ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦

 

ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ።
ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦
አዲስ አበባ።
"ጎለመስኩ አረጀሁም፤
ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል
ሲለምን አላዬሁም።"
(መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭)
 
 May be an image of 1 person and text that says 'የኢትዮጵያ የኢ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን AHL ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COMMISSION Photo Source internet'May be an image of 1 person
 
 May be an image of 4 people
May be an image of 8 people 
 
 
May be an image of temple and text
ዶር ዳንኤል ሆይ!
በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ።
1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ።
2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም።May be an image of briar and mushroom
3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ የጥቃቱ ሰለባ፤ ዒላማም ሆነዋል። ለምን? ይህን በሚመለከትም የትውልድ ተከታታይነትን በተፃሮ ያለ ክፋ ድርጊት ነውና ኮሚሽኑ በተለዬ አትኩሮት ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ።
4) የመንግሥት ሠራዊት በዓውደ ውጊያ ከቆዬ በኋላ ሲመለስ ያገኛቸውን ንፁኃን ላይ የጭካኔ ተግባርም እንደሚፈፀም አዳምጣለሁኝ። ለማጣራት ከእኛ ይልቅ እናንተ በቅርብ ስላላችሁ ጉዳዩን አጣርቶ ይህ የበቀል እርምጃ የሚቆምበት ጥረት ኮሚሽኑ ቢያደርግ መልካም ይሆናል።
ቁጭ ብዬ ሳስበው ኢትዮጵያ በውጭ ኃይል እዬተገዛች እንደሆን ይሰማኛል። በዕውቀት አንባወች ላይ ይህን መሰል ጥፋት በአገር ልጅ አይታሰብም እና። ማዳበሪያ ተከልክሎ የዘራውን ሰብል ሲሰበስብም ያ መከረኛ ህዝብ ጥቃት ይደርስበታል። ችግሩ ግዙፍ ስለሆነ በልኩ መትሮ መሞገት የሚገባ ይመስለኛል። ዝልቅ የሆነ የጥፋት ተልዕኮ ያለው ኃይል ነው ምራኝ ብሎ የአማራ ህዝብ የመረጠው። ለዚህም ነው "ቁጭ ብሎ የሰቀለውን ቆሞ ማውረድ የተሳነው።"
ኢንተርኔት ዘግቶ በህዝቡ ግፍ የሚፈጽም ሥርዓት ውስጥ አብሮ መሥራት ቢከብድም፦ እኛ ጭንቀታችን የማጋራት ግዴታ ይኖርብናል። ድርጅቱም በመጠነ ሰፊ፤ ሁለአቀፍ የተከፈተውን ምህረት አልባ ጥቃት ለመቋቋም፤ ለማጋለጥ መትጋት ግድ ይሆናል። እኛም አላችሁ እነሱም ተቋማት ገንብተናል ስለሚሉ። ከከሸፈ ራዕዩ ደግሞ መቁረጥ፤ መወሰን ይገባል። አብሮ ከመውደቅ። ምክንያቱም ተቋሙ አለ ተብሎ በዓለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ ስለሚታወቅ ሽፋን ብቻ ሆኖ እንዳይቀር። በውነቱ ሙሉ ስድስት ዓመት በአማራ ህዝብ መኖር ላይ የተፈፀመው ግፍ እና በደል መሬት አንደበት ቢኖራት እላለሁኝ። የገለማ እና የከረፋ በቀል ነው የሚስተዋለውና።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/11/2023
ሰው ከጠፋ አገር አለ ማለት ይቻል ይሆን???

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።