ልጥፎች

ቅዱስ መርቆሪዮስ

ምስል
  ቅዱስ መርቆሪዮስ    ሰመዓቱ ቅዱስ መርቆሪዮስ ከአባቱ ሎሪዮ እና ከእናቱ ክርስቲና በ271 ዓ.ም ጣሊያን ሮም ውስጥ ነበር የተወለደው። ወቅቱ ክርስትና ገና ያልተስፋፋበት እና ጣኦት አምልኮ የነገሠበት ዘመን በመሆኑ ቤተሰቦቹ እና የሮማ ገዥዎች ሁሉ ጣኦት አምላኪ አረማውያን ነበሩ። ቅዱስ መርቆሪዮስ በክርስትና ሀይማኖት አምኖ ሲጠመቅ ፕሉፖዴር (የእግዚአብሔር አገልጋይ) ተብሏል። ቅዱስ መርቆሪዮስ አባቱ እንደሞተ የጦር መሪነት ስልጣኑን ተረክቦ ከሮም ንጉሥ ዳኪዮስ ጋር ተቀናቃኝ ጠላትን ለማጥፋት ዘምቷል። በጦርነቱ ድል አድርገው እንደተመለሱ ንጉሡ ድል እንዳደርግ ለረዱኝ ጣኦታት መስዋዕት አቀርባለሁ ብሎ በደገሰ ጊዜ ቅዱስ መርቆሪዮስ ይቃወማል። ለኢየሱስ ክርስቶስ ካልሆነ ለጦኦት አልሰግድም፣ መስዋዕትም አላቀርብም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው መከራ ይፈፀምበታል። ቅዱስ መርቆሪዮስ ነገሥታቱ የሚፈጽሙበትን መከራ ሁሉ በጸጋ ተቀብሎ በክርስትና ሀይማኖቱ እንደፀና ህዳር 25 ቀን 310 ዓ.ም ሰማዕት ሁኗል። ቅዱስ መርቆሪዮስ ለክርስትና ሀይማኖት የከፈለው መስዋዕትነት በመላው ዓለም የጽናት ምልክት ሁኖ ተሰብኳል። የዓለም አብያተ ክርስቲያናትም መርቆሪዮስን ቅዱስ ብለው ሰይመውታል። የቅዱስ መርቆሪዮስ ክርስቲያናዊ ተጋድሎን አምነው ከተቀበሉ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መካከል የኢትዮጵያ እርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት። ቅዱስ ላሊበላ 11ዱን አስደናቂ አብያተ ክርስቲያናት ሲፈለፍል የአንዱን ፍልፍል ቤተ ክርስቲያ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ "ቤተ መርቆሪዮስ" ብሎ ሰይሞታል። በሸዋ እና ጎጃም አብያተ ክርስቲያናት በቅዱስ መርቆሪዮስ ስም ተሰርተዋል። በቤጌ ምድር ደግሞ ቅዱስ መርቆሪዮስ ከነፈረሱ እየተዘከረ ዛሬን ደርሶል። ቅዱስ

ማርከሻ መረጃ የዶር አብይን ቁዘማ ፋርሽ ዬሚያደርግ።

ምስል
ማርከሻ መረጃ የዶር አብይን ቁዘማ ፋርሽ ዬሚያደርግ። ከአቶ እኔ እና አባቴ ያገኜሁት ነው።   "ከግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ የተተረጎሙ መጻሕፍት" -"ለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የተዘጋጀ ከግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ የተተረጎሙ መጻሕፍት በከፊል -ጥቆማ ላደረጋችሁ አመሰግናለሁ፡፡ የተተረጎመልንን እናንብብ፡፡ ተርጓሚያን ተጨማሪ ሥራ ለመሥራት በርቱ፡፡ እውነት ለምዕመናን የሚቆጭ ሰው በሆነው ባልሆነው ከማለቃቀስ ይልቅ የድርሻን መሥራት ይገባል፡፡ -በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሁነን መጻሕፍትን ለምዕመናን ተደራሽ ለማድረግ የምንችለውን ያህል ማን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ የትርጉም ሥራ እንዳንሠራ እጃችንን ያዘን? " "1. ውዳሴ ማርያም (Galata Maariyaam) 2. ዓምደ ሃይማኖት (Utubaa Amantaa) 3. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Seenaa Mana Kiristaanaa Ortodooks Tawaahidoo Itiyoophiyaa)፣ 4. ፍኖተ ቅዱሳን (Daandii Qulqullootaa)፣ 5. ክርስቶስ ኢየሱስ ማን ነው? (Kiristoos Iyyesuus Eenyudha?)፣ 6. ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ (Deessuun Waaqaa Kitaaba Qulqulluun)፣ 7. ነገረ ቅዱሳን (Dubbii Qulqullootaa)፣ 8. ውዳሴ አምላክ (Galata Waaqaa)፣ 9. ፍኖተ አሚን /ቁጥር-1 እና ቁጥር-2) (Daandii Amantii)፣ 10. ነገረ ሃይማኖት (Dubbii Amantaa)፣ 11. የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ (Seenaa Mana Kiristaanaa Sadarkaa Addunyaatti)፣ 12. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን (Sirna M

አዲስ #ምዕራፍ። እዮባዊቷ ዬኢትዮጵያ ቅዱስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህግ ባለሙያ ልጆቿን ጠርታለች።

ምስል
#አዲስ #ምዕራፍ ። እዮባዊቷ ዬኢትዮጵያ ቅዱስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህግ ባለሙያ ልጆቿን ጠርታለች። ዬእግድ አቤቱታክስ ለመመስረት መሰናዶ የማሟላት ሰላማዊ ሂደት …… ማህበረ ምዕመኑም ህግን እንዳይተላለፋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ቃለ አቃባዩ በአፅህኖት ገልፀዋል።    ትንታግ ልጆቿ ከዓይን ያውጣቸው። አሜን። ይደንቃል የትውልዱ አቅም ምራቁን የወጣ መሆኑን። በጣም ዬተደራጀ የተቀናጀ ነው። ህግ አውጪውን፣ ህግ አስፈፃሚውን፣ የህግ ተርጓሚ አካል ፍትህ ይሰጠናል ብለን እናምናለን። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" በዝምታ ውስጥ የባጀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ማህበረ ምዕመናን ማተቤ ይቀድማል እያለ ነው። እዮባዊቷም ታጋሽነቷ፤ ችሎታዋን በህግ፤ በሥርዓት ይፈታ ዘንድ በደሏን ለህግ ልታቀርብ ነው። ጠበቃ አቶ አንዱዓለም ዓወቀ በሰብሳቢነት ዬሚሳተፋበት የህግ ሂደቱን መጀመሩን ይገልፃሉ። "መንግሥት አይከሰሰ ሰማይ አይታረስ የሚለው ብሂል እያለቀበት ነው" ይላሉ ዬአደበባይ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ መላከ ኤዶም ቀሲስ ኤፍሬም እሸቱ። ቃለ ምልልሱን አደባባይ ሚዲያ ላይ ታገኙታለችሁ። ስንዱዋ ዬተደራጀ፤ ዬተቀናጀ ተግባር ዬተፈፀመ ነው። ዬእኔ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃዋ አይለያቸው አሜን። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዬኦሮምያ መስተዳደር በሥሩ ያሉ ሚዲያወች ለህገ ወጡ አካል አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ መተላለፋ ታውቋል። OBN አብሮ ነበር ይቀጥላል። ጋሜ የሚባል በገዳ ጉዳይ ዬሚሠራ ሚዲያውም ይከውናል። በፀሎት እንተጋገዝ። • https://www.youtube.com/watch?v=tnQk5wswL9A MK TV || ቀጥታ ሥርጭት ከቤተ ክህነት ወስባኃት ለእግዚአብሄር።

ስለ ብፁዑ አባታችን አባ ህግጋት አቡነ አብርኃም ዬተፃፈ ነው።

ምስል
  ስለ ብፁዑ አባታችን አባ ህግጋት አቡነ አብርኃም ዬተፃፈ ነው።   ለዚህ ነው እኮ ሲመረጡ ሐሴት ያገኜነው። ዬእኔ ድንግል ትጠብቅልን። አሜን። ከአቶ ቻላቸው አታላይ ያገኜሁት ነው። ዛሬ ደክሞኛል ነገ ይነበባል። "እጅግ የምናከብረው መምህርና ዲያቆን Birhanu Admass Anleye እንደፃፈው " ==================================== አቡነ አብርሃም ሥራ አስኪያጅ ባይሆኑ ኖሮ "ሰሞኑን ጉዳዩን እንዲህ ተይዞ ቢሆን ፣ እንዲህ ተደረጎ ቢሆን እዚህ አይደርስም ነበር የሚሉ አንዳንድ ሀሳቦችን አደምጣለሁ። ሀሳቦቹን ከሚሰነዝሩት አንዳንዶቹ በቅንነት ሊሆን ይችላል። ቢያንስ የጥቂቶቹን ግን ከተንኮል ሊሆን እንደሚችል እገነዘባለሁ። ሀሳቦቹ ከላይ ከላይ ሲታዩ የአስተዋይነት የሚመስሉ ቢሆንም ስናስተውላቸው ደግሞ ለመከፋፈል እና በቤተ ክርስቲያኒቱ በኩል ያለውን ድጋፉን ለመቀነስም ይመስላል። ለማንኛውም ባለፈው ስለ ባዕድ እጅ ስጽፍ የተውኳትን አንዲት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ በማቅረብ ነገሩ ምን ያህል የታሰበበት እና አለፍ ያለ ዕቅድም ያለው እንደሆነ ለማሳየት ልሞክር። ይህ ችግር ከተፈጠረ ጀምሮ ከዚያኛው ወገን ያሉት አንዳንድ ሰዎች ለጥፋቱ ዋና ተጠያቂ አድርገው ከሚያቀርቧቸው አንዱ አቡነ አብርሃም ናቸው። በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስም በስም ጠርተው ሁሉንም ናቸው ያሏቸውም አቡነ አብርሃምን ነው። ይህን የመሰለውን ሀሳብ መጀመሪያ አካባቢ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለ ሃይማኖት በአሁን ስማቸው መርጌታ አውላቸው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተነሡበት ሁኔታ በጥብቅ ከአቡነ አብርሃም ጋር ተደጋግም ስለሚነሣ ያንን የሚሉ መስሎኝ ነበር። ነገሩን ስናጠናው ግን ቀደም ያለ ነበር። የቀድሞው አባ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪ

"ዬችግር መፍቻችን፤ መውጫ በራችንም ህጋችን። ህግ ያድናል ይገድላል። ህግን መክሰስ አንደማይቻል ዬታመነ ነው። " (ብፁዑ አቡነ ኤልያስ።)

  "ዬችግር መፍቻችን፤ መውጫ በራችንም ህጋችን። ህግ ያድናል ይገድላል። ህግን መክሰስ አንደማይቻል ዬታመነ ነው። " (ብፁዑ አቡነ ኤልያስ።) "ቀኖና አይረዝም አያጥርም ይተረጓማል እንጂ።" (ብፁዑ አቡነ ሚኬኤል።) "አቨው መምህራን አባቶቻችን ከዬት መጣህ ብለው አይጠይቁንም። "መምህርህ ማን ነበሩ?" በማለት ነው ያሰተማሩን። "ከዬት ነህ?" ስትባሉም ከኢትዮጵያ፤ "ወዴት ትሄዳለህ?" ስትባሉም ወደ ኢትዮጵያ ይህን አዋህደው አሳድገውናል።" (ብፁዑ አቡነ ማርቆስ።) " ቀኖና እና ሃይማኖት ተመጋጋቢወች ናቸው። ቀኖና ሃይማኖትን ዬሚተረጉም ነው። ቤተክርስትያን በቋንቋ፤ በጎሳ አትሰፈርም! አትለካም!" (ብፁዑ አቡነ ድሜጥሮስ።) (አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።) ተመስገንም። ዬብፁዓን አቨው በረከት፤ ረድኤት ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን። ጥብቅ ማሳሰቢያ ሼር ማድረግ በአክብሮት ዬምሻው ነው። ኮፒ አድርጎ ድካሜን መዝረፍ ግን አይፈቀድም። ለታሪክ የሚቀመጥበት ቦታ ስላለ ነው። አድካሚውን ዘርፍ ዬመረጥኩት። ስለዚህ ለትልልፍ መልሴ መራራ ስንብት ነው። ሌላ ለቀለጤ ታዳሚ ሥርጉተ ምርጫችሁ አትሁን። ቆፍጣና፤ ዬቆረጠ፤ ዬፀና ሰው ብቻ ነው ቤተ ሥርጉተ መቆዬት ዬሚችለው። ትዕዛዝም መስጠት አይቻልም። የምትሹትን ብራናውም ብዕሩም አላችሁ በግላችሁ ጣፋት። እኔ በውራጅ ማንነት አልተፈጠርኩም። እኔ እኔ ብቻ ነኝ። በውስጤ ያለሁት እኔ ሥርጉተሥላሴ ሰብለ ሕይወት ብቻ ነኝ። የራሴ እንደራሴ እኔው ብቻ ነኝ። የብፁዓን አቨው ቃለ ህይወት እንሆ። …… መዳኛችን በማስተዋል ማድመጥ ያደመጥነውን መዋጥ። " ከፈተናው ጋራ መውጫውን ይሰጣችኋል ተጽፏል። ከፈተናው ጋራ መውጫውን እ

MK TV || ቀጥታ ሥርጭት ከቤተ ክህነት

ምስል

አክሊላዊት፨

ምስል

አክሊላዊት፨

ምስል

MK TV || ወቅታዊ ጉዳይ || የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ መግለጫ

ምስል

የዋሺንግተን ዲሲ ሰልፍ የቀጥታ ሥርጭት|| ቤተ ክርስቲያንን ያሸነፈ መንግሥት አልነበረም፤ አይኖርምም

ምስል

የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል::

የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል:: "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን ይልቁንም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ልዩነት አጥፍቶ የሰው ልጅ ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ በአንድነት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ የተጠመቁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲሆኑ ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤ ምንም እንኳ ከቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲየን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት ጥቃት፣ እና የመፈንቅለ

ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም። ፈፅሞ።

ምስል
  ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም ። ፈፅሞ። #የአቡነ ሳዊሮስ ጉዞ አሪወሳዊ ነው። መፈንቅለ ኢትዮጵያ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ባጃችሁ ክብሮች። ለእኔ አዲስ ነገር የለውም። ያስደነገጠኝ ነገር ዬለም። ለምን? ምክንያታዊ ስለሆነ። ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ በውል ስለተገነዘብኩት። ኢትዮጵያ መፈንቅል እንደ ተካሄደባት አምስት ዓመት ሙሉ ላልተገለጠል ይህ መቀስቀሻ ይሆንለታል። እንጂ በኢህአዴግ ኦነግ መፈንቅል አካሂዷል። በስልት እያለዘዙ ሲያጓጉዙ ባጅተዋል። የሆነ ሆኖ ……… 1) ዬዘመኑ የዬፖለቲካ ባህሪን ገና ከጥዋቱ አቋም ስለያዝኩበት አልደነግጥም። ዬሚሆነው የሚሆነው ከሥርዓቱ ባህሪ ነው። የገዳ ታሪክ ጽልመት ነው። ድሉ በደም ዋንጫ ዬቀለመ ማፍረስ፤ ማቃጠል፤ ማውደም። ስንቁ ቀውስ። ዬሚገርመው ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ከዶር አብይ አህመድ የሥልጣን ሱስ ቀለም ነው በማለት የሚተነትኑ አሉ። "ዬተረኝነት" ዬሚሉትም አሉ። ይህ መሰል አዝለኝ ቁጭ አድርጎ እዬነዳ ናደ። አሉታዊ ዴሞግራፊን ዕውን ላደረገ ሥርዓት ማስታመሙ የመከራ ማባዣ ነው። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አፈጣጠር እና ውድቀቱ መነሻው አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። መስፋፋት፣ ወረራ፣ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን አስኳሉ ፋሺዝም ነው። ይህን በጥዋቱ አይቻለሁኝ። ስለዚህም አቅሜ አይባክንም። መንፈሴም አይናወጠም። ተከታዮቼንም በሰከነ መስመር ይጓዙ ዘንድ አስተምሬያለሁ። ያባከንኩት ጊዜ የለም። በአደብ ማጥናት፤ ማዳመጥ ሲያሰኜኝ ጊዜ ወስጄ ጥሞና ዕወስዳለሁኝ። ላንካካ ዬማልሻቸው ጉዳዮች ሲኖሩም ተከታዮቼ መንፈሳቸው እንዳይጎዳብኝ ዝም እላለ

እዮባዊቷ ቅድስታችን።

ምስል
እዮባዊቷ ቅድስታችን። በማዕከላዊ መንግሥት ሁነኛ ልጅ የሌላት እናታችን። አባቶቻችን ቅድስና አላነሳቸውም። አቨው ልቅና አልጎደለባቸውም። ብፁዓን መንፈሳዊ ፀጋ አልሳሳባቸውም። ደናግላን ገሃዳዊ የቀለም ትምህርትም አልነጠፈባቸውም። ሁሉም አላቸው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   አንዳንድ ነገር አዳመጥኩኝ። ቀረ፣ ጎደለ ስለሚባለው አመክንዮ። ግፍ ነው። በጣም። እርግማን እንዳይሆንም ፈጣሪ ይርዳን። አሜን። ብፁዑ አቡነ ኤርምያስ የሠሩት ገድል በቂ ነው፣ የማስተዳደር፣ የመምራት፣ የማደራጀት፣ የርህራሄ ክህሎታቸውን አይተንበታል። ይህ ሁሉ ሰርክ በግብረ ሰላም ዬሚሽሞነሞነው ዘመነኛ ባለስልጣን ሁሉ የሳቸውን ሲሶ ያክል አቅም ቢኖር የሚሊዮን ደም እና ዕንባ በቅድስት አገር ኢትዮጵያ ምድር ባላጎረፈ ነበር። በብዙ እኮ ተዋርደናል። አንገታችንም ተደፍቷል። ዬእኛ አባቶች ተረጋግተው ጥሪያቸውን እንዳይከውኑ ዘጠኝ አብያተ ቤተ ክርስትያናት በጅጅጋ በማቃጠል፣ በማንደድ ነበር የአብይዝም ዘመን አህዱ ያለው። ብፁዑዓኑ አበው አንድም ወር፣ አንድም ወቅት፣ አንድም ሳምንት፣ አንድም ዓመት፣ አንድም ጊዜ ከወከባ እርፍ ብለው ተረጋግተው የአደባባይ በዓላትን ያከበሩበት ጊዜ አልነበረም። አስተዳደራቸውን ሰክነው ለመምራት አልታደሉም። እነሱን የሚዋጋ የሰለጠነ ሾተላይ ዘመን ላይ ነውና የባጁት። በርካታ ቤተ መቅደሶች ሹግ ሆነዋል። ማህበረ ምዕመኑ፣ ማህበረ ካህናት እስከ ቤተሰቦቻቸው ሰማዕትነት በተለያዬ ጊዜ ተቀብለዋል። ሰብሳቢም የላቸውም። አጥቢያ አድባራት ዬፈረሱት ፈርሰው፣ የቀሩት ተዘግተዋል። ማህበረ ምዕመኑ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በሃዘን፣ በዕንባ፣ በዋይታ ዬከተመ ዘመነ ምፅዓት። እንደዚህ ዘመንም በርከት ባለ ሁኔታ ብፁዑ ቅዱሳን ጳጳሳት በሥጋ ዬተለዩን ዘመን የለም። አ

ዬኦሮሞ ልጆች በጥዋቱ ዕውነትን ወግነው ቁመዋል። ህወሃት 27 ዓመት ያን ሁሉ ማት ሲያወርድ ይህን መሰል የተጋሩ ሊቃናት ሲጋፈጡ አላዬሁም።

  ዬኦሮሞ ልጆች በጥዋቱ ዕውነትን ወግነው ቁመዋል። ህወሃት 27 ዓመት ያን ሁሉ ማት ሲያወርድ ይህን መሰል የተጋሩ ሊቃናት ሲጋፈጡ አላዬሁም። የኦሮሞ ልጆች ግን በግል የሚሰማቸውን ሳይቀር ገና በጥዋቱ ነው ፊት ለፊት ወጥተው የተቃወሙት። በአገራቸው በኢትዮጵያ ያላቸው ውስጥነት እራሳቸውን ማግደው ነው የሚታገሉት። ዛሬ ብቻ አይደለም። ባለፋት የመከራ ዓመታት ሚዲያ ያገኙ እህት ወንድሞቻችንፊት ለፊት፣ ገጥ ለገጥ ወጥተው ይቅርታ ሁሉ ጠይቀዋል። እስከዚህች ቀን ድረስ ከተጋሩ አልሰማነም። አሁን እንኳን በኦህዴድ እዬተቀጠቀጡ ሞት የተፈረደበትን አማራን ሲከሱ ውለው ያድራሉ። ይህም ብቻ አይደለም በመተማ፣ በሁመራ ከሱዳን ጋር የሚያጠፋት ጥፋት፣ በጦር ባጠቁት ዬአማራ፣ የአፋር ላደረሱት ጥፋት ውግዘትም፣ ፀፀትም ዬለም። 30 ዓመት ሙሉ። የኦሮሞ ሊሂቃን ግንፊት ለፊት የወጡት ማልደው ነው። በቅድስት ተዋህዶ ፈተናም በጥንካሬ፣ በብርታት እዬሞገቱ ነው። ዝንፍ አላሉም። እዬተከታተልኩት ነው። ውስጣቸው ሲነድ ይታያል። እንደ አንድ አደራጅ እኔ ያዬሁት ይህንዕውነት ነው። ይህ ተው ኢትዮጵያዊነት፣ አገራዊነት፣ ብሄራዊነት። " ዬቤትህ ቅናት በላኝ። " መልካም ምሽት። ዬጠነከረ ዬተደሞ ጊዜ እመኛለሁኝ። ሥርጉትሻ አገልጋይ። • https://www.youtube.com/watch?v=8NMi8JjO_Pw ሰበር ዜና የኦሮሞ ተወላጅ የሆነችው ሜቲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዘረኝነት እና ተረኝነት በአደባባይ አጋለጠች ! • https: