ልጥፎች

ለአሜሪካ የዐቢይ አደገኛ መሪነት ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው

ምስል

ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦

ምስል
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦ አዲስ አበባ። "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭)     ዶር ዳንኤል ሆይ! በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ። 1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ። 2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም። 3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ የጥቃቱ ሰለባ፤ ዒላማም ሆነዋል። ለምን?

ቤተ - የዕብደት አለሎ!

ምስል
  ቤተ - የዕብደት አለሎ! ቤተ - የበቀል ካስማ። ቤተ - የፍርሰት ናዳ! ቤተ የኢትዮጵያ ቅብረት - የሞት ድንኳንኛ። ቤተ - የሴ ራ የሬሳ ግብረ ኃይል። የኢትዮጵያኒዝም ነቀዝ አድናቂነት¡¿¿¿ ቤተ _ የጥላቻ ካንፓኒ ሎቢስት¡¡¡ "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ማህበረ ግብረ ሰይጣን ዝክረኞች ይህ ሁሉ የአማራ ደም፤ ጉስቁልና፦ የህልውና አሳር ለእናንተ ፌስትባል ነው። "የቡርቃ ዝምታ" የዲያቢሎስ ቅኝት አድናቂነት ዲዲቲነት የትውልድ ካንሰር ነው። ለዚህም ነው እኔ አማራ ከማን ጋር ለእርቅ ይደራደር የምለው። ፋክቱም ሎጅኩም አያስኬድም። ከጭንቅላት ውስጥ የተገነባው የጥላቻ ሃውልት መፍረስ ነው እርቀ ሰላም፤ ፍትህ ሊያመጣ የሚችለው። ሰይጣን በቅድስት አገር ኢትዮጵያ መዘከር የሰማይም የምድርም ወንጀል ነው። የስንት ሊቀ ሊቃውንት አገር ኢትዮጵያ? የስንት ዓራት ዓይናማ ፀሐፍት አገር ፈላስፊት ኢትዮጵያ? ኢትዮጵያን ለመሰነጣጠቅ የፋንታዚ ፖሊሲ ነዳፊ አውጪን የመቃብር ሥፍራን መዘከር ማለት እኔ ፀረ ኢትዮጵውያዊነትም ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 2/11/2023

የዕውቀት ባለፀጎች ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያን እንዳይገጥማት እሰጋለሁኝ።

ምስል
  የዕውቀት ባለፀጎች ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያን እንዳይገጥማት እሰጋለሁኝ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።" አገር የሰፈር የእድር ማህበር አይደለም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ደጋፊያን እዬጠቀሟቸው አይደለም። ምንም አይነት የእርምት ዕይታ እንዳይኖር ጠቃሚ ሃሳቦችን በደቦ እያስበረገጉ ነው። ይህ ደግሞ ቁልቁለት ዳጥ እና ምጥ ያዋልዳል። ለትውልድ፤ ለአገር የሚጠቅመው በሁሉም የሙያ መስክ ያሉ ኤክስፐርቶት የሚሰጡት ሙያዊ ክሪቲክ ሊደመጥ ይገባል። በሌላ በኩል መከራውን የተሸከመው ህዝብ አጋጣሚ ሲያገኝ የሚያሰማው ብሶት ፖሊሲ ቀራጭ ሊሆን ሲገባ አደና እና እስር፤ ግለት እና ማሳዳደድ የውድቀት ዋዜማወች ናቸው። እረኛ ምን አለ ታላቅ የዊዝደም ፈር ቀዳጅ ነው። በሌላ በኩል በተለያዬ ሙያ ፕሮፌሽናል የሆኑ ኢትዮጵውያን ወጀብ ፈርተው አንገታቸውን ደፍተው መጠበቅ እናት አገርን መካድ ይመስለኛል። ይህም ብቻ አይደለም የሙያ ሊቀ ሊቃውን ከሙያዊ፤ ከዕውቀታዊ ማዕቀፋቸው ወጥተው ፕሮፖጋንዳውን ከተቀላቀሉም ሰፊ የሆነ የአዋቂወች በረከተ ፀጋ ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያ ሊገጥማት ይችላል። የኢትዮጵያ የስድስት ዓመቱ ችግር የተጋገር ችግር ነው። ስለሆነም ያልሰከኑ ቦጅቧጃ ፍላጎቶች ትውልድንም አገርንም ማዳን አይቻልም። በሌላ በኩል የአገር እና የትውልድ ክብር እና ልዕልናም ከግለሰቦች ሙገሳ፤ ውደሳ ዝቅ ካለ ይህም የሚያስፈራ አደጋ ይመስለኛል። ውዶቼ እንደምን እዬሆናችሁልኝ ይሆን? ቸር ሁኑልኝ። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 4/12/2023 ፈላስፊት ኢትዮጵያ ይቅናሽ። አሜን። Sergute Selassie   · Shared with Public

ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦

ምስል
  ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦ አዲስ አበባ። "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭)               ዶር ዳንኤል ሆይ! በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ። 1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ። 2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም። 3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ የጥቃቱ ሰለባ፤ ዒላማ

ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ። 29.11.2019

  ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ። ትናንት ምሽት በልዕልት ጎንደር ፍሰኃ ነበር አሉ። ህወሃት እንደ ልዕልት ጎንደር እና እትብት የተበቀለው፣ የነቀለው የለም። ለሰሞናት ሰናዩን ማጣጣሙ ባይከፋም የህወሃትን በቀል የሚቋቋምለት መንግሥት አለመኖሩን ሊያውቅ ይገባል። ልቅምቅም ብለው ካቴና ላይ ልጆቹ እንዳሉም ልብ ሊል ይገባዋል። ጎንደር በቅሎ ለማዬት ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቅም ያለው ሰው፣ ድርጅት፣ ተቋም የለም። ይማገዳል ማገዶነቱን አጊጦበት ይኖራል። ሌላው ቀርቶ በአማራ ተጋድሎ ልቡ የነበረው ቅኔው ጎጃም ቂም ተይዞበት ይኽው ይቀጠቀጣል ነጋ ጠባ። ጎንደር በታሪኩ ስለጎንደር ሁለመናውን የገበረለት ብቸኛው ቅኔው የጎጃም አማራ ብቻ ነበር። "ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብሎ ሁለመናውን የገበረ የቁርጥ ቀን ህሊናው የጎጃም ህዝብ ነበር። ያ የፅድቅ መንፈስ ሊከበር ይገባል። ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል። የእኔታ አቻምዬለህ ታምሩ የሰራው ገድል በራሱ ከተቋም በላይ ነው። ስለወልቃይት ጠገዴ ዕውቀታዊ ተቋም ከፍቷል። ለእሱ እንኳን ዕውቅና ለመስጠት አቅም የለም። አዲስ አበባ ቀዳሚት በረራ ፀሐፊ የኔታ ፕሮፌሰር ኃብታሙ ተገኜ ኢትዮጵያን ገለጧት። የመገለጥ አስተርዮ ዘመን ብዬዋለሁኝ። እሳቸው መፀሐፋን የፃፋበት አመክንዮዊ ጉዳይ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተገዳሎ ነው። ያፈራ፣ ያሰበለ እጬጌ ተግባር የጎጃም አማራ ህዝቡም ሊቃናቱም ከውነዋል። መከወናቸው ብቻ ሳይሆን መከራን ተቀብለውበታል። ወጀብን አስተናግደዋል። ስለዚህም በሁሉም ጉዳይ ሰክኖ ማዳመጥ፣ እረግቶ መጓዝ ያስፈልጋል። በተለይ እራስን አሳልፎ ለመስጠት በስለላ መሰማራት ኃጢያትም ወንጀልም ነው። እኔን እምትሰልሉ ሰዎች ታቀቡ ብያለሁ። ማንም ሰው ጠፍጥፎ እንዲሰራኝ አልፈቅድም። በመዳፌ ገብ

አማራ ሆይ! አቅምህን ቆጥበህ ለራስህ መሆን ነው 19.11.2019

  አማራ ሆይ! ቁንጥንጡ፣ ድንገቴው የኦሮሞ ፖለቲካ ነገ በሬው አርዶ ይስማማል። ሲሰነጠቅ ሲገጣጠም ተፈጥሮው ነው። አንተ ማድረግ ያለብህ አቅምህን ቆጥበህ ለራስህ መሆን ነው። አማራ መኖሩን የተቀማ የህልውና ታጋይ ነው። ህልውና ተጋድሎ ደግሞ በፈተና የታጠረ ነው። የለማወአብይን ጉዳይ ለጦማሪ ስዩም ተሾመ ለቀቅ አድርጎ አማራ በየቀኑ ስለሚፈሰው ደም እና፣ ስለወገንህ እንግልት ትጋ። ስለእነሱ ጉዳይ ጃዋራዊው ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ይታመሱበት። አንተ ግን ካቴና ላይ ላሉ ወገኖችህ ታገል። ስለ ነገ፣ ተነገወዲያ ስለሚፈጠሩት የአማራ ልጆች የአገር ባለቤትነት እሰብ ትጋ። ፍሬ ሁን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selssie

29.11.2019 የዱቤ ፓርቲዎች ስሞታ ቋት።

የዱቤ ፓርቲዎች ስሞታ ቋት። ምን እያሉን ነው የዱቤ ፓርቲዎች? እያሉን ያሉት ልንታገል የሚገባው አቶ ጃዋርን ብቻ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ላይ ተድርሷል። ይህ በድርጅታዊ ሥራ የተሰጠ አብይ አጀንዳ ይመስላል። የሚገርመው የተበዳይ ፍዳ አደባባይ እንዲወጣም አይፈለግም። አድርጊዎችም ሥማቸው አይነሳ እዬተባለ ነው። ቄሮ ጀግና ሲባል ካልከፋን ቄሮ ገዳይ ሲባልም ሊከፋን አይገባም። ጀግናም ያሰኜው ገዳይም ያሰኜው ድርጊቱ ነው እና። በፎቶ እዬተነሱ የሚለጥፋትም እነሱው እራሳቸው ናቸው። በደቂቃ መሰብሰብ ማዝመት እንችላለን ሲባል ያልታፈረ ፈታኝ ዕውነት ሲመጣ ከወገብ በላይና በታች የሚል ጨዋታ መጣ። ሲፈለግ በአበባ አቀባበል ይደረጋል፣ ሲፈለግ ደግሞ በሜጫ። ይህን ዕውነት መሸሸት አይቻልም። ግርም የሚለው ካለ መንግሥታዊ አቅም ማህል አዲስ አበባ ላይ አንድ ብሄራዊ መከላከያ፣ የአይር ሃይል፣ የደህንነት፣ የፖሊስ ሙሉ አካል ያላት አገር መዋቅርም፣ ድርጅትም ህጋዊ ዕውቅና ባልተሰጠው አካል ህዝብ መኖሩ እንዲህ ሲጠበስ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል በዬለም ደረጃ ነው ያለው። ወይንስ መንግሥት ነኝ የሚለው በዬቀኑ እዬወጣ የሚፎክረው የቀውስ ቤተኛው ነው ወይ? የቱ ነው ለኃላፊነት ቅርቡ? በአባል የግንባሩ ድርጅት ጫና ለማድረግ ኦነግን፣ ቄሮን በተሟላ የሎጅስቲክስ ድጋፍ እያጠናከረ ያለው ማን ነው? የትኛው አካል ነው። ለምን በዘመነ ህወሃት ይህ መቃናጣት አልታዬም? በደል በገፍ አለ ተጠያቄ አካል ግን የለም። ኢትዮጵያ በኪነ ጥበቡ ነው ያለችው። ይህ ልፍስፍስ አስተዳደር እንደ መንግሥት ታይቶ አትንኩት፣ ድርሽ አትበሉበት የዱቤ ፓርቲዎች አታሞ ነው። ዛሬ ዓለም እራሱ ሁሉን ነገር በተደሞ እዬተከታተለው ነው። ይህ ሁሉ ቀውስ ሲመራ፣ ሲደራጅ ምንጭ፣ ደጋፊ መንግሥታዊ አካል አለ። ይ

29.11.2019የእነ አብረን እናልቅስ ዝልቦ ሬሳዊ ሃሳብ።

  የእነ አብረን እናልቅስ ዝልቦ ሬሳዊ ሃሳብ። ሌላ አማራጭ የለም ከአብይወለማ ውጪ እንደ ዓዋጅ የሆነ ይመስለኛል። እኔ ሥርጉተ ሥላሴስ እላለሁ ከእነሱ ውጪ ከአብይወለማ እምስ ዘመን ኢትዮጵያ መሽቶ የማይነጋላት ከሆነ ለምን ተቃዋሚ፣ ተፎካካሪ፣ ተቀናቃኝ፣ ተደማሪ የሚባለው የአቅም ተጠማኝ የፖለቲካ ድርጅት ሁሉ ስለምን ወደ ሲቢክስ ማህበር አይቀዬርም? ምን አደከመው? ለመሆኑ ይህ ሁሉ የፖለቲካ ድርጅት ሲቋቋም ትንበያ ነበርን? አብይ የሚባል መሪ እስኪመጣ ብቻ ብለው ነበርን ትግል የጀመሩትን? አዬ የአቶ ለማ የዴሞግራፊ የህሊና ነቀላ እና ተከላ ስንቱን ሰው ስልብ አደረገው መሰላችሁ? ህውኃት ቢኖርበትም ከጅጅጋው መፈናቀል ጀምሮ ያሉ ሰብዕዊ ቀውሶች "ከእነሱ ውጪ" የሚል አዲስ ቀኖና ሳይሆን እንደ ዶግማ እንድንቀበልም ነው ዘመቻው የአብይዝም የካድሬዎች የወግ ቋት። ዛሬ እኔ እንደምታዘበው ከሆነ ህወሃት የሚወገዝበት ያህል ኦነግ አይወገዝም። በተደማሪ ተቺዎች ተመስጥሮ የተያዘው ኦነግ ወገን ነው። ለምን? ምኑ አዚም ይሆን እንዲህ ልንቁጥቁጥ፣ ልፍስፍስ ያደረገው መንፈሱን ሁሉ። የተጣበቀ ዕይታ ነው የሚደመጠው። ወላድ በድባብ ትሂድ እንጂ የተሻሉ፣ የበቁ ዓራት ዓይናማዎች ኢትዮጵያ አሏት። መሪ ሊሆኑ የሚችሉ። የሚበልጡም ከአብይወለማም፣ ከታከለወሽመልስም፣ ከንጉሡወደመቀም። በቅድሚያ ታማኝነት የሚጠይቁ የሉዕላዊነት አመክንዮች አሉ። ኢትዮጵያዊነት በውስጥነት እንጂ በምላስ ገበር አይገለፅም። ኢትዮጵያዊነት የውስጥ ፅላት ሲሆን እንዲህ አይወዛወዝም። የኢትዮጵያ ፓርቲ ለማለት የወለሌ ገበታ የሚል ተልባ ሥፍር ለገናናው ማንነት በፍፁም አይመጥነውም። ኢትዮጵያዊነት በሰከነ ጥበብ እንጂ ጎርፍ በከመረው ዕድፍ ዕሳቤ የተፈጠረ ማንነት አይደለም። ትውልድ የቆመ ይመስል &quo

29.11.2019 ምን እግር ጣለው ፋኖ ከጠቅላይ አብይ አህመድ አንደበት ለዛውም ለዬምስራች? ለመሆኑ (ፋኖ )የአማራ የህልውና ተጋድሎ የታገለው ለአምልኮተ አብይ ነበርን?

ምስል
ምን እግር ጣለው ፋኖ ከጠቅላይ አብይ አህመድ አንደበት ለዛውም ለዬምስራች? ለመሆኑ (ፋኖ )የአማራ የህልውና ተጋድሎ የታገለው ለአምልኮተ አብይ ነበርን?     "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል" አሉ ሊሂቃኑ። የምሥራቹን ሰማን። ምን እንዲህ እንደሚያጣድፍ አይገባኝም። የምሥራች የሁሉም ለሁሉም ቢሆን እንደለመደብን አብረን በደለቅን። እኛ እንደሳቸው አልደላን። መከራ ሲመጣ ፊት ለፊት ወጥተን ስንሞግት እሳቸው ድብዛቸው አይገኝም። ሽርሽር ይወጣሉ። ለሃኒ ሙን ብቻ የተፈጠሩ ጠሚር። ለጭብጨባ ደግሞ ማን ቀድሟቸው። መጥኔ ብለናል። "ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዛርማ እንኳን ደስ አላችሁ" ማለታቸውን ሰማን ዶር አብይ አህመድ። ምነው ዛሬ ፋኖ እንዴት ትዝ አላቸው? አንቦ ላይ ሹመታቸውን ሲያስበስሩ "ቄሮ ጀግናው ያሰኙ ዛሬ ደስታውን ልናበስርህ መጥተናል" የተባለው ቄሮ እንጂ ፋኖ አልነበረም። ይልቁንም ሲያሳድዱት ፋኖ ማለት እኔ ነኝ ያሉትን ብጄ አሳምነው ፅጌ፣ በአደባባይ እሬሳውን ሲያንገላቱ የትዳር አጋር አስረው ፅንስ ሲበቀሉ ነው የታዬው። የልዩ ኃይሉም ሲረሸን እዬታደነ ነው ያዬነው። የአማራ የህልውና ተጋድሎ ለአጤ አብይ የብልፅግና ፓርቲ አልታገለም፣ ለሳቸው የሰብዕና ግንባታም አልነበረም ያን ያህል መራራ መስዋዕትነት የከፈለው፣ እሳቸው ከነመፈጠራቸው ከቶውንም ተጋድሎው አያውቅም ነበር ተጋድሎው አህዱ ሲል። ለአማራ የህልውና ተጋድሎ አብይ ትናንትም አጀንዳው አይደለም ወደፊትም አይሆንም። የብልፅግና ፓርቲው ምስረታም፣ ክስመት ይሁን ክስለት ለተጋድሎው አጀንዳው አይደለም። የተጋድሎው የህልውና መሰረት መኖርን ለማኖር አማራ የአገር ባለቤትነቱን በዘለቄታ የሚረጋገጥበትን ሥርዓት በብሄራዊ ደረጃ እንዲፈጠር መታገል ነው። አማራ ባበጃት አገር ባይተዋር

እያንዳንዱ ልጅ ……

ምስል
እያንዳንዱ ልጅ …… #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል። #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። አገላለፁ የእኔ ነው። እኔም በዚህ ውስጥ መሆኔን አምነዋለሁ። እቀበለዋለሁም። ስለዚህም በመክሊቴ፣ በተሰጠኝ ጥሪ እና መልዕክት ውስጥ መኖሬን እወደዋለሁኝ። መማገድ የሚያሳሳኝ፣ የምወደው ጭር ሲልም የሚናፍቀኝ አንጡራ ጥሪቴ እና መስመሬ ነው። "አድርገህልኛል እና አመሰግናለሁኝ።" እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? አይዟችሁ። ሁሉም ያልፋል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/11/2023 በተሰጠኝ ልክ መኖሬ ሐሤቴ።  

ጥሞና። የዛሬ የፓርላማ ውሎ በጨረፍታ ዕድምታ። 30.11.1020

ምስል
ጥሞና። የዛሬ የፓርላማ ውሎ በጨረፍታ ዕድምታ።        መቅድም። የተቆለፈባቸው ጠቅላይ ሚኒስተር ዘገባ ከቅድመ እስከ ድህረ ዕድምታ በጨረፍታ። አስፈላጊ ከሆነ እመለስበት ይሆናል። በር። ጥሞና የሚጠይቁ ሁለገብ ጉዳዮች አሉ። ዳንኤሏ ኢትዮጵያ በመጠነ ሰፊ ቀውስ ውስጥ ነው የባጀችው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጥሞና ያስፈልገዋል። ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ዝርዝር መግለጫ አሰምተዋል። ለሳቸውም ለተናጋሪው ለአድማጩም መጦመን ያስፈልጋል። መቼ ይሆን የሳቸው የጥሞና ጊዜ? የሳቸው የሥልጣን ዘመን ችግር ሁሉ ምንጩ፣ መነሻ መድረሻው ህወሃት ብቻ ነው ብለዋል። ዕውነት ይሆን? እሳቸው እና ካቢኒያቸው ደግሞ በመርዛማው ህውሃትወኦነግ ህገ - መንግሥት ተኮትኩተው ያደጉ አሁንም ያን እናስከብራለን ብቻ ሳይሆን እንደ ቃለ አቀባያቸው እንደ አንባሳደር ሬድዋን ገለፃ እናሰርፃለን ተብለናል። እንዴት እናገናኜው? ያን ሲኦል ህገ - መንግሥት ለማስቀጠል በኮፒ ራይት እፍግብ ይህ ሁሉ ድቀት ተፈጥሯል። በአጭርም ይቋጫል ብዬ አላስብም። መሬቱ እራሱ ተዋጊ ነው። ዞጋዊ አደረጃጀቱም ገዢ መሬት ነው። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ኦህዴድንም ኦነግንም ንክት አላደረጉም። እንዲያውም ለስሜኑ ጦር ደጀን ነበር ኦሮምያ እና ጉምዝ የፀጥታ ኃይል ብለውናል። ቤቴ እስኪነቃነቅ ከትከት ብዬ ስቄያለሁ፣ የታሪክ ሽሚያ። ህም። በጭልፋ የተሰማኝን። ዛሬ እንደ ቀደመው ሰው ሳያውቃቸው በ2016/17 ሲያውቃቸው 2018 አዳምጣቸው እንደ ነበረው በጥሞና አዳምጫቸዋለሁኝ። ከተጀመረ ስለነበር ያገኜሁት፣ በተጨማሪም ረጅም ስለሆነም ደግሜ በጥሞና ማዳመጥ ይኖረብኛል። ከዚህ ውስጥ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ላይ ያነሱት ትክክል ነው ብዬ መቀበል እችላለሁ። የሠራዊቱ የእግር ጉዞ እማውቀው ስለሆነ አምነዋለሁኝ። ማንም አ

አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። 25.11.2020

  አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። አባ ቅንዬ የአማራ ህዝብ የዘመኑን ባህሬ በማንበብ የህሊናዊነት አድማሱን ሊያሰፋ ይገባል። ከሩትን ተግባር ወጥቶ ባለ እርስትነቱን በሉላዊ ህግጋት ማስከበር ግድ ይለዋል። ሰርክ የቹቻ እና የሰኔል መሰናዶ ሊሰለቸው ይገባል። ዘወትር ሊቃናቱ ተለይተው ለካቴና፣ ለባሩድ፣ ለካራ፣ ለሳንጃ፣ ለሜጫ፣ ለእሳት ሲዳረጉ ለምን ብሎ እራሱን ይፈትሽ አማራ! በቃኝን ለምርምር ያውል። በስተቀር የኩርድሽ ዕጣ ክፍሉ ይሆናል። ማንም እንዳይኖረው ነው ሊቃናቱ በረድፍ የተረሸኑት፣ ልቅምቅም ብለው አሁንም ለካቴና የተሸለሙት የትውልዱ ተስፋ ቀና እንዳይል፣ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ነው የታለመው። የሚከወነው። አለኝታ፣ ጋሻ እንዳይኖረው ማድረግ ሙሉ ፕሮጀክት ነው የአገዛዙ። ስለዚህም የአማራ ህዝብ በማስተዋል መራመድ፣ አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር፣ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር መምከር ይኖርበታል። ቂም፣ በቀል የፀነሰ ዕለት ከሰዋዊ ውርጅብኝ በላይ ሰማያዊ እሳት ይወርድበታል። ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ፈርኃ እግዚአብሔር፣ ፈርኃ አላህ መሆኑን ሆኖ በመገኘት፣ ማክበር፣ ማስከበር ይኖርበታል። ጥላቻ አመድ፣ ክሰል፣ ትቢያ ነው። እሱ አልተፈጠረበትም። እና ለሰከንድ እንዳያስጠጋው። በስተቀር ምርቃቱ ይነሳል። ሁላችንንም ያጠፋናል። መክሊታችን ይሰረዛል። ሰብዕነታችን ፍግ ይሆናል። አደራ። ከዚህ ባሻገር ባለው ተጋድሎ ቆርጦ ትግል ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ቀን እዬቆጠረ ፀረ አማራ፣ ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ ሰው አዬሩ ይጠራል። ሥራው የመዳህኒዓለም ነውና። ከሰብዕነት ተርታ ለጠፋት ፈጣሪ የንሥኃ ጊዜ ይስጣቸው። አሜን። እኛ የተሰጠንን መልካምነት ይዘን የሚጠሉን ክፋነትን ሰንቀው ቢጓዙ ችሎቱ የእዮር ነው። ካለ ካህሊ - ሥልጣናችን ዘው አንበል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። 25.11.2020 የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?

የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?    ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተው የሚማሩት ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት የዓለም መድህን የሆነ የምርምር ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊነት አናባቢም ተነባቢም ቅዱስ በረከት ነው። ኢትዮጵያዊነት ተዘርዝረው በማይዘለቁ ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ምጥን ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት በጉልት ገብያ አውጫጭኝ አልተመሰረተም። ኢትዮጵያዊነት በውስጥህ ከኖረ ክህደት፣ ዝቅጠት፣ ስላቅ፣ ዝንፈት፣ መስቃ፣ ትዕቢት፣ ፀረ ሰውነት አያሸንፋህም። ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሯዊነትም፤ ሰዋዊነትም ነው። ኢትዮጵያዊው ሰው ፀጋው ዝልቅ ነው። ተማረ አልተማረ። ሰማዩን አይቶ የአዬሩን ባህሬ ይነግርኃል። ዛፍ ቆርጦ ዕድሜውን ይነግርኃል፣ የሰውነት ዛላህን አይቶ ውስጥህን ያነበዋል። ያብራራዋል እንደ ዘመንኛው ራዲወሎጂ በለው። ኢትዮጵያዊነት መርኽም ነው። ኢትዮጵያዊነት መንገድም ነው። ኢትዮጵያዊነት በህግ አምላክነትም ነው። ህግ ነው። ኢትዮጵያዊነትን በውስጡ ለፈቀደ ብርኃን ነው። ከፍ ቢል ዝቅ ቢል መጥኖ በቁጥብነት መኖርን ያኗኑራል። ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ኃይሌ ላሪቦ ኢትዮጵያዊነትን "ረቂቅ ሚስጢር" ይሉታል። አባ ትሩጉም አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት አፈጣጠር ኦርጋኒክ" ነው ዬሚል ጥልቅ ፍልስፍና አለው። ውስጡን ላጠናው ዕውነት ነው። ይህን የሚሸከም መሪ ማግኜት ግን አልተቻለም። ለዚህ ነው የአፍሪካ አገር መሪዎች እዬተሸማቀቁ ያሉት። አፍረውብናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ኢትዮጵያዊነት ቅኔ ነው።  

የአማራ እርቀ ሰላም እንዴት ከእነማንስ ጋር?

ምስል

ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቅ ይሆን?

ምስል

''ፀጋዬ ሼክስፒርን በአማርኛ ያናገረ ሰው ነው'' | እንዳለጌታ ከበደ ከአበበ ባልቻ ጋር | ''እሳት ወይ አበባ'...

ምስል

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተሳሳተ ትርክት፥ "አማራ የነገድ ማንነት የለውም" ሲፈተሽ

ምስል

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መታገታቸው ተደመጠ፨ 24.11.2023

ምስል

የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? #ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

ምስል
  የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? እንዴት አደርን? የቅኔ አድባራት እንዴት ውለው አደሩ ይሆን? እነ ማህበረ ቅንነትስ እንዴት አላችሁልኝ??? #ሚስጢረኛችን #ኢትዮጵያ #ብቻ #ናት ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       ይህ ጥያቄ ከ32 ዓመት በላይ ተቀንቅኗል። አማራ እንደ አማራ የጠላውም፤፦የሚጠላውም፤፦የሚያሳድደውም፤፦የሚያወግዘውም፤ ያፈናቀለውም፤፦ያሳደደውም፤ መኖሩን የቀማውም፤ ጋብቻ የከለከለውም፤ በጉርብትና ፊት የነሳውም፤ በግብይት ያገለለውም አይደለም ማህበረሰብ፤፥ተቋም ቀርቶ ግለሰብም የለም። ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው አምላክ አላህ ያውቀዋል። የእኛን ቅንነት እና ገራገርነት። ስለዚህም አማራ ሊታረቅም ብሎ አቤቱታ የሚቀርብለት ግለሰብ፤፥ተቋም ማህበረሰብ የለውም። ይልቁንም ከሙሉ የህሊና ካሳ ጋር ሊካስ የሚገባው የአማራ ህዝብ ነው። በዳዮቹ መበደላቸውን አቁመው ይቅርታ ጠይቀው ሊክሱት ይገባል። የመንፈስ ካሳ። ውሃ በቀጠነ ማቱ የሚወርደው በአማራ ላይ ነው። ነፃ አውጪወች ሲደራጁ የማኒፌስቷቸው ጭብጥ ፀረ አማራነት ነው። ስለዚህ ይህን ጭብጥ ቢተውት ተቋማቸው የሁሉም ይፈርሳል። እርቀ ሰላሙ ይህ እና ይህ ብቻ ይሆናል።   ህወሃት ሙሉ 47 ዓመት ሚዲያው ሊቃውንቱ ዛሬም ፀረ አማራ ዲስኩር ነው። ጦርነት የከፈተው የ፬ኪሎው ኦነግ ሆኖ ዛሬም ናዳ የሚለቀቀው በአማራ ላይ ነው። ኦነግ ፬ ኪሎ የንጉሦችን ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት በአማራ ትጋት እና ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ዛሬም አማራ ላይ ዛሩ እንደተደረረ ነው። የከተማ ተቋማቱ፤ የጫንካ ክንፋ ውግዘቱም ምንጠራውም አማራ እና ጠረነ አማራ ብቻ ነው። የኦነግ ሊቃውንት የላንቃቸው ጠበለ ጣዲቅ ይህው ፀረ አማራነት ነው። ተማሩ አልተማሩ አንድ አይነት ማት ይፈሳል። እዬረሸኑም፤ እ