ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ። 29.11.2019

 

ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ።
ትናንት ምሽት በልዕልት ጎንደር ፍሰኃ ነበር አሉ። ህወሃት እንደ ልዕልት ጎንደር እና እትብት የተበቀለው፣ የነቀለው የለም። ለሰሞናት ሰናዩን ማጣጣሙ ባይከፋም የህወሃትን በቀል የሚቋቋምለት መንግሥት አለመኖሩን ሊያውቅ ይገባል።
ልቅምቅም ብለው ካቴና ላይ ልጆቹ እንዳሉም ልብ ሊል ይገባዋል። ጎንደር በቅሎ ለማዬት ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቅም ያለው ሰው፣ ድርጅት፣ ተቋም የለም። ይማገዳል ማገዶነቱን አጊጦበት ይኖራል።
ሌላው ቀርቶ በአማራ ተጋድሎ ልቡ የነበረው ቅኔው ጎጃም ቂም ተይዞበት ይኽው ይቀጠቀጣል ነጋ ጠባ። ጎንደር በታሪኩ ስለጎንደር ሁለመናውን የገበረለት ብቸኛው ቅኔው የጎጃም አማራ ብቻ ነበር።
"ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብሎ ሁለመናውን የገበረ የቁርጥ ቀን ህሊናው የጎጃም ህዝብ ነበር። ያ የፅድቅ መንፈስ ሊከበር ይገባል። ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል።
የእኔታ አቻምዬለህ ታምሩ የሰራው ገድል በራሱ ከተቋም በላይ ነው። ስለወልቃይት ጠገዴ ዕውቀታዊ ተቋም ከፍቷል። ለእሱ እንኳን ዕውቅና ለመስጠት አቅም የለም።
አዲስ አበባ ቀዳሚት በረራ ፀሐፊ የኔታ ፕሮፌሰር ኃብታሙ ተገኜ ኢትዮጵያን ገለጧት። የመገለጥ አስተርዮ ዘመን ብዬዋለሁኝ። እሳቸው መፀሐፋን የፃፋበት አመክንዮዊ ጉዳይ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተገዳሎ ነው።
ያፈራ፣ ያሰበለ እጬጌ ተግባር የጎጃም አማራ ህዝቡም ሊቃናቱም ከውነዋል። መከወናቸው ብቻ ሳይሆን መከራን ተቀብለውበታል። ወጀብን አስተናግደዋል።
ስለዚህም በሁሉም ጉዳይ ሰክኖ ማዳመጥ፣ እረግቶ መጓዝ ያስፈልጋል። በተለይ እራስን አሳልፎ ለመስጠት በስለላ መሰማራት ኃጢያትም ወንጀልም ነው። እኔን እምትሰልሉ ሰዎች ታቀቡ ብያለሁ።
ማንም ሰው ጠፍጥፎ እንዲሰራኝ አልፈቅድም። በመዳፌ ገብታለች ተብሎም ፋከራ ሲያምራችሁ ይቅር። አትሰቡት። ለተሰራሁበት ለተፈጠርኩበት መክሊት ተጋድሎው ይቀጥላል።
ቂም፣ ጥላቻ፣ በቀ፣ ምቀኝነት ቅናት ድርሽ አይልም ከእኔ ቤት ስለማንኛውም ወገን ሥርጉተ መስክራለች ቅናት፣ ምቀኝነት ቢኖርባት አታደርገውም። ሥርጉተ ሥላሴ ብላችሁ ጎልጉሉ ሥለ ሰው ምን ያህል ስማገድ እንደኖርኩ ይነግራችኋል። ንፁህ ነኝ።
ስለህወሃት ጫካ እያለ ታግዬዋለሁ፣ ከተማ ሲገባም ጫካ ገብቼ ታግዬዋለሁ፣ እስር ቤቱንም አውቀዋለሁ፣ አንቱ ያላቸውን ምርኩዞቹን ነቅንቄያለሁ፣ ተሳክቶልኝም ነቅያለሁ፣ በሰነፋ አብይዝም እንዝላህልነት ለተፈጠረው ቀውስ እና ውጤት ግን ታዛቢ እንጂ አፋሽ አጎንባሽ ልሆን አልፈቅድም። ተጨማሪ ማገዶነት ለኦነግ ሎሌነት አላዋጣም። የለመደበት ይዳክር።
ወደ ቀደመው ስመለስ መንፈሶቻችን፣ ህሊናዎቻችን ካቴና ላይ ነው ያሉት። የሰንደቃችን ትጉኃን። ስለእነሱ መትጋት ይገባል። ስለእነሱ መበርታት ይገባል። ስለእነሱ መፀለይ ይገባል።
የዛሬዋን ብልጭታ ላልተፈቀደላቸው የእኛዎች ቢያንስ አይዟችሁን ልንልክላቸው ይገባል። አያስከፍል። ውድ አይደል። በእጅ ያለ ፈውስ።
ከሁሉም ቅን እንሁን። ቅን ሰው እኔ በግሌ ማግኜት አልቻልኩም። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ካህዲን ተጠዬፋ ኃይማኖቱ ከኖረ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።