለያዩ አገር ቡናወች ጋር እዬቀላቀልኩ ጣዕሙን ለማምጣት ሞክሬያለሁኝ።
ከአንድ ኮንብኔሽን ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ። ያው እንደነገርኳችሁ። ቤቴ ውስጥ በዚህ መሰል ጉዳይም አተኩራለሁ። እራሴን እንደ አንድ ኦብጀክት ወስጄ ማለት ነው።
ገበሬው ቡናን በጥሬጨው፣ በጣዝማ፣ በማር ወይ በባዶ ይጠጣል።
ጣዝማ ከማር ይገረምማል። ይከብዳል። ለጤናም ልዩ ነው።
ጥሬጨው ማህል አገር ጨው እምትሉት ነው። ከእኛ ጨው አይባልም ጥሬጨው ነው።
ትክክለኛ አማርኛ ትርጉሙም ይህ ነው። ሌላ የጨው ዓይነትም አለ። አሞሌ ጨው የሚባል። ለከብት የሚሰጥ።
የሆነ ሆኖ የአብሽ ቡና ጠቀሜታውን ጠይቄ ባልረዳም ገበሬወች እንደሚጠቀሙበት አይቻለሁ። በስኳርም ሆኖ እጅግ በጣም ይመራል። ቤት ስመለስ ሞከርኩት ይመራል።
በዚህ ይከወን። ደህና ሁኑ። መልካም ሰንበት። ቸር ወሬ ያሰማን አሜን።
#ፎቶው ከአቶ ሰንጋ ተራ ፔጅ ያገኜሁት ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/11/2021
ኑሩልኝ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።