ልጥፎች

18.01.2020 ኢትዮጵያዊነትን አማራነት ያነበዋል፣ ይተረጉመዋል፣ ያመሳጥረዋል። ውስጥህን ስትፈትሸው እሚነግርህ ሚስጢር አለ። ሚስጢረኛ ብታደርገው አማራነት ጥበብ ነው። ሁንበት! ኑርበት! ታተርፋለህ ልቅና።

ምስል
 አማራነት የማይሸነፍ ማንነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie      ተፈሪነታችን ልቅና በልዕልና ነው። ስለሆነም ተፈሪነታችን ንጥረ ነገራችን ስለመሆኑ አሳምረን እናውቀዋለን። አማራነት ይለምልም! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራ በመሆኔ ሐሤት አደርጋለሁ። አማራነት ይስፋ አማራነት ይንሠራፋ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  በአማራነቴ በውስጤ ያለውን ጥልቅ መንፈሳዊ ኃብት እማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። ስለዚህም አማራነቴን አመሰግነዋለሁ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራነት የህሊና መክሊት ነው። ስለዚህም አቅመ ቢስ ጊዜ ሰጥ መሪዎች አጥብቀው ይፈሩታል። አይፈረድባቸውም። አማራነት ሱቅ ተሂዶ የሚገዛ አይደለም እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  የአማራነትን የጥሞና ልክ ገላጩ፣ ሚስጢረኛው፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው አረንጓዴ ቢጫ ቀዪ ብቻ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  ኢትዮጵያዊነትን አማራነት ያነበዋል፣ ይተረጉመዋል፣ ያመሳጥረዋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራነት ያብባል ገና! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራ ስትሆን ድምቅ ስትል ሁለመናው ያምርብኃል። እና ማህበረ ፀረ አማራ የፈጣሪን ፀጋ ለማምከን ይተጋል። ግን አይሳካለትም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie    ዝም ብለህ እሰበው አማራነትህን። በሰብአዊነት፣ በተፈጥሯዊነት ውስጥ ስለመስከንህ ያጫውትኃል። መሆኑን አንተው አሳምረው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie    ውስጥህን ስትፈትሸው እሚነግርህ ሚስጢር አለ። ሚስጢረኛ ብታደርገው አማራነት ጥበብ ነው። ሁንበት! ኑርበት! ታተርፋለህ ልቅና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አስተውለው። ጥሙና አጉርሰው። አገር ማበጀት

አገር ጠልቶ አገር መምራት አለ ወይ???

 አገር ጠልቶ አገር መምራት አለ ወይ??? ሥርጉትሻ 18.01.2024

#ችኮላ #አይገጠግጠኝም።

ምስል
  #ችኮላ #አይገጠግጠኝም ።   በጓዳ እዬመጣችሁ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የሞተ ዘመድ የለሽም ወይ? እንደ ሌለ ቁጠሪው የምትሉኝ ቅኖች ችኮላ አያስፈልግም። ይህንን ጭብጥ በተለያዬ ጊዜ ፅፌዋለሁኝ። ወቀሳ፣ ነቀሳ፣ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ማስወገድ ከተፈለገ ፊት ለፊት ብዙ ቀኖች አሉ። ይደረስበታል። ወት ብርቱካን ሚዲቅስ ስንት ግብር የከፈልኩላት እኮ ይኽው በራሷ ጊዜ ከስንት ዓመት በኋላ በእሷ ምክንያት በሉላዊ ሁኔታ ባን ካሰደረጉኝ ጋር መከተሟ ሳይሆን ድርጊቷ ቋሰኛ መሆኑ ከውስጤ ወጣች። በቃ። ይደረስበታል። እኔ የተስፋ አቀንቃኝ ነኝ። የመጀመሪያው የአዋቂዎች የግጥም መድብል መፀሐፌ "ተስፋ" ነው። በ2008 በተመሠረተው የፀጋዬ ድህረ ገፅ ላይ #ተስፋ የሚል አንድ መምሪያ ነበረኝ፣ #የሎሬት ተስፋ የሚል የልጆች ዝግጅት በድምፅም በፁሁፍም ነበረኝ። ለ13 ዓመት የዘለቀው የፀጋዬ ድምፅ ራዲዮ በወር ሁለት ጊዜ በሚቀርበው መሰናዶ መግቢያው #በተስፋ #ተስፋ የተቀመረ ነው። ከፊደል "ተ"ን ከሥም "ተስፋን" እወዳለሁኝ። ስለዚህ ተስፋ ባለበት ቦታ ተስፋዬን አድርቄ አልማስንም። እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽንም፣ ኮሚሽነሩንም ዶር ዳንኤል በቀለን ተስፋዬ አድርጌ አያቸዋለሁኝ። ክፍት ሲለኝም ለእሳቸው በግል እፅፋለሁ፣ አቤት እላለሁ። ይህን ፈጣሪ ያስቀጥልልኝ ዘንድ እማፀናለሁኝ። ኮሚሽኑ የሚወስናቸው፣ ዳታ የሚያበዛባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ ደግሞ በአክብሮት ወቀሳዬን አቀርባለሁኝ። … እንጂ መብራቱን ድርግምግም አድርጌ በጨለማ አልደናበርም። ብርኃን አለ፣ በዛ ተጉዤ ተጨማሪ ሙሉ ይሆን ዘንድ ሃሳቤን አጋራለሁኝ። አንድ እሱ ብቻ ተቋም መጠለያ የተስፋ ጥግ ኑሮ እሱንም ለመንቀል አዕምሮ ውስጥ መ

#ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።

ምስል
  #ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።     ስሜን ፖለቲካ ኢትዮጵያን የፀነሳት፣ ያረገዛት፣ የወለዳት፣ ያሳደጋት፣ ያጎለመሳት፣ ያደረጃት የሚስጢር ባለሟል፣ የዕደምታ እጬጌ፣ የተደሞ ንጥረ ነገር ነው። ህወሃትን ጨምሮ የፈለፈላቸው የመንፈስ ዲቃላዎቹ፣ የጡት ልጆቹ ሁሉ ደግሞ ሲነሱ ሲወድቁ ኖረው አሁን ተሳካላቸው። በመሪያቸው በሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ እና በተደማሪ ሚዚዎች አማካኝነት ከሰኔ 15/2011 ጀምሮ ከዛም ቀደም ብሎ ዋዜማው በማዕከላዊ ጎንደር በሺህ ዘመናት የመፈናቀል ታሪክ ከ80 ሺህ ህዝብ፣ ከስሜን ፓርክ ቃጠሎ ጋር ዛሬ እስካለንበት ጥር ጣና ዘገሊላ ሰሞናት ድረስ በግፍ፣ በበቀል ታረሰ። ለእኔ የሥነ ልቦና ጦርነትም ነው ብዬ አስባለሁኝ። አሁን ራህቡም፣ ጥማቱም፣ መፈናቀሉም፣ መታረዱም፣ ግፍ መቀበሉም አገራዊ ሠራዊት አልበቃ ብሎ የሱማሌ፣ የኤርትራ፣ የሱዳን ጦር በህብረት ኢትዮጵያ የተሠራችበትን የወርቅ ማህለቅ ሚስጢር ጥሶ ገብቶ አደቀቀው፣ አመሸከው፣ ተቀበለው። መቃዲሾ ካራማራ ላይ ያጣችውን ድል፣ ኤርትራ ባድመ ላይ ያላገኜችውን ድል፣ ሱዳን መተማ ላይ ያልተሳካላት ህልም በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የሞጋሳ ብልፅግና አመራር ተሳካለትን። ተዋረድን። ተሸማቀቀቅን። ሁሉም የችግር አይነት ስሜን ላይ ተፈቀደለት። ጦርነቱን በጥሞና ማዬት ይገባል ብለን የሞገትን ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ፀጋዬ፣ ጋዜጠኛ ኃብታሙ አያሌው፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት ማዕዛ ማህመድ እና እኔ እራሴ ሥርጉተ ሥላሴ ብቻ ነበርን። የዓለም ተራዕዶ ድርጅቶች ሳይቀሩ እኛ በሞገትንበት ጊዜ አልነበሩም። አሁንም ቢሆን ተባደግ ነው ዕይታቸው። ፍሬ ነገሩን አላገኙትም። ስለተጋሩ ቢጮሁም ስለ አማራ ግን አይጮሁም። ይህን የሚያስደርጉት ደግሞ አቅም

#ትቢያነት አስተሳሰባዊ እርከኑ።

ምስል
  #ትቢያነት አስተሳሰባዊ እርከኑ።   ለዚህ መኖር የሴራ ስልጠና፣ ለዚህ መኖር የቁማር ተቋም፣ ለዚህ መኖር የኢንትሪንግ ብልፅግና፣ ለዚህ መኖር የቂም ድሪቶ፣ ለዚህ መኖር የበቀል እንድርቺ እንድርቺ፣ ለዚህ መኖር የግለኝነት ቅልሞሽ፣ ለዚህ መኖር የበቀል ሥልጣኔ። ትቢያነት አስተሳሰብ። #ህዝባችን ይሄን ይመስላል። ለዕለት ጉርስ ያልበቃ። በማረፊያው ጊዜ ማስኖ ለመኖር ያልተፈቀደለት። የደላው ደግሞ እስረኛን ለመጠዬቅ የክት እና የዘወትር ይበጅለት፣ እኛ ዜግነቱን የሰረዝነው አሳርኛ ለምን ከወገኖቹ ጋር ገጥ ለገጥ ተገናኜ ብሎ ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ኩፍትርትር ይላል። እርግማን። አብሮነት ጠላቱ #የገዳኦዳ #ምርጫ #ቦርድ ፣ #የህወኃት ማንፌስቶ ተህገ-መንግሥት ብቻ ሳይሆን ነፃነት የናፈቀውም ሆኖ ስታዩት የውስጥ አቅሉ፣ የአስተሳሰብ ዲካው #ጎግማ ፣ #ቆባ ፣ #እጭ ላይ እዬዳከረ እንደሆን ታያላችሁ። መሥራት አለብን። ውስጣችን ወና ነውና። አልበቀለበትም ልቅና። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። 19/01/2021 ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

#ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።

ምስል
  #ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።     ኢትዮጵያዊው ሰው እኔን ጨምሮ በዚህ ልክ ስለመሆኑ ይፈትሽው። ኢትዮጵያዊው ውሻ ያለው የፅናት አቅም፣ የመታመን ልቅና የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት እስተካቢኔው፣ እስተሚያላግጥበት #የሞጋሳ #ብልጥግና ፣ የገዳ ምርጫ ቦርድስ ይኖረው ይሆን? እኛ ስልጣኑም አቅሙም ተደማጭነቱም የለንም እና። የቤተ - መንግሥቱ ሽማምንት፣ #የኦዳወገዳ ቤተ - መንግሥት ቅልጥመኛ፣ #ፍሪንበኛ ፣ አንጣፊ፣ ዕልፍኝ አስከልካይ ሊጋባ ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት ዝልቅ ሚስጢር ዬመታመኑ ልኩ፣ ወቄቱ ከዚህ ቅዱስ ታማኝነት ጋር እቆማለሁ፣ እወዳደር ይለን ይሆን? #ዬልግጫ #ልጣጭ ። ሁላችንስ ከዚህ ቀደም ስለ ዓድዋ የዘመርነው፣ የተቃኜነው፣ ፅላታችን ያደረግነው፣ ስለፋሲል፣ ስለ ቴዲ፣ ስለ በላይ፣ ስለ አብርኃም፣ ስለ ካራማራ፣ ስለባድመ፣ ስለ መቅደላ፣ ስለ አሉላ፣ ስለ ዮሖንስ፣ ስለ ዘርዓይ፣ ስለ አብዲሳ፣ ስለ ኃይለማርያም ማሞ የውስጥ ውህድነት በምስክርነት ዛሬ አለን? #ውሸት ማን ነው? #ዕብለትስ የማን ነው? #ሃቅስ ተዬት ነው? #ክህደትስ ከወዴት ነው? እጬጌው ዘመን ዝክንትሉን አውጥቶታል፣ ሸግሽጎታል፣ ሸክሽኮታል፣ ፈትጎታል። ተመስገን። #አኔዊነት ፣ #አገራዊነት ፣ #ብሄራዊነት ፣ ፓናዊነት ግን የት ናቸው? ፈተና አላፊና ወዳቂ፣ መቀነስ እና መታከል፣ መጠቅለልና መወረር እንደምን እና እንደምን #በገዳኦዳ ? ከዚህ ሁሉ ኳኳቴ፣ ከዚህ ሁሉ ትርምስ የፀዳ፣ የነጣ፣ የበቃ ታማኝነት በዚህ እንሰሳ ውስጥ ፈልቆ ተገኜ። መማር ከተቻለ የሐዋርያነት ኩነት ተፈፀመ። ተመስገን። #ውስጥ እስቲ ይመርመር? #አነስን ወይንስ እኩያ ሆን? #የት ላይ ይሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ከእነ ካቢኔዎት? ይመዝኑት መዝኑት። ይ- መ - ዘ - ኑ

መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።

ምስል
  #መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።   ለዚህ ኑሮ የሴራ ፖለቲካ፣ የሸፍጥ ፖለቲካ፣ የደባ ፖለቲካ፣ የአድመኝነት ፖለቲካ ፋፍሪካ ተከፍቶለታል። እኔን የምትከተሉ ውዶቼ ዛሬ እራስን መርምሮ እራስን ከአድማ - ከሴራ - ከበቀል - ከምቀኝነት ፖለቲካ ጋር እንፋታ ዘንድ እለምናችሁ አለሁኝ። #አንዱን ሰው ወደህ ሌላውን ጠልተህ፣ #አንዱን ሞት አዝነህለት ሌላውን ደልቀህበት፣ #አንዱን ራህብ የእኔ ብለህ ሌላውን እልልታ ልከህበት፣ #አንዱን መፈናቀል ውስጥህ አድርገህ ሌላውን ፊት ነስተህ አለሁ አትበል የለህም። #እነግርኃለሁ የለህም። በሆነው ነገር፣ በሚሆነው ከንቱ ነገር ሁሉ አብረን እንፈር። ውርዴቱ የጋራ ዝቅጠቱም የወል ነው። ከፈፃሚዎቹ የተሻለ ለመሆን ከራስ ይጀመር። #በኃጢያት ተልተናል። ሰው ሞተ፣ ቤተ መቅደስ ተደፈረ፣ መስኪድ ተቃለለ፣ ቅርስ ወደመ፣ ታሪክ ጠለሼ፣ ሰውነት ተሰደደ፣ መኖር ተዘረፈ ሁሉም ከጎጆ ካልገባ ፋሲካ ነው። ዋዮ! #ወዮልን ! እንደ ኩርድሾቹ ስንሆን ስንቀረቀር ይገባናል። አፈር አልባ መሆን፣ አገር የለኝም ማለት፣ መለያ የለኝም ማለት ቀና ማለት ሳይሆን #አፍ ባለው መቃብር መከዘን ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። 19/01/2022 ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ፀሎት የፅናት ወተት ነው።

ምስል
 ፀሎት የፅናት ወተት ነው።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/01/2021

በ2019 ነው እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የደወል ንቅናቄ እንድትጀምር በትህትና ያሳሰብኩት። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም። " ቢሰሙን ይበጅ ነበር።

ምስል
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን። ይድረስ ለብፁዐን ቅዱሳን አባቶቼ። ባሉበት።   በአለፈው ሳምንት አንድ ቁልፍ ነገር አንስቼ ነበር። የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ አላወቀችውም እንጂ የቁም እስረኛ ናት። በጠቅላላ እንቅስቃሴዋ ሁሉ በኦሮሙማ የደህንነት ተቋማት ሥር ነው። ይህንን አውቃ ቤተክርስትያናችን ቀለል ያሉ ሰላማዊ ዬትግል መስመሮችን ደፍራ መጀመር ይኖርባታል። በተለይ በአዲስ አበባ። " ተማህፅኖ " የተባለው ቀልድ ነው። በዚህ ውስጥ ያለው ዕውነት የመንፈስ የሥነ ልቦና ካቴና ነው። ስለሆነም ቀደም ባሉ ቀናት እንደፃፍኩት የደወል አቤቱታን ለእዮር የምታቀርብበት ንድፍ ሊኖራት ይገባል። አሁን ሦስት ቀን ምህላ አውጃለች። ከምህላው ፍፃሜ በኋላ በሁሉም አብያተ ቤተክርስቲያናት የአንድ ሰዓት የደወል ፕሮግራም ሊኖራት ይገባል። ይህን ሳያቋርጡ በተለይ አዲስ አበባ በሁሉም አድባራት በዬሳምንቱ ለምሳሌ ከጥዋቱ ፬ ሰዓት እስከ ፭ ሰዓት በደወል ፈጣሪያውን መጠዬቅ። ይህ አንድ ሰው ብቻ የሚፈፅመው ቀላል፣ ሥልጡን፣ ብዙ ሚስጢራትን የያዘ ተጋድሎ መስክ ነው። የኔታዋ የኦሮሙማ ፖለቲካ መተንፈሻዋን ሙሉ ለሙሉ ከመከርቸሙ በፊት፣ መንበረ ፓትርያርኩ ከመደፈሩ በፊት፣ ብፁዐን ወቅዱሳን አባቶቻችን ከማጣታችን በፊት ቢያንስ የደወል አቤቱታ ፕሮግራሙን ደፍራ ትጀምረው። ወስብሃት ለእግዚአብሄር።

ጊዜውን ያላባከነ ሰው ሞተ አይባልም። አረፈ ይገልጽልኛል።

ምስል
      በሌላ በኩል ትውልድ የተካም ሞተ ሊባል አይገባም። ተክቷል እና። ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ሠርቷል። ጊዜው አልባከነም። እወላጅ አባቱንም፤ ባለቤቱንም በወል አጥቶ ያን ተቋቁሞ አገልግሎቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። ጋዜጠኛው ፀጋውንም አልተላለፈም። ፀጋው ጋር ተዋህዶ ፀጋውን አስከብሮ በትውልዱ ድልድይ ሠርቶ፤ ባትሎ፤፥ተግቶ፤ ታትሮ ወደ ጠራበት ጽረ አርያም ሁሉንም ሰጥቶ ሳይሰስት፤ ሁሉንም ለግሶ ሳይንቆጣቆጥ እና ሳይለግም ወደ ዘላለማዊ ህይወቱ ገስግሷል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መልዕክት፤ መክሊት፤ ጥሪ ይዞ ይወለዳል የምለው ፍልስፍና አለኝ።   እንዲሁም ትልቅ ሰው ሞተ አይባልም። ትልቅ ወንዝም ደረቀ አይባልም። ዕድሜ ዘመኑን ጥቅም ላይ የዋለ ቋሚ አሻራን በእጁ ያበጀ ትልቅ ሰው ህልው ነው። መንፈሱ ይኖራልና። ተግባሩ ይሰጣልና። ድርጊቱ ቁሞ ያስተምራልና። ዛሬ ጋሼ አማኑኤልን፤ ጋሼ ዘውዱን ጋሼ ተክሌ መጡብኝ። ድምፃቸው ሽው ውል አለብኝ። ሦስቱም የጀርመን ድምጽ የአማርኛ ቋንቋ ክፍል ባልደረቦች ኃላፊወች እና አስተዳዳሪወች ነበሩ። ለዛቸው ቃናቸው ጣማቸው ትውልድን በሙያ የመቅረጽ ቅንነታቸው ልዩ ነበር።   ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻም መልዕክቱን አድርሶ፤ ጥሪውን አንሰራፍቶ፤ መክሊቱን አቆላምጦ እና አለምልሞ የኖረ ሰው ነበር። ፍቅር ሰጥቶ ፍቅርን በገፍ ያለ ገደብ ያገኜም ዕድለኛም ሰው። ሚሊዮኖች የዚህ ዕድል ባለቤት ሳይሆኑ ያልፋሉ። እሱ ግን ዕድለኛ ነው። ሁሉን አይቶ፤ ሁሉንም አጣጥሞ ተወዶ፤ መውደድን አከፋፍሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ታላቅነት በውል እንዲታይ ምክንያት ሆኖ አርፏል። እኛም ተከተይ ነን። ቀሪ የለም። ልጁን ጃፒ እና መላ የኢትዮጵያን ህዝብ ቤተሰቡን እግዚአብሄር ያጽና። ቢያንስ ለቀሩት ጋዜጠኞች ፍቅርን ክብርን እንለግስ። ጨምተን ታግሰን ጋዜጠኞችን እንውደድ። እ

"የአማራ ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ ፌድራሉ ወሰነ" #ፋኖነት ደሜ ነው መለያዬ!

ምስል
  "የአማራ ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ ፌድራሉ ወሰነ" ይላል ፋሲሎ ኤችዲ። #ፋኖነት ደሜ ነው መለያዬ!     ያሰጋኛል ይላል ዝልግልጉ የኦህዴድ ሥርዓት የአማራን ፋኖ። ይህ ለአማራ ህዝብ ብቻ ነው። ይህ ማለት የአማራ ህዝብ አትኑር ማለት ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ የአማራ ህዝብ ፋኖ ነውና። ይህ ማለት እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ሲወለድ ፋኖ ሆኖ ነው የሚወለደው። አያውቁም። ጎንደር ልጅ ሲወለድ ቅቤ ይውጣል። ቅቤውን በአፈሙዝ እንዲውጥ ይደረጋል። እኔ እራሴ አቀባብዬ መተኮስ እችላለሁ። ሰልጥኛለሁ። ብሄድ ቀጥታ ውጊያ ወረዳ መግባት እችላለሁ። የከተማ ልጅ ነኝ። ግን ትውፊታችን ያ ነው። ኮልቷ፣ ክላሽኗን ተንተርሼ ነበር እማድረው። አዋና። ጫካዋንም አውቃታለሁ። ጉድቧንም። አቀበት ቁልቁለቱንም። ቆላ ደጋውንም። አትሰቡት። መላ ህዝቡ ይሸፍታል። ይሸፍትም! ያን ዘልዛላ የግርባው ብአዴን የምድር እንቧያችሁን ይዛችሁ ትቀራላችሁ። የምርኮ አለቃችሁን ጅጅጋ መላካችሁን ሰምቻለሁ። ለምን እንደሆን አውቃለሁ። አቶ ሙስጠፌ ኡመር። ተራቸውን የሚጠብቁ ለእርድ የተዘጋጁ ቀጣይ ኢላማችሁ ናቸው። አማራ ክልል አንድ ነገር ስታስቡ ለሚዛን እምትሮጡት ጅጅጋ ነው። አይምሰላችሁ። ሲከር ይበጠሳል። ሲሞላም ይፈሳል። አይደለም እናንተ ዲሞክራቶች በቀጣዩ ምርጫ የሚገጥማቸውን ፈተና ያወቁት አልመሰላቸውም። የአማራ ህዝብ አቅሙ ያልናቃት፣ ያልሸፈተባት፣ ያልተዋት ኢትዮጵያ ናት። የትናንትም፣ የዛሬም፣ የወደፊትም የአቅማችን ፏፏቴ ከዛ ይመነጫል። ትንታጎችን ሚሊዮኖችን በዚህች ቅፅበት ታጣላችሁ። ድምፃቸውን አጥፍተው በዝምታ ውስጥ ያለ አሉና። ምነው የእናንተ ኦነግ በጠራራ ጠኃይ ሥልጠና ሲወስድ፣ ሎጅስቲክስ ስታሟሉ አልጨነቃችሁ? ነፍሳችሁን ላቆዬ የአማራ ፋኖ ብድሩ ይህ ነውን? አትሰቡት። ሽፍትነ

12.01.2020 ከቶ አሁንስ ተረኝነት አለመሆኑን ተረዳን ይሆን?

  ከቶ አሁንስ ተረኝነት አለመሆኑን ተረዳን ይሆን?   ይህ መከራ ማለዳነቱ ለኢትዮጵያ ነው። አፍሪካም ቀጣይ ናት። የፖለቲካ አስተሳሰቡ ከፍ ወደ አለ ደረጃ ማደግ አለበት የምለው ለዚህም ነው። የሶልዳሪቲ ትግልም ያስፈልጋል የምለውም ለዚህ ነው። ጉዳዩ የተረኝነትም፣ የፈረቃም አይደለም። ከዛ ከፍ ያለ ነው። የኦሮሚያ አገራዊነት ዕወጃ ነው። የአማራ ሊሂቃን የተጨፈጨፋበት ሚስጢርም ይኽው ነው። የሰኔ 15 ቀን 2011 ዓም ትልም ይኽው ነበር እገታ። አዲስ አበባን ለኦሮምያ ርክክቡ የተፈፀመው መስከረም 5 ቀን 2011ዓም ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ። ዕውነቱ ይህ ነው። ስለዚህ በስክነት ቀጣዩን መራራ ተጋድሎ አህዱ ለማለት የጥምኖ ጊዜ መውሰድ እና በጥበብ ቀጣዩን ምዕራፍ መጀመር ነው። መደናገጥ አያስፈልግም። የሰው ልጅ ደህና ከሆነ ፈቃደ እግዚአብሄር በራሱ ጊዜ የሚሠራው ታምር ይኖራል። ይህም ለበጎ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይገባል። ከዚህ ቀጥሎ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በቁም እስር ላይ እንደነበር ይታወቃል። በቀጣይ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ አይታወቅም። መራራው ጊዜ የገባቸው ጥቂት ስለነበሩ አሁንም አዲስ የመማሪያ ሌሰን ለተኙ ሁሉ ተሸልሟል። ጃዋሪዝም ይህን ይመስላል። የፈለገውን የማስፈፀም ሙሉ አቅም አለው። ኢትዮጵያዊው ሰው ቀፎውን ነው ያለው። ተቦርቡሮ፣ ተጎርጉሮ ደመ ነፍሱን ነው የሚንቀሳቀሰው። ነገስ? በእንቅልፋችን ልክ ይወሰናል? አይዞን። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ፅናት ብቻ ሳይሆን በአብይዝም እና በተደማሪ የወግ ገበታ እራስን አለመገበር ይጠይቃል። የባልደራሱ ባለ አደራው ትውልዳዊ ድርሻውን በሚገባ ተወጥቷል። አደራውን በሚገባ አሳክቷል። ቀጣዩ ጉዳይ ህልውናውን የተነጠቀው ህዝብ የልዕልና ልቅና ምላሽ ነው የሚጠበቀው። ኢትዮጵያ አጥር ውስጥ ናት የ

በትውልድ ግንባታ ላይ መብት ኖረንም አልኖረንም መሳተፋችን አይቀሬ ነው።

ምስል
  በትውልድ ግንባታ ላይ መብት ኖረንም አልኖረንም መሳተፋችን አይቀሬ ነው። "ዬሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)     አጤ ፌስቡክ ከቶ ደስብሎህ ሰነበተን? ግብት ስል ማስጠንቀቂያውን ይዘህ ከቸች ትላለህ። ዬሆነ ሆኖ ዛሬን ዕለቱን በጦቤያው ጥር 6/2015ን ቅኝት ላድርግ ብዬ ጎራ ብያለሁኝ። ዋርካ ያለው ጥላ ይኖረዋል። ዬተከበረው ዬሁለመና ሁለመና ጋሽ ግርማ በዬነ፤ ዬተከበረው ዬሁለመና ሁለመና ጋሽ ይልማ ገብረአብ መኖራችሁ ተስፋችን ነው። የተስፋ እርግብ በር። ለዝግጅቱ ግርማ ሞገሱ ጉልላቱ ነበራችሁ። ኑሩልን። አሜን። ዛሬ ዬፋና ላምሮት ዬአሸናፊወች አሸናፊ ውድድር ነበር። ስከታተለው ነበር። አስተያዬትም ስሰጥበት ነበር። ትውልድን ለመቅረጽ ዬሚደረገውን ሁለገብ ጥረት መደገፍ የዜግነት መብት ሳይሆን ግዴታም ነው። ዬእኔ እንደ ጥሪዬ ዬማዬው ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ይህ መጀመሩ አበረታች ነው። ሙዚቃ ዬመኖር የውስጥ ሙዳይ ነው። ደስታህን፤ መከፋትህን፤ ሲቃህን ቅኔህን፤ ቃናህንም፤ ታሪክህ፤ ማንነትህ፤ ነፃነትህ የሰጠህ የምትገልጽበትም። ሙዚቃ ላይ እኔ እምብዛም ብሆንም ግን በጥበብ ቤተኝነቱ፤ በሥነ - ፁሁፍ ለዛ እና ጣዕሙ መመሰጤ አይቀሬ ነው። ዬፋና ላምሮት ዬሥራ አስፈፃሚው ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው "ዬእኔ፤ ያገባኛል" ዬሚል ስሜት ፋና ላምሮት ፈጥሯል ሲሉ መግቢያቸው ላይ ገለፁ። አወን ተፈቀደልንም፤ አልተፈቀደልንም እንሳተፋለን። እኔ እርግብ በር፤ ዬተስፋ በር ሁለት መጽሐፌን የፃፍኩት፤ የምክር ዬመነሻ ሃሳቦች ናቸው ዓለም ዓቀፍ ውድድሮችን እዬተመለከትኩ ነበር። ክፍተቶችን አይቼ ገምግሜ ትውልድ እንዴት ይቀረጽ? ትውልድ እንዲቀጥል እንዲህ ያሉ ነፍስ ሆነው ነፍስ ዬሚዘሩ

Das Reinste in der Liebe ist Klarheit.

ምስል
  Das Reinste in der Liebe ist Klarheit.    Das Wasser, das vom Himmel kommt, ist sauber. Liebe braucht Klarheit, wie Wasser am Himmel. Dies ist normalerweise nicht der Fall. Dies ist eine Lektion, die wir aus der Natur der Liebe gelernt haben. Transparenz ist übrigens ein eigenständiges Thema. Deshalb sage ich, die Natur der Liebe ist der Ozean. Die Natur der Liebe selbst kann dir inneren Frieden bringen, wenn du daran denkst. Die Natur der Liebe ist eine facettenreiche Generation. Für mich ist die Natur der Liebe eine Generation. Oder der 13. Planet. Was wir noch nicht recherchiert haben. Abgesehen von der Natur der Liebe, wie viele moderne Projekte hat unser Planet geplant? Können wir die Jahre seit der Erschaffung der Welt zählen? Kann er es platzieren? Bitte gehen Sie vor Gericht und fragen Sie die Wissenschaftler? Auf Wiedersehen, bis wir uns in meinem nächsten Beitrag treffen. Ich wünsche Ihnen einen schönen Tag. Gott das Heilige Land Schweiz; Heiliges Land Äthiopien; Schütze di

አርበኛ ጎቤ የዘመን ንጥር

ምስል
  አርበኛ ጎቤ የዘመን ንጥር   ጥቃት አውጬ ጥንድ የብረት አጥር። የዕውነት ዓይን ባለ ሙሉ ዝናር የእሱዪ አባት የዘመን በር አንበሳው ጎቤ፣ አርበኛው ጎቤ አታስደፍር! ዋዋ ዓለሙ ለምለሙ፣ ሲሳይ አዳሩ ለአድባሩ፣ ሁሉን የሰጠህ ለቃሉ፣ ለውለ - ግብሩ የኪዳን ማደሪያ ነው ሥሩ! የፍኖ አባት ግንደ ፍኖተ - ዘሩ አትንኩኝ ባይ፣ ሲነካበት አድባሩ! የአማራ ትርታ ህብርህ! ያበራል ገና ጉልላትህ። ይደምቃል ዘውዱ በበላይህ ዘልቋል ዘምኗል ፋናህ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/01/2022 18.59 ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር

የገዳ የሰበር የሲቃ - ህቅታ - በትንታ - ህማማት!

ምስል
  የገዳ የሰበር የሲቃ - ህቅታ - በትንታ - ህማማት!   ስክን እርግት ህይወት! ዘመኑ በመጨመት ይሁን በአስተውሎት። ማረግረግ በጥድፈት አያሻትም እናት ብልህነት - በስክነት ለሱባኤው ህማማት! ሲተመተም ሲጉተመተም የህምምታ አውዳመት የሰኔል የቹቻ ረከቦት እሽቅድድድምሾ የአልቦሽ ሂደት። የቃጠሎ የአመድ ቅልቅሎሽ ግሳት የድንጋይ የአካፋ የዶማ ክሳት የአፈር ደለለል ሁካታ በእልልታ ያለለፈው የገዳ ሆታታ የለት ተለት // ቱማታ የሰበር ትንታ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 14/01/2022 18.31 ለዘመነ ኦህዴድ ይሁንልኝ።