ሆዴን ባር ባር ቢለውም። ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን።
ሆዴን ባር ባር ቢለውም። ይህን ፍፅምና ትህትና ነው እያሰደደው ያለው የቤተ - መንግሥቱ ደራጎን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ለምን ስለምን ሆዴን ባር ባር አለው? ብፁዓንን ሳይ፣ ይህን አውሬ ሥርዓት ሳስብ፣ ቅንጣት ስለማላምነው እንደ ሌላው ሁለመናችን እንዳያራግፈን እሰጋለሁኝ። እንዳያሳጣን እሰጋለሁ። እንደዚህ ዘመን ብፁዓን አቨው በሥጋ በብዛት የተለዩበት ጊዜ የለም። በአራት ዓመት ውስጥ ብዙ ነገር አጥተናል። አውሬ ዘመን ነውና። ስልቱን አናውቀውም። ይፈፀማል ዕንባችን አፍሰን ዝም እንላለን። ለማስተዋል፣ ለጥሞና ጊዜ ወስደን አናውቅም። እንጂ ለተዋህዶ ምፃዕት ዘመን ላይ ነን። አጥንተውናል። በአጠኑን ልክ በስውር እያጠቁን ነው። ዛሬ እምናዬው መልካም ነገር የነገ #ሃዘን እንዳይሆን እሰጋለሁኝ። ምነው በቀረብን እንዳንል። ብፁዑ አባታችን አቡነ አብርኃም አጽናኛችን፣ ጥጋችን፣ በከፋን ሰዓት ከጎናችን የማይለዩትን ሳይ ሆድ ይብሰኛል። ለሳቸውም ለእኛም የመኖር ዋስትና ባህርዳር ምርጫዬ ነበር። ይህን ሥርዓት አናውቀውም። ከአጠቃን በኋላ ነው የሚገባን። ስንቀደም እንጂ #ቀድመነው አናውቅም። እና መጪው ጊዜን ፈራሁት። ብፁዑ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ (ዶር) እሳቸውም ቢሆኑ በፈተና የፀደዩ፣ ርትፁ ናቸው። ልስሉስ። የእኛ፣ የውስጥ ናቸው። ቅርባችን ናቸው። የእሳቸውም ህይወት ያሳስበኛል። ይህን ሥርዓት አምኖ #ልብ #መጣል አይገባም ባይ ነኝ። ከፈጣሪ በታች። ይህ ድንቅ ሥራ የፈጣሪ ቢሆንም ዲያቢሎስ የሰፈነበት የቤተ - መንግሥቱ ዓውድን ግን አላምነውም። እርቅ እና ውጤቱ እኛ በቅንነት ብናዬውም የሆነው ነገር ዘለግ ብሎ ታስቦበት፣ ለአንድ ትርፍ ወዘተረፈ ኪሳራ ተደራጅቶ አይቻለሁኝ። እናም እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ ውስጤ በስክነት፣ በአትኩሮት ከመከታተል ው