ወጣት አቶ ፋሲል ጌትነት ታረቀኝ ያያችሁ የሰማችሁ? Nomber 16.2020
ወጣት አቶ ፋሲል ጌትነት ታረቀኝ ያያችሁ የሰማችሁ?
ይህ ወጣት ፋሲል ጌትነት ታረቀኝ ይባላል፣ ይህ የሚያሳሳ ቀንበጥ ወሮ ቀለቤ ሥዩም ስትታሰር ታፍኖ የተሰወረ ነው። ለቀለቤ ዋርሳ ነው። ዋርሳ ማለት የባለቤት ወንድም ማለት ነው። እናት አለው።
እኒህ እናት ትክን ብለው፣ ኩርምት ብለው ደጅ ደጁን ያያሉ። ይመጣልኛል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። ያ ባዕት ተፈጥሮው ለአማፅያን ምቹ ስለሆነ የመጣ የሄደው ሁሉ የሥልጣኑ ማርጊያ በዚህ ባዕት የደም ፍሳሽ ነው። አሁንም መቀጠሉ ማህፀንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል።
የሚገርመው ጠቅላዩ በጥርሱ የያዙትም ይህን ባዕት ነው። ከዚህ ባዕት ልጅ ብቅ ብሎ እንዲታይ አይፈለገም። አጨዱት። ሰው መስለውኝ እንዲህ እንደ ባሎን ቅትት ሳይሉ፣ ሞድ ቤት ሳይከፍቱ የኦህዴድ የፅህፈት ኃላፊ ሳሉ ዘርዝሬ ፅፌላቸው ነበር የጎንደር እናትን የመከራ የውኃ ልክ። ትርፋ ቅጣት ሆነ እንጂ።
የሆነ ሆኑ ይህን ወጣት ያለበትን ሁኔታ የምታውቁ እባካችሁ እናቱን በቃሽ እንባ በሏቸው። የከፋም ነገር ካለ ንገሯቸው። ሽዋ ውስጥ የተሰወሩ የአንድ ቤተሰብ አራት ወጣቶች ድብዛቸው አልተገኜም። አጀንዳው የሆነ አካል የለም። ተረስተዋል። ትውልድ የማይተካው ሊቅ አቶ በዓሉ ግርማም እንዲሁ።
እጅግ የሚያሳዝነው የወጣት ፋሲል ጌትነት ታረቀኝ ወንድም የትዳር አጋር የሰላም አንባሳደር ወሮ ቀለቤ ስዩም አራሷ አሁንም እስር ቤት ናት። አማቷ ስለልጃቸውም ስለምራታቸው አሁንም ጭንቅ ላይ ናቸው።
የጎንደር የአማራ እናት ሁልጊዜ የልጅ ሊኳንዳ ቤት እንደተከፈተባት ነው። አሁንም የሚሞተው እሱው ነው። ለዛውም እሱን ለሚያጠፋ አውሬ መንፈስ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እናት ሆይ መቼ ይሆን ቀንሽ?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ